“እንኳን ኣደረሳቹ” …! ( ከወይዘሮ ኣልጋነሽ ልጆች )

የተከበራቹ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለበዓለ ልደት በሰላም ኣደረሳቹ ኣደረሰን የሚሏቹ የጀግናዋ ወይዘሮ ኣልጋነሽ ገብሩ( ኣሸባሪነትና መንግስት በሃይል ለመገልበጥ በሚል ክስ ተፈርዶባት ለ3 ዓመት ወህኒ የወረደችው ) ልጆች ግርማነሽ ታደሰ፣ ዘነበ ታደሰ፣ ገብረሂወት ታደሰ ናቸው።

የጀግናዋ ልጆች ይሄ መልእክት ያስተላለፉላቹ ትናንት 27/ 04 / 2008 ዓ/ም በኣንድ በጎ ኣድራጊ ወጣት ኢትዮጵያዊ ልጆቹ በናታቸው መታሰር እንዳይከፋቸውና ለልደት በዓል መዋያ እንዲሆናቸው በማለት የላከው 1000 ብር ( ኣንድ ሺ ብር ) ብር ይዘን በኣካል እግሪሓሪባ ቀበሌ ተገኝተን ስንሰጣቸው ነው።

የጀግናዋ ልጆች ከዚ በፊት የተቻላቹ ድጋፍ ያደረጋቹላቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ኣመስግነዋል።

እኛም በዚህ ኣጋጣሚ ወጣት ወገናችንና ሌሎቻቹ ከዚ በፊት ልጆቹ ለጎዳና ተዳዳሪነት እንዳይጋለጡ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ላደረጋቹላቸው በሙሉ በማመስገን ለክርስትና ሃይማኖት ከተከታዮች ወገኖቻችን መልካም በዓል ይሁንላቹ ለማለት እንወዳለን።

+ርሑስ በዓል ልደት+

+መልካም የገና በዓል+

አሜን…

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በቋራ ለነጻነታቸው የሚታገሉትን ለማጥቃት የሔዱ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጉዳት ደረሰባቸው | በወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
Share