አረመኔው የሕወሐትና የደሕንነት ሹም – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ የነበረው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል ከያዘው ስልጣን መነሳቱን ምንጮች በመጥቀስ ከሁለት ወር በፊት ዘገባ አቅርበን ነበር። በጭካኔው የሚታወቀውና በሙስና የተነከረው ወ/ስላሴ በሙስና ዘብጥያ ወርዷል። በእስር ቤት በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን ያሰቃይ የነበረው ወ/ስላሌ ከበረሃ ጀምሮ በርካታ የድርጅቱን ታጋዮች በመረሸን እንደሚታወቅ ባለፈው ዘገባ መገለፁ ይታወሳል። በትግሉ ዘመን የፓርቲው አባለት « ፆታዊ ግንኙነት ስታደርጉ ተገኝታችኋል…» በሚሉና ሌሎች ተልካሻ ምክንያቶች እንዲረሸኑ በበላይ አመራር ውሳኔ የተላለፈባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፓርቲው አባላት (ታጋዮች) ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት መካከል ኢሳያስና ወ/ስላሴ ዋናዎቹ ነበሩ ። አቶ መለስ ሁለቱን አባላት ወሳኝ በሆነው የደህንነት ቢሮ ቁልፍ ስልጣን የሰጧቸው « አድርጉ » የተባሉትን ያለማመንታት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ወ/ስላሴ ስልጣን በጨበጠ ማግስት በአንድ ቀን አርባ የቢሮው አባላትን ( መኮንኖች ተብለው ነው የሚጠሩት) እንዳባረረ የገለፁት ምንጮቹ፣ በየጊዜው በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላትን « ተሃድሶውን አልተቀበላችሁም፣ የቅንጅት ደጋፊዎች ናችሁ..» በሚሉና ሌሎች ምክንያቶች ከማባረር – እስር ቤት እስከመወርወር የደረሰ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል። ከመለስ ጋር በሃሳብ ያለተስማሙ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትን በገዛ መኖሪያ ቤታቸው በገመድ በማነቅና በስለት በማረድ የጭካኔ ተግባር ያስፈፀሙት ወ/ስላሴና ኢሳያስ መሆናቸውን ተገልጧል። በግፍ የተገደሉት የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነውና የቤተመንግስት የደህንነት ሹም አቶ ዘርኡ ናቸው።
መስከረም 2 ቀን 1996ዓ.ም የኢትኦጵ ጋዜጠኛን ቢሮው በማስጠራት ለሁለት ሰአት ያክል ካስፈራራው በኋላ እንደሚገድሉት ዝቶ አሰናበተው። ጋዜጠኛው በ15 ቀን ውስጥ አቋሙን አስተካክሎ፣ የመረጃ ምንጮቹን አሳልፎ ካልሰጠ እንደሚገደል ነግሮ ያሰናበተው አረመኔው ወ/ስላሴ፣ መስከረም 20 ቀን 1996ዓ፣ም ሰባት የፌደራል ፖሊሶችን በማሰማራት ጋዜጠኛው የግድያ ሙከራ እንዲፈፀምበት አድርጓል። ፖሊሶቹ አካሉን ካጎደሉትና ክፉኛ ከደበደቡት በኋላ ድልድይ ውስጥ ወርውረት እንደሄዱ ይታወቃል። በ1997 እና 98 ዓ.ም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተወሰደውን ጭፍጨፋ፣ እስርና ድብደባ ከጠ/ሚ/ሩ ትእዛዝ በመቀበል ተፈፃሚ ያደረገና ዋና ተዋናይ የነበረው ወ/ስላሴ፥ ዜጎች ያሰቃይበት ወደነበረው ማእከላዊ እስር ቤት ተወርውሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዶ/ር ቴዎድሮስና ሌሎቹ !
Share