November 22, 2014
3 mins read

በጂቡቲ ታጎሪ ከተማ የኢትዮ-ጂቡቲ የሁለትዮሽ የድምበር ሰላም በሚል ሰብሰባ ይካሄዳል ተባለ

et map300

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:-

በአቶ እስማእል አሊ ሲሮ የሚመራው ቡዱን ዛሬ ጧት በጋላፊ አቆረጠው ወደ ጀቡቲ ገበተዋል።

የኢትዮጲያ መንግስት ከጀቡቲ እስከ መቀሌ እየገነባ የሚገኘው የባቡር ሃዲድ መንገድ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ከጅቡቲ መንግስት ጋር አብሮ ለመሰራት ተሰስማምተዋል።

በዚያ አከባቢ የሚገኙ የጅቡቲ መንግስት ተቀዋሚዎች በእንግለዘኛ ምህጻረ ቃል FRUD እንዲሁም የኢትዮጲያ መንግስትን የሚቃወሙ የኢትዮጲያ አፋሮች ኡጉጉሞና የአፋር ጋዲሌ የሚንቀሳቀሱበትን አከባቢዎች ላይ የሁለት አገራት ደህንነቶች አብረው ለመስራት እንደሆነ መረጀው ያሳያል።
ይሁን እንጂ ካሁን በፊት በአፋር ክልል በኤሊ ዳዓር ወረዳ በማንዳ ከተማ የጅቡቲና የኢትዮጲያ
የመከላኪያ ጀነራሎች በሰላም ዙሪያ ባደረጉት ስምምነት የአቶ እስማእል ኡመር ግሌ መንግስት የኢትዮጲያ መንግስት የፉሩድ ተጣቂዎችን እንዲዋጋ ቢጠይቁም የኢትዮጲያ መንግስት የፉሩድ አባላት ወደ ኢትዮጲያ ገብተው እሰካለተገኙ ድረስ የኢትዮጲያ መንግስት ሊዋጋው እንደማይችል ግን ወደ ኢትዮጲያ ገብተው ከተገኙ አሳልፈን እንሰጣቹሁለን በማለት ነበረ የተስማሙት።
ወያኔ በፉሩድም ሆነ በአፋር ኡጉጉሞ እንዲሁም ጋዲሌ ላይ አንድም የሃይል እርምጃ እወሰዳለሁ ቢል የሚያስከፊለውን ዋጋ ጠንቅቆ ያውቃል።
ይህ በእንደህ እያለ የጀቡቲ መንግስት በዚህ ከታጎሪ እሰከ መቀሌ የሚገነባው የባቡር መንገድ እስኪጠናቀቅ የጀቡቲ ተወላጆች ብቻ በጉልበት ስራ እንድሳተፉ ቢጠይቅም ህወሀቶች አልተስማሙም። ይህ ከ1800 ኪሎ ሚቴር በላይ የባቡር ሃዲድ መንገድ
በኢትዮጲያ የአፋር ክልል ነወሪዎች በብዙ መልክ የሚጎዳ ነው።
እንደሚታወቀው አበዛኛው የአፋር ህዝብ አርቢቶ አደር በመሆኑ በዚህ መንገድ ዳር የሚኖሩ ነወሪዎች ለእንስሶቻቸው አደጋ ሰለሚሆንባቸው ሊፈነናቀሉ ይገደዳሉ።
ይሄ ደግሞ ካሁን በፊት በሱኳር ፋብሪካ ምክንያት ተፈናቅለው በበረሃ ለሚኖሩ ነዋሪዎች በጣም አስቸጋሪ ነው።
ባለ ቤት አልባው የአፋር ክልል መሬት ህወሀቶች በፈለጉት መልክ ስጠቀሙበት ያአፋር ህዝብ ግን በራሃብና በውኃ ጥም እየተሰቃየ ይገኛል።

ያላህ ፈትህ ስጠን!!!!
ምንጭ አኩ አብን አፋር

1 Comment

  1. “ይህ ከ800 ኪ.ሜ በላይ የባቢር ሀዲድ መንገድ በኢትዮጵህያ የአፋር ክልል ነዋሪዎችን በእጅጉ የሚጎዳ ነው”። እናንተ ሰዎች በቃ ልማትን ቀጥታ መቃወም ጀመራችሁ ገና ብዙ ያሰማናል። ፀረ ልማትና ፀረ ሰላም መሆናችሁ ግልፅ ነው።

Comments are closed.

blue party 2
Previous Story

ኢህአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ታወቀ • የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል

addisdemo3
Next Story

የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የትብብሩን ደብዳቤ አልቀበልም አለ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop