የጅምላ እስርና ግድያ እየፈጸሙ ያሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግድያና ጅምላ እስር እየፈጸሙ ያሉ ባለስልጣናት ሆነ የጸጥታ ሃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ጠየቀ።
አለም አቀፍ ህብረት ለኢሳት በላከው መግለጫ ህዝብን ማገልገል የሚገባው መንግስት ዜጋውን እየጨፈጨፈ መቀጠል ስለለለበት ስልጣንን መልቀቅ ይኖርበታል ብሏል።
ከዚህ በኋላም የሚፈጸም ግድያና ጅምላ እስር በአስቸኳይ እንዲቆም አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች አንድነት በመግለጫው ጠይቋል።
ህብረቱ ለኢትዮጵያ ህዝብን የሚያገለግሉና በዕውቀት የሚሰሩ መሪዎች እንድሰጣት ሁሉ በጸሎት እንዲተጋና ህገወጥ ድርጊቶችን እንዲያወግዝ ጥሪን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መዋቅርና ሃብቷ በዘር ሃረጋቸውን በፖለቲካ አቋማቸው ከገዢው ፓርቲ ጋር በወገኑ ሰዎች እየተበዘበዘ መሆኑን ህብረቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አብራርቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አድዋ የድል አምባ (ተፈራ ድንበሩ)
Share