ሰማያዊ ፓርቲ በወልዲያ እና በሆሳዕና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን አደረገ

April 5, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሳኩ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረጉን አስተባባሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ፓርቲው ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት በወልደያ ከተማ፣ እንዲሁም እሁድ መጋቢት 27/2007 ዓ.ም በሆሳና ከተማ ከ7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ተኩል ህዝባዊ ስብሰባዎችን በማድረግ አማራጩን ለህዝብ እንዳቀረበ የስብሰባዎቹ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ወልደያ ከተማ ላይ ለተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ዝግጅት ወቅት የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ፖሊስ ከፍተኛ ጫና እንዳደረገባቸው የገለጹት የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወረታው ዋሴ በቅስቀሳ ወቅት ፖሊሶች ‹‹ቅስቀሳ በይፋ መፈቀዱን የምናውቀው ነገር የለም›› በሚል በቅስቀሳ ላይ የተሳተፉትን አባላት በማወከብ እንቅፋት እንደፈጠሩባቸው ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የከተማውን ከንቲባ ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት ሰማያዊ ስብሰባ ያደረገበት አዳራሽ በር ድረስ በመምጣት ወደ ስብሰባው የሚገባውን ህዝብ ለማሸማቀቅ እንደሞከሩ ገልጸውልናል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን እንዳያደርግ ከገዥው ፓርቲ ካድሬዎች የተፈፀመበትን ወከባና እንቅፋት ለምርጫ ቦርድ ቢያሳውቅም የምርጫ ቦርድ ተወካዮች ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ሰማያዊ ፓርቲ ከ250 በላይ ህዝብ የተገኘበት ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳደረገ አቶ ወረታው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ መጋቢት 28/2007 በሀድያ ዞን ሆሳና ከተማ ጎፈር ሜዳ ላይ የአደባባይ ደማቅ ህዝባዊ ስብሰባ እንዳደረገ የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ተሰማ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ምንም እንኳ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ፖሊስ በቅስቀሳ ወቅት አባላትን በማሰር፣ የመኪና ቅስቀሳዎችን በማደናቀፍ እንቅፋት ለመፍጠር ቢሞክሩም የሆሳና የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ ባደረገው ጥረት ከ500 በላይ ህዝብ የተገኘበት ስኬታማና ደማቅ ህዝባዊ የአደባባይ ስብብሰባ አድርገናል›› ሲሉ አቶ ሰለሞን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ህዝባዊ ስብሰባዎቹ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ አካልና አማራጩን ለህዝብ ያስተዋወቀበት እንደሆኑ የገለጹት ኃላፊዎቹ በገዥው ፓርቲ በኩል ህገ ወጥ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነና እነዚህ ህገ ወጥ ተግባራት መቆም እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ ‹‹አስፈጻሚው ኃይል ለህገ ተገዥ አይደለም፡፡ በማናለብኝነት የመምረጥና አማራጭ የማቅረብ መብት እየተደፈጠጡ ነው›› ያሉት አቶ ወረታው ዋሴ አሁንም ሰማያዊ ፓርቲ ገዥው ፓርቲ ለህግ ተገዥ እንዲሆን የበኩሉን ጫና እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሰለሞን በበኩላቸው ‹‹አፈናውን ተቋቁመን ህዝቡ ሰማያዊ ጎን እንደቆመ ለማሳየት ችለናል፡፡ ህዝቡ በገንዘብ፣ በሞራልም ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንደሚቆም አሳይቶናል፡፡ እኛም ዜጎች ያለ መድሎ የሚኖሩበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደምንመሰርት ቃል የገባንበት ነው›› ብለዋል፡፡

hosaena
Previous Story

የዘንባባው እሑድ – የሆሳዕና በዓል

Next Story

Hiber Radio: “በሳዑዲ አረቢያው ላይ እንደተደረገው በየመን ላሉ ኢትዮጵያውያን መጮህ አለብን ተባለ.. የቻይና የባህር ሀይል አባላት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከየመን ከ200 በላይ የ10 አገር ዜጎችን ታደጉ… አቶ እንዳርጋቸው ፅጌን ለማስለቀቅ የእንግሊዝ መንግስት ዛሬም ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየ.. የግብጹ ሚድያ ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያና ሱዳን ጋር የፈረሙትን ፊርማ የግብፅን ህዝብ አይወክልም አለ… የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ልደት ፕሮፌሰር መስፍንን ጨምሮ የተለያዩ የተቃዋሚ መሪዎችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ተከበረ… እና ሌሎችም

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop