በቂሊንጦ ግንቦት 7 ነው ተብሎ የታሰረው ወጣት 10 ጥፍሮቹን ነቅለው ብልቱ ላይ የላስቲክ ውሃ አንጠልጥለው እንዳሰቃዩት ተጋለጠ

(ዘ-ሐበሻ) የግንቦት 7 አባል ነው ተብሎ የታሰረው አበበ ካሴ የተባለ ወጣት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሕወሓት/ኢሕአዴግ ካድሬ ወታደሮች ከፍተኛ የሆነ ግፍ እየተፈጸመበት መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያደረሱ ወገኖች አስታወቁ።

“ዛሬ ከወደ ቂሊንጦ የደረሰኝ መረጃ እጅግ የሚዘገንና እንቅልፍ የሚነሳ ነው” በሚል መረጃውን ያቀበለን ውስጥ አዋቂ አበበ ካሴ ግንቦት 7 ነው በሚል የታሰረ ሲሆን መቀጣጫ እናደርግሃለን፤ ምስጢር አውጣ እያሉ በሚዘገንን መልኩ የ10 ጣቶቹን ጥፍሮች እንደነቃቀሉት አስታውቋል። እንደ መረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ ብልቱ ላይ የታሸገ የላስቲክ ውሃ (ሃይላንድ) በማንጠልጠል ሲያሰቃዩት የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከብልቱ ፈሳሽ መውጣት መጀምሩም ተገልጿል። እንደመረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ አበበ በብልቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ሕመም ህክምና እንዲደረግለት ቢጠይቅም “ሕክምና ማግኘት አይደለም ገና እንግድልሃለን” ብለው ከልክለውታል።

አበበ በአሁኑ ወቅት የእስረኛ መለያ መታወቂያውን መቀማቱን ያጋለጠው የመረጃ ምንጫችን የሚፈጸምበት ግፍ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱን እና እየተፈጸመበት ያለው የጭካኔ ተግባርም በምን ዓይነት ቋንቋ መግለጽ እንሚቻል ከባድ እንደሆነ ገልጾልናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርኮኞችን አያያዝ ባልጠበቀ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል በሚል የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑንም አስታውቋል

7 Comments

  1. Ethopia goverment murder and Ethopia people the not lik you
    If you have humanity brain good but you are not you are dame brain

  2. በሚኒሊክ ዘመን የነበረ ትዉልድ አሁን በመሀከላችን የለም ግን ለዚህ ትዉልድ የትግሬ ወያኔዎች ሚኒሊክ አደረሰ የሚሉትን አወሩ አስወሩ የሚያነብዉም ካገኙም ታሪክን ከለሰዉ በመጽሐፍ አቀረቡ ስለሆነም ይህ ሁሉ መወራጨት ለማን ለምን ይሆን? ስንል በልባቸዉ ያለዉን እዉርነትና እርግማን በመግለጥ የበደልና የግፍ ዘግናኝ ተግባራቸዉን ዕለት ዕለት መልኩን እየለዋወጠ እያየን እየሰማን እያጣጣምን አንገኛለን እንግዲህ እዉነት ነዉ የዋህ ቃልን ያምናል ብልህ ግን አካሄድን ይመለከታል እንደሚለዉ ቃሉ! ይህዉ እ\ር ምህረትን ያድርግልን እንጂ ሥቃይ መከራዉ ለሁሉ ጦስ እንደሚሆን ነዉ !!

  3. አይገርምም የበታችነት ስሜት የለከፋቸው ሰወች ሁሌም የሚያደርጉት ነው

  4. ተባብረን ካልተነሳን ገና የእያንዳንዳችን ዓስር ጥፍሮች እንደሚነቀሉ አንጠራጤር ምንድነው ችግሩ አንድ ለመሆን በግድ ጣሊያን ኢትዮጵያን መልሶ መውረር አለበት እንዴ ? እረ እባካችሁ

  5. በሚኒሊክ ዘመን የነበረ ትዉልድ አሁን በመሀከላችን የለም ግን ለዚህ ትዉልድ የትግሬ ወያኔዎች ሚኒሊክ አደረሰ የሚሉትን አወሩ አስወሩ የሚያነብዉም ካገኙም ታሪክን ከለሰዉ በመጽሐፍ አቀረቡ ስለሆነም ይህ ሁሉ መወራጨት ለማን ለምን ይሆን? ስንል በልባቸዉ ያለዉን እዉርነትና እርግማን በመግለጥ የበደልና የግፍ ዘግናኝ ተግባራቸዉን ዕለት ዕለት መልኩን እየለዋወጠ እያየን እየሰማን እያጣጣምን አንገኛለን እንግዲህ እዉነት ነዉ የዋህ ቃልን ያምናል ብልህ ግን አካሄድን ይመለከታል እንደሚለዉ ቃሉ! ይህዉ እ\ር ምህረትን ያድርግልን እንጂ ሥቃይ መከራዉ ለሁሉ ጦስ እንደሚሆን ነዉ !!

Comments are closed.

Share