የቤተክርስቲያንን መፍረስ የተቃወሙት ተደበደቡ

ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 11 በለሚ አካባቢ የምትገኘው ማሪያም ቤተከርስቲያን በህገወጥ መንገድ ተሰርታለች በሚል ፖሊሶች ለማፍረስ ሲሄዱ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
ድርጊቱን የተቃወሙ ምእመናን “ቤተክርስቲያኑዋን ማፍረስ አትችሉም” ማለት ሲጀምሩ ፖሊሶች መደብደብ የጀመሩ ሲሆን፣ ህዝቡም በአጸፋው በፖሊሶችና በወረዳው አስተዳዳሪ ላይ ድንጋይ በመወርወር የተወሰኑ ፖሊሶችን አቁስሏል። የወረዳው አስተዳዳሪም ጉዳት ደርሶባቸው አምልጠዋል።
ወደ አካበባው በፍጥነት የደረሰው የፌደራል ፖሊስ፣ በቀጥታ የሃይል እርምጃ በመውሰዱ በርካቶች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንደሚሉት ፌደራል ፖሊሶች በተደጋጋሚ ጥይቶችን ተኩሰዋል። ይሁን እንጅ በብረት ዱላ የምእመኑን እግር በመምታት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታላቅ አገር አቀፍ የማኅበረ ቅዱሳን አጋርነት መረሃግብር እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል

5 Comments

  1. wow Tigrians are out there in full force to weaken Orthodox Church which they see as their main enemy like Amhara people and Amharic language

  2. Now Wayne like big sis my think
    They working with terrorists
    Next steps my think they sale ethopian
    People. Even Alhmudei the one.
    Enve is enve Ethopin peoples don’t sleeping
    Wackup

  3. When the rules of law is not respected, that’s what is going to happen power rules, this is the system we’ve to fight together oppositions or the other side of the isle. Just because u r the supporter of the regime as long as the law is not above everyone one day u or your family will be the victim like the living example Prim Minster Tamerat, former defense minster Isaya Abreha so many people pro Wayana are in prison because they never taught the judicial system will be against them so we’ve to learn from the past unless we have created the law that treat equal everybody the power holders will do anything against anybody to achieve their goals so my fellow Ethiopians wake up fight to bring justice for everyone democracy is the absolute tools to make powerless the dictators and as the same time give power to powerless

  4. እናንት ኦርቶዶክሶች እነማናችሁ ህገ ወጥ ህንጽዓ የምትሰሩ እንደውም መንግስት ታግሱዋችዋል ሌላው ቤተ እምነት በብዙ መቶ ሺ እና በሚሊዮኖች እየከፈለ እናንተ ያለግብር በነጽመሬት እየወረራችሁ ይዛችሁ ወንጀል ስትሰሩ ነበር ኢትጵያ እኮ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል የሚኖሩባት ሃገር ናት ይላል ህገመንግስቱ…….በተግባር ግን ፕሮቴስታንቱ,ሙስሊሙ,ጆቫው …….ወዘተ ህግ አክብሮ በውድ ዋጋ የቤተ እምነት መስሪያ መሬት ሲገዛ ዳሩ ግን ኦርቶዶክስ በነጻ መሬት እየተሰጣት በዚህ ላይ ህገወጥ በመሆን መሬት ትወራለች ዘመኑ ተቀይሩዋል በድሮ በሬ ያረሰ የለም!!!
    ደሞ ፖሊሰን በድንጋይ መደብደብ?ህግ አስከባሪ ካልተከበረ ማን ሊከበር…..?…!

    • ለምን እንኳን በነፃ እንደሚሰጥ የምታመልከውን ከንቱ አማልክት ጠይቀው::ምቀኛ ምን ትሆን ትፈነዳ ኦርቶዶክስኮ ትናንትም ዛሬም ነገም ንጽሂት ቅድስት ናት::ዉይ እምዬ ማሪያም የጌታዬ እናት ባንቺኮ ነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ያወቅናት::

Comments are closed.

Share