ሕብር ራድዮ ሙሉ ፕሮግራም: የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት.. እና ሌሎችም

/
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 18 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…መንግስት ራሱ ገዳይ ሆኖ በራሱ መዋቅር ውስጥ ያለ ከዚህ ቀደም ባለው ሪከርድ የመንግስትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመሸፋፈን ብቻ ሳይሆን ያንን የሚያጋልጡ ሪፖርቶችን የሚያወጡትን የሚያወግዝ የስርዓቱ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ የተደረገውን ግድያ አጣራለሁ ማለቱ ተአማኒነትም ተቀባይነትም የሚያመጣ አይመስለኝም …የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን መረጃ በተመለከተ ይሄ ተቋም መረጃዎችን ለማሸሽም ሆነ ለመደበቅ ከመሞከሩ በፊት ግን… >

አቶ ያሬድ ሀ/ማሪያም የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ከቤልጂየም   በወቅታዊ አገዛዙ ራሱ ገሎ ራሱ አጣራለሁ ስላለው የኦሮሚያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት   ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ   (የመጀመሪያውን ክፍል ያዳምጡት)

 <…የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከተለያዩ ማህበረሰብ የመጡ የነገዋ ኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስባቸው በሚያስማማቸውም በሚለያዩበትም ጉዳይ በቪዥን ኢትዮጵያው ጉዳዔ ላይ መክረዋል። ይሄ አስደሳች ነው   ኢትዮጵያውያን ለመተማመን መነጋገር አለብን ነው የእኛ መርህ እኔም በዚያ ተገኝቼ የሲቪል ማህበረሰቡ ሚናን በተመለከተ በተሰጠኝ ርዕስ ተናግሬያለሁ ይህ መሰሉ ውይይት በየቦታው መቀጠል አለበት የእኛም በሚኒሶታ በቅርቡ የምናደርገው ውይይት ጠቀሜታው ይሄው ነው።መነጋገር መቀራረብ መስማማት ያለብን ዛሬ ነው… >>

 አቶ ኦባንግ ሜቶ በዋሽንግተን ዲሲ ቪዥን ኢትዮጵያ ከኢሳት ጋር ያዘጋጁትን ጉባዔ አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…የአሜሪካ ምርጫ በአሜሪካ የምንኖር ኢትዮጵያውያን የመምረጥ መብት ያለን መብታችንን ተጠቅመን መምረጥ አለብን…ከኢትዮጵያ የወደፊት ጉዳይ አንጻር ሳየው ከኦባማ አስተዳደር የክሊንተን የተለየ አይመስለኝም ። በበኩሌ ትራምፕ የሚያሸንፍ አይደለም ቢሆን ደስ የሚለኝ በርኒ ሳንደርስ ነው ግን የኔ ግምት… >

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሃይማኖት አባቶችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የካናዳ ፓርላማ አባላት በተሳተፉበት ውይይት ለሃገራችን ችግሮች አማራጭ አቀረቡ

አቶ ከባዱ በላቸው ከዋሽንግተን ዲሲ የአሜሪካን የምርጫ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን መራጮች ያለውን ጠቀሜታ አስመልክቶ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡን ምላሽ( ሙሉውን ያዳምጡ)<… በምርጫው ውስጥ ያለንን ተሳትፎ ማሳደግ የመምረጥ መብታችንን መጠቀም እኛንም ሆነ ልጆቻችንን የሚመለከት ጉዳይ ነው ።የዲሞካራት ፓርቲን በተመለከተ አሁን ካለው የቅድሚያ የምርጫ ሒደት አኳያ ክሊንተን እየመራች ነው ።ፓርቲውን ወክላ ተወዳድራ ካሸነፈች የኦባማ አስተዳደር የሚከተላቸውን ጉዳዮች የምታስቀጥል ነው…የኔም ግምት…>

አቶ ዮሴፍ መንገሻ በቬጋስ የቀድሞው የኢትዮጵያ ራዕይ ማህበር ዋና ጸሐፊ ስለ አሜሪካ ወቅታዊ ምርጫ ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉ ውይይቱን ያዳምጡት)

<…የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣው በቬጋስ የታክሲ ሊዝ ስለሚደረግበት ሁኔታ የሚመለከተው በአግባቡ መታየት አለበት ። ዲፖዚት ያስቀምጣል ይላል ይሄ ዲፖዚት ምን ያህል ነው ከዲፖዚቱ ላይ ኩባንያው የሚቀንሰው ለእንዴት ላሉ ጉዳዮች ነው? ግልጽ አይደለም…>  

አቶ ቢኒያም ሰመረአብ የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያወጣውን የታክሲ ሊዝ ተግባራዊ ስለሚሆንበት ሁኔታ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)የአውሮፓ ሕብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች (ናቶ) መዲና በሆነችው ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ የሰሞኑ የሽብር ጥቃት ጠንሳሾች ማንነት እና ዓለማቀፋዊ ምላሾቹ ሲቃኙ ( ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም

 ዜናዎቻችን

የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማሳፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ አውጥቷል የሚል ወቀሳ ቀረበበት

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቻይና ዕዳ ሳቢያ ጥንቃቄ ካልታከለበት ሊንኮታኮት እንደሚችል ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ አስጠነቀቁ

በማዕከላዊ የታሰሩ የኦሮሞ ተወላጆች በረሃብ አድማ ሳቢያ ጉዳት ደርሶባቸው 31 ሆስፒታል ገቡ

በጎንደር ኳስ ጨዋታ ለማየት በስታዲየም የተገኘው ሕዝብ አገዛዙ በወልቃይት ላይ የሚወስደውን ግፍ አወገዘ

ተጨማሪ ያንብቡ:  40 ወታደሮች ፋኖን ተቀላቅለዋል | ጄነራሉ በፋኖ ተማረከ | “ህወሓት ከፋኖ ጋር” ጠ/ሚኒስትሩ፣

ይለያል ዘንድሮ የኢህአዴግ ኑሮ ሲል ተቃውሞ አስምቷል

በኢትዮጵያ የተከሰተው የረሃብ አደጋ አስከፊ እየሆነ መሄድ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆነ

በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬም አላባራም

በትግራይ የባጃጅ ሾፌሮች የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ታገደ

በአዲስ አበባ ታክሲዎች ዳግም የስራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ የሚል ግምት አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Share