የወያኔው ወመኔዎች መንግስት የደህንነት ቡድን በድጋሚ በአዲስ መልክ ተዋቀረ

October 5, 2014
(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የቀድሞው መዋቅር ከተቃዋሚ ሃይሎችና ለሚዲያዎች የመረጃ ክፍተት ፈጥሮላቸዋል።
– የዲያስፖራውና የተቃዋሚዎች ትግል ፍሬ ማፍራቱ የደህንነት ተቋሙን አደፍርሶታል።…
– የተጀመረው ፍሬያማ ትግል እያደገ መሄዱ መጪውን ጊዜ ለወያኔ ጨለማ አድርጎበታል።

የተቃዋሚ ሃይሎች እና የዲያስፖራው ህዝባዊ ተቃውሞ በርትቶ እና ገኖ መውጣት፣በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች ፣የካድሬዎች እንቢተኝነት፣ የውጪ ሃይሎች ጫና፣ የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ የሃገሪቱን እና የሕዝቡን አንጡረ ሃብት ስድሳ ከመቶውን ካለምንም እውቅና በዘፈቀደኝነት ለደህንነት እና ለስለላ ተግባር የመደቡት ከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መልክ እንደገና መዋቀሩን ምንጮች አስታውቀዋል።

ኢሕአዴግ ውስጥ በተነሳው የብሩህ ተስፋ ክሽፈት የመጣ በባለስልጣናቱ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መከሰቱን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት አመራሮችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። ባለፉት 23 አመታት በህዝብ እና በሃገር ላይ የተደረገው ከፍተኛ የሆነ በደል እና ዘረፋ በሕዝቡ ዘንድ ጥርስ እንዳስነከሰባቸው እና መጪው ጊዜ ይጨልምብናል ብለው ከፍተኛ ስጋት ስላደረባቸው በአራት ቡድኖች የተከፋፈለ በሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ እና በመላው ሃገሪቱ የተበተነ የድህንነት እና የስለላ ሃይል ማሰማራታቸው ታውቋል።

በከፍተኛ የሕወሃት አመራሮች የሚመራ የደህንነት ቡድን በአገሪቱ በአዲስ መዋቅር ዳግም የተዋቀረው በየአከባቢው ከመንደር እና ቀበሌ ጀምሮ እስከ ከተሞች የገጠር ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በወያኔ ላይ ደባ ይሰራሉ ይፈጸማሉ ይመከራሉ የተባሉ እያንዳንዱን የዜጎች እንቅስቃሴዎች ሪፖርቶችን በትጋት በመሰብሰብ ወደ መሃል አገር በመላክ መታፈን ያለባቸው መገደል ያለባቸው ደብዛቸው መጥፋት ያለባቸውን ሰዎች በተመለከተ ከበላይ በሚተላለፍለት ትእዛዝ መሰረት መፈጸም ዋናው ስራው ነው።

ወያኔ የሚጠራው መጪው ምርጫ ሕዝቡ በ1997 እንዳደረገው አሁንም እንዲሁ ቂሙን በካርድ ይገልጽብናል በማለት የሚሰጋው ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የሃይል እርምጃ በመጠቀም ለማክሸፍ የሚያስችለው በየትኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ሊሆን እንደሚችል ስለላውን ተያይዞታል፤በፓርቲው ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎች የካድሬዎች እንቢተኝነት የውጪ ሃይሎች ጫና የህዝብ እሮሮ እና አቤቱታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተቱት ወያኔ ማጣፊያው አጥሮት የሃገሪቱን ግማሽ በጀት የሚሆነውን ለደህንነት እና ለስለላ ተግብር በማዋል ከፍተኛ የሆነ አደጋ በሃገር ላይ አውጆ ሕዝብን እያሸበረ ይገኛል።

2 Comments

  1. ኣዬ መመኜት አይክለከል……..በቅርቡ መመኜትም ይክለከላል….

  2. “ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም” ይላል የአገሬ ሰው። እንኳንስ የ5ተኛ ክፍል የሚመራው ጨካኝ አረመኔ በሆዳሞች የወንበዴ ቡድን የሚመራው ደህንነት ይቅርና የቀድሞው የሩማንያው አምባገነን ቻዎ ቸስኮ ለዚሁ ተግባር ባሰለጠናቸው በወንድሙና በቅርብ ዘመዶቹ የሚመራው አደገኛው “ሴኩሪታቴ” በህዝብ ትግል ውልቅሉቁ ወጥቷል

Comments are closed.

Breking News
Previous Story

በአፋር ክልል የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች ከሶማሌው ዒሳ ጎሳ ጋር ተዋግተው 3 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

Next Story

በጎንደር አዘዞ አካባቢ 1250 ኮንደሚኒየም ቤቶችን የተረከቡ አባወራዎች ላለፉት 3 ዓመታት መብራት ማጣታቸውን ገለጹ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop