(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ

October 28, 2015

(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓ የተለያዩ ሃገራት በማጥመቅ ላይ ቆይተው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት መምህር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመምህሩ ቅርብ ሰዎች የሆኑ ታማኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተጠቅመው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በማስተማር እና በማጥመቅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ነው የታሰሩት::

በአገልግሎታቸው የተነሳ በወንጀል እንደሚጠየቁ በፖሊስ እንደተነገራቸው የተገለጸው መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ላይ ውለው ምርመራቸው እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ምንጮቻችን የሚያደርሱንን መረጃዎች ይዘን እንቀርባለን::

8 Comments

 1. this is outragious how coame you are aressting someone who is healing and helping desperate and valnourable people who are possesd by the devil and saitan unless you people you are after the money he gets it from his followers he is not even using it for personal need but he is using it for repairing the old ones and building the new ones so why you arestting him?now you turn many of your supporters even against your party and government.stop this none sense attack against innocent people.after all you are leading people so do not turn yourself against your own people.

  • Neknik, you sound your self “yete Nekenekih timesilaleh” nothing to do with government. Orthodox leaders are after the case. we expect justice in this case Kes Girma make a big mistake faking stamps and writing letter to loot innocent Ethiopians all over the world. ha ha ha

   Matty

 2. የማንም ስራ ፈትና ቀን የጎደለበት ሁሉ ተአምር እንዲፈጠርለት ይፈሊጋል. የምን አጋንንት ነው? ኢትዮጵያዊ የአጋንንት ቤት ማን ነው ያደረገው? ምን ነዉ ፈረንጆች አያጉአሩም? ድንቁርና ነው ..ምድረ ኪሳራም ሁሉ..በጣም ከጥቂቶች በሽተኞች በቀር ሑሉ አውቆ አበድ ነው:: ገንዘቡን ሲያባክን ኑሮ ተመተተብኝ ይላል…መስራት ሰንፎ ጫትና አረቒ ሲጠጣ ኖሮ አዞሩብኝ ዪላል….ማፈሪያ ሁሉ ..አለም ዪስቅብናል…..መንግስት አገር ወዳድ ሁሉ ዪህን ድርጊት በጣም ሊያወግዙትና እርምጃ ሊወስዱ ዪገባል…ቄስ ግርማ በደካማ ህብረተሰብ የሚነግድ ራስ ወዳድ ግለሰብ ነው እንጂ ምንም አይነት መለኮታዊ ግንኙነት ከፈጣሪ ጋር የለዉም…ካለዉም ከእርኩሳነ መናፍስት ጋር ነው…የይህ የሚያስቆጣዉ ይጸልይና እዉነቱን ዪረዳ….ዘራፍ እላለሁ ካልክ አንተም ደንቁረሃልና ብርሃን እስኪበራልህ በጨለማህ በሰላም ኑር….አምላክ በሰጠን ዐእምሮ ተጠቅመን በሽታን መዋጋት ከቻልን 100 አመታት ተቆጠሩ ገናም ብዙ እንሰራለን….አጭበርባሪዎች ቦታ የላቸዉም……

  ማቲ

 3. “መምህር ግርማ ወንድሙ በእስጢፋኖስ ቤ/ክ ከቀኖና ውጭ የማጥመቅ ሥራ እየሰሩ ነው በሚል መታገዳቸውን፤ የእገዳ ደብዳቤውን ጭምር በማያያዝ ዘ-ሐበሻ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም። ይህን እገዳ ተከትሎም መምህር ግርማ “እኔ አስማተኛ ወይም ጠንቋይ አይደለሁም” በሚል ለላይፍ መጽሔት የሰጡትን ቃለምልልስ በዘ-ሐበሻ ላይ አስነብበን ነበር። አሁን የደረሰን መረጃ ደግሞ የመምህር ግርማ ዜናን የሚቋጭ ይግሆናል።
  የዘ-ሐበሻ ምንጮች በማስረጃ አስደግፈው እንዳደረሱን መረጃ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ፈቃድ በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ የወንጌል አገልግሎትና እንዲሁም የህሙማን ሐብተ ፈውስ እንዲሰጡ ተፈቅዶላቸዋል። ከምንጮቻችን የደረሰን የተፈቀደበት ደብዳቤም የሚከተለው ነው።
  – See more at: https://zehabesha.info/archives/13144#sthash.LP56fmot.dpuf
  ፩) ህወአት/ኢህአዴግ ከመቼ ጀምሮ የሃይማኖት ተቆርቋሪ ሆነ?
  ፪) ግለሰቡ ከማጥመቅ ያገኙትን ገንዘብ ሁሉ ለተጠሩበት ሀገርና ቤተክርሰቲያን ይለግሱ የለምን?
  ፫) ማጥመቅና መፈወስ ክህሎትና ፀጋ በፈጣሪ አምላክ የተሰጠ እንጂ ከመንግስት አሳውቆና አስፈቅዶ ተጀመረ?
  ፬) ለመሆኑ እነኝህ ፈቃጅና አሳሳሪ ልማታዊ ሃይማኖተኞች ማስተማር፣ማጥመቅና መፈወስ ይችላሉን?
  ፭) የግለሰቡ አማኝና ተከታይ በባዛ ቁጥር የሚሰበሰብ ወርቅና ብር ለአውራው ፓርቲ አለመድረሱ አናደዳቸው?
  ፮) ቤተክሕነቱ ማስተማርና ማጥመቅ መፈወስን ከከለከለ ሕዝቡን በፖለቲካ እየጠረነፈው ምን እያደረገው ነው?
  ፰) ይህ ውንጀላ የኢህአዴግ የውጭ ሀገር ክንፍ ቤተክርስቲያን አባላት ስለጠፉባቸው የዘር ሸርና ተንኮል ይሆን?
  ፱) ህወአት/ኢህአዴግ በሄደበት ሁሉ የዘረኝነት የጎጠኝነት ክታብ አስጠልቆ ግራ ቀኝ አሸባሪዎችን በውስጥም በውጭም አሰማርቷል በአብዛኛው ኤርትራውያንን በብዛት መፈወሳቸው አሸባሪ ብሎ አስወንጅሏቸው ይሆን?
  ፲) ይህ በሃይማኖት ነፃነት የመንግስት አጋር /ተለጣፊና/ደጋፊዎች ስውር ሴራ ሃይማኖትን ማዳከም ይሆን?
  ፲፩) “አማራና ኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ወጣቱንም በማሰር በማምክን በማፍዘዝ በማሰደድ ሽማግሌና አዛውንት በመደብደብ፣ በማሥራብ፣ በማዋረድ፣ የተጀመረ.. እስከዘር ማጥፋት የሚዘልቀው ራዕይ በዚሁ ሲቀጥል አደለምን?
  ፲፪) ማሌሊት(ማርክሲስት ሌሊኒስት ፅንሰ አሳብ አራማጅ)አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፈላስፎች እንደ ታምራት ላይኔ አገላላፅ አምላክ የለም ብለው የተማማሉ ዛሬ እንዴት ስለሃይማኖት ተቆርቋሪ ሊሆኑ ቻሉ?።
  ፲፫) ለመሆኑ እነኝህ “ሃይማኖታችን ያለ ንግድ ፍቃዳችን” የሚሉ ሸቃዮች…ለተራበው፣ ለተጠማው፣ ለታረዘ፣ ለሚሰደደው፣በሰው ሀገር ለሚማቅቀው፣ በእሥር ለሚንገላታው፣ሥራ አጥቶ በይ ተመልካች፣ቤት አጥቶ ለሚኖሩ የሚያኗኑር፣ በተለያየ ሱስና ሴስ፣ ለተጠመደ ዜጋ ምን አድርገዋል? ምን እያደረጉ ነው?
  ፲፬) ቄስ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ የፖለቲካ ጥጥ በእየ ድረገፁ ከሚፈለቅቁ በሰው ችሎታና በረከት አይናቸው ደም ከሚለብስ የያዙት መስቀል ቢፈውስ፣ የሚረጩት ፀበል ቢያድን፣ ፀሎታቸው ለእግዝሐብሔር ቢደረስ፣ ሀገርና ሕዝብ በረከት ቢኖረው ዘለዓለም ውድቀት፣ ድርቅ፣ እርዛት፣ ቸነፈር፣ ግዜ ቆጥሮ ይፈራረቅብን ነበር?
  ፲፭)በግዱ የጉግ ማንጉግ የኮከብ ዓርማ የተሸከመ ባንዲራ ይዞ መቀሰፍ እንጂ ፈውስ የለም ማለታቸው ነው?
  *** እንግዲህ እላችኋለሁ አሳሳሪዎችና አሳሪዎች ብሔር፣ፖለቲካ፣ጥቅማጥቅመና የግል ቁርሾን በአጋጣሚ ለሃይማኖት ማፍረሻነት አትጠቀሙ! የግልና የቡድን ክፍፍልን አንፀባርቃችሁ ትውልድን ባልረባ ወሬ አታደንቁሩ ሃይማኖቱ ቃለአዋዲ (ሥርዓተ ሕግ) አለው።ሕዝብ ወሳኝ ነው ሕዝቡ ተታልያለሁ የግለሰቡ ሥራ ጥሩ አደለም ካለ በቦታውም አይገኝም ሀገርና አህጉር አቆራርጦ አይከተላቸውም።አንዳንድ ሃይማኖት አልባ የምሁር ደንቆሮዎች ብዙ ሲፈላሰፉ ይሰማል ይታያል ይነበባል ግን እነሱ ይህንን ሲሰሩ ማን ወክለው በየትኛው የሥነምግባር ሚዛን ይሆን ግለሰቡን የሚዘልፉት? እነማን ናቸው ?በሌሎች ሀገራት ያሉ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ሁሉ በህወአት/ኢህአዴግ ካልተጠመቁና አባል ካልሆኑ የሚሰሩት ስሕተት ነው ብሎ ማለት እራስን ጠባብ ታማኝ አብዮተኛ አድርጎ ማሳየት እንጂ ሃይማኖታዊ ቀኖና ያወቀ ወይም ብልህነት አደለም በለው!። ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን

 4. @matty ምን አባህ ነው የምትዘባርቀው ። በአንተ ቤት አሁን ተናግረህ ሞተሀል ፣ ምን ያህል ንፍጥ የሆነ አእምሮ አንዳለህ ነው የሚያሣየው ንፍጣም ።
  pleas በመጀመሪያ ይህን ንፍጥህን ህፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ብለህ አውጣው የሆንክ ወሰክ

 5. እባካችሁ ከዳቢሎስ ጋር በመተባበር እነኝህን ንፁህ አባት አትፈታተኑዋቸው!!!

 6. አንተ የመትናገረወነና የምታደርገውን የማታውክ ሰነፍ በ ሃየማኖት ሰም የተደበከህ የምታታለል የ ፖለትካ ካድሪ ነህ ፈረንጅ እንደማያጎራ የት አየህ ክፉን የ ሰው ልጆች ተላት ሰይታን እና አጋነንት የለም ካልክ መልካሙን እግዚአብሂርንማ እንደት ታውካለህ አንተ እና መሰሎችህ ክፉ የዲያብሎስ መሳሪያ ናችሁ ቤተክህነትን በ እራስ ወዳዶች ሆዳሞች የ ፖለቲካ ካደሬዎች በ ሰላዮች የሞላችሁ እመነተ ጎዶሎ ክፉዎች ጌታን ክርስቶስን በ ሃሰት ክስ ወንጅላችሁ የሰከላችሁ አይሁዶች ዛሬም መምህር ግርማን በሃሰት ክስ ወንጅላችሁ አሳሰራችሁ ነገር ገን ይህ ለ አባታችን ስለ ክርስቶስ ቢሰደቡ ክብር ነው እኔ በምኖርበት ሃገር ሩሲያ መምህር ግርማ ቢኖሩ ኖሮ ተከብረው በኖሩ ነበር ግና ነብይ በሃገሩ አይከበርም ዛሬ የ አንተ እና መሰሎችህ አፋችሁን ትከፍታላችሁ በ መምህር ግ ርማ ስብከት እና ፈውስ አገልግሎት ድነን ተፈውሰን ህይወታችንን በሰላም እየመራን ያለን ብዙ ሚሊዮን የመንፈስ ልጆችአችው አለን እወነትን እንመሰክራለን እናንት ግን የ ሃሰት አባት የ ዲያቢሎስ ችፍሮች ናችሁ ለመምህር ግርማ እረጅም እድሜ

Comments are closed.

Azeb Mesfin
Previous Story

የባራክ ኦባማና የወይዘሮ አዜብ መስፍን ታሪካዊ ግንኙነት

girma wendimu
Next Story

መምህር ግርማ ዋስትና ተከለከሉ * የማታለል ክስ የቀረበባቸው መምህሩ “ሴራ ነው – ከሳሹን አይቼው አላውቅም” አሉ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop