በእሬቻ በአል በተወሰደው ግፋዊ እርምጃ ላይ የተለያዩ ከተሞች እና ከፊል አዲስ አበባን ጨምሮ የተቃውሞ አሰሙ በወያኔ ንብረቶች ላይ እርምጃ ወሰዱ።

(ዘ-ሃበሻ)በእሬቻ በአል ላይ በጨካኙ የወያኔ ሰራዊት የተፈጸመው ህዝባዊ ተቃውሞ በጃሞ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ ክልሎች እየተዛመቱ መምጣቱ ተገልጦአል ። በአዲስ አበባም የተለያዩ የንግድ ሱቆች ተዘግተዋል ። በሌሎችም ቦታዎች የኦሮሞ ተወላጆችም ሆኑ ሌሎችም ዜጎች በህብረት የኦሮሞ ህዝብ ነጻ መሆን አለበት ግድያ ይቁም ፣ወያኔ ከስልጣን ይውረድ በማለት ከፍተኛ ድምጽ በማሰማላት ላይ ይገኛል ።
በአለም ገና ሞጆ ፣ቡራዩ እና ሌሎችም ቦታዎች ከፍተኛ ንቅናቄ ከመታየቱም በላይ በአሸዋ ሜዳም ከፍተኛ ሃይል ያለው ህዝብ ወደ ከተማ በመግባት የተለያዩ ድምጾችን አሰምቶአል ፣መንገዶችም ተዘግተዋል ። የትራንስፖርት አገልግሎቶች የቆሙ ሲሆን የአጋዚ ጦርም በተለያዩ ቦታዎች ተሰግስገው የገቡ ሲሆን በአንዳንድ ቦታውችም በንጹሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ ።
ትምህርትቤቶችም በጊዜ የተዘጉ ሲሆን በሰሜን ሸዋ በሰላሌ አካባቢ ህዝቡ በአደባባይ ከገበሬው ጋር በመተባበር ወደ አደባባይ ወጥተዋል ። በሌሎች ገጠር ከተሞች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ቀጥሎአል ተቃውሞው በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚዛመት ምንጮቻችን ገልጸዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “በኢሕአዴግ መንግስት የሕግ የበላይነት ጭላንጭል በሐገራችን እየተዳፈነ ነው” – (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)
Share