የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ አካሄደ የወቅቱን ሁኔታ ገምግሞ የጋራ ትግሉንለማጠናከር ተጨማሪ መመሪያ ሰጠ

የካቲት 7 ቀን፣ 2008 (ፌበርዋሪ 15፣ 2016)

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ)

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) የአመራር ምክር ቤት ቅዳሜ ጥር 28፣ 20008 (ፊበርዋሪ 6፣ 2016) መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። በዚህ ጉባኤው ምክርቤቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ሁኔታ፣ በህዝባችን ትግል አኳያ የሚታዩትን ተስፋ ሰጭ ገጽታወችና አሳሳቢ ክስተቶችን በሰፊው ገምግሟል፡፤ የሸንጎ የተለያዩየስራ ክፍሎች የሚያካሆዱትን ተግባር በተመለከተ የቀረቡትን የስራ ሀገባወች መርምሯል፡፡ በመቀጠልም በህዝበችን ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ግፍ ሊያከትምእንዲችልም መካሄድ በሚገባው ትግል ላይ አስፈላጊውን የተግባር መመሪያወች ሰጥቷል፤ የትግል ጥሪም አስተላልፏል።

የ25 አመቱ የህወሀት/ኢህአዴግ አምባገነን የግፍ ስርአት ኢትዮጵያን አደጋ ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያውያንን አስመርሯል። በሁሉም የሀገራችን ክፍል የሚገኘውኢትዮጵያዊ ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት እውን የሚሆንበትን ጊዜ ናፍቋል።  መናፈቅ ብቻም ሳይሆን፣ አንድነቷ በተጠበቀ ኢትዮጵያ ስር መብቱንለማሰከበር፣ የህግ የበላይነትን እውን ለማድረግ፣ ከፋፋይ ስርአትን ለማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየቦታው ተቃውሞውን በተለያየ መልክ በመግለጥ ላይ ይገኛል፡፡ህዝባችን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል መብቱን ለማስከበር ከፍተኛ መስዋእትነትን በመክፈል ላይ ነው። ስርአቱ በመፍረክረክ ላይ ይገኛል፣ክንዱ ዝሏል። አደንቋሪፕሮፓጋንዳው የሚያዳምጠው ጆሮ አጥቷል። በሀገራችን ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚያሳየው ሀገራችን  የለውጥ ዋዜማ ላይ መሆኗን ነው።

በዚህ አኳያ በአሁኑ ሰአት በመላ ሀገራችን በተለይም ደግሞ ኦሮሚያ፤ አማራና ጋምቤላ ተብለው በሚታወቁት ክልሎች  እየተካሄደ ያለውን የመብት ማስከበር ትግል፣የመሬት ቅርምትንና ዘረፋ የመቃወም ትግል ፣ አግላዩን የፖለቲካ ስርአት በመቃወም፣  የሚደረገውን ትግል የመሰረታዊ መብት መገፈፍን፤ በቃኝ በማለት የስርአቱንጨቋኝ  አገዛዘ እንዲወገድ የሚደረገውን ትግል፣ ስርአቱ በተከታታይ የሚያካሂደውን ህዝብን የእርስ በርስ የማጋጨት ተግባር  በመቃወም የሚደረገውን የህዝብእንቅስቃሴ  ሽንጎ ካሁን በፊት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ይደግፋል፣ የትግል አንድነቱንም ይገልጻል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መቆሚያ ያጣው በመተከል ያሉ ሰዎች እልቂት! - ኢሰመጉ

ስርአቱ ለዚህ የህዝብ ትግል ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ እንደተለመደው በማን አለብኝነት ለማፈን የሚወስደውን የሀይል እርምጃ፣ እስራት፣ ድብደባና ግድያ ምክርቤቱ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ አሁንም ያወግዛል።  በደል ለደረሰባቸው ሁሉም የሀዘናቸው ተካፋይነቱን ይገልጣል።  ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዞም የታሰሩት ሁሉባስቸኳይ እንዲለቀቁ ንብረታቸው ለጠፋው እንዲሁም በስርአቱ የጸጥታ ሀይሎች ለተገደሉ አስፈላጊው ህጋዊ ካሳ ለቤተሰቦቻቸው እንዲከፈልና ገዳዮቹም ሆኑ ትእዛዝሰጭዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ትግሉን እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ይህን የህዝብ ትግል ለጠባብና ከፋፋይ አላማ ሊያውሉት የሚጥሩትን አንዳንድ የውስጥም የውጭም ሀይሎች እንዲሁም የስርአቱን ደባ ሁሉምኢትዮጵያዊ በጥንቃቄ ነቅቶ እንዲከታተልና የከፋፋዮች ሰለባ እንዳይሆንም፡ ነቅቶ እንዲጠብቅ አሳስቧል።

የህዝባችንን የትግል መነሳሳት ወደተፈለገው የስርአት ለውጥ እንዲያመራ የተቃዋሚው ወገን ታላቅ ሀላፊነት እንዳለበትና  በተናጠል የሚደረግ ትግል ለስርአቱ እድሜመራዘም የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመገንዘብ ይህን ሁኔታ ለመቀየር የሚያሰችል አስተማማኝና ቀጣይ ትግል ለማካሄድ ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በጋራለመስራት በሽንጎው በኩል የሚደረገውን ጥረት ከመረመረ በኋላ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮና ቅድሚያ ተሰጥቶት አንዲቀጥል፣ ሌሎች የአንድነት ሀይሎችም የጋራትግሉን እውን ማድረግ አጣዳፊነት ተረድተው ጠንካራ የተቃዋሚ ህብረት በመመስረቱ ተግባር ላይ በጋራ መረባረብ ይገባቸዋል ሲል ምክር ቤቱ ለሁሉም የአንድነትሀይሎች የትብብር ጥሪውን በድጋሜ አስተላልፏል።

የህወሀት/ ኢህአዴግ አምባገነን ስርአት ዕለታዊ ተግባር በሀገሪቱ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲጠፋ እያደረገ እንደሆነ አለም አቀፍ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ  ይህን አደጋ ለማስወገድም የኢትዮጵያ ህዝብ  ለመሰረታዊ መብቱ መከበርና ፣ ለህግ የበላይነት  የሚያካሂደውን ትግል  እንዲያግዝ  ከምን ጊዜውም የላቀ ዲፕሎማሲያዊ ትግልእንዲካሄድ ምክር ቤቱ ተጨማሪ መመሪያ ሰጥቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በልደታ ለአንድ ንግድ ቤት በካሬ ሜትር 71,770 ብር የመጫረቻ ዋጋ ቀረበ

በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመሰረታዊ ጥያቄዎቹ መልስ ማግኘት ማለትም ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር፣ ራሱ የመረጠውና የሚቆጣጠረውመንግስት ለመመስረት፣ ለህግ የበላይነት መከበር፣

 

1 Comment

  1. ምን አዲስ ነገር አለ አሁን እዚህ? መመሪያ ..መመሪያ መመሪያ..ዘላለም መመሪያ..

Comments are closed.

Share