Hiber Radio: በአንዳርጋቸውላይ የተቀናበረው ፊልም በሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ አጋለጠ፤ * ድምጻችን ይሰማ የኢዱን ተቃውሞ ሰረዘ

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሐምሌ20 ቀን 2006 ፕሮግራም

ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልጥር በዓል አደረሳችሁ

<< በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የቀረበው የአገዛዙ ፊልም ያው እንደተለመደው ተቆርጦ የተቀጠለ አቶ አንዳርጋቸው ከነበሩበት ክፍል ቀጥሎ ቶርች የሚያደርጉት ሰው የጣር ድምጽ የሚሰማበት እንዳሰቡት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ጠቀሜታ የሌለው የስርዓቱን ማንነት የበለጠ የሚያጋልጥ ፊልም ነው...>>

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በአቶ አንዳርጋቸው ላይ አገዛዙ ያሰራጨው አዲሱ ፊልም አስመልክቶ ከሰጠው

<.. ኢህአፓ ተመልሶ መጠናከር አለበት ኢህአፓ ዛሬም አንድ ነው ። የሽምግልና ስራ ሳይሆን የኢህአፓ ችግር ተፈቶ የተጠናከረ ድርጅት እንዲሆን ነው ።..ዓላማችንን የተረዱ ከዚህ ከአሜሪካም ከአውሮፓም አባላት እየተቀላቀሉን አንዳንዶች እየጠዩ እየመለስንላቸው ነው...> ወ/ሮ ጸዳለ እጅጉ ኢህአፓን ከ15 ዓመታቸው ጀምሮ የተቀላቀሉና በትግሉም ሜዳ ከኢህአፓ ሰራዊት አባላት አንዷ የነበሩ <<ትንሳዔ ኢህአፓ>> ብለው ከሚንቀሳቀሱት አስተባባሪዎች አንዷ ስለ እንቅስቃሴያቸው ካቀረብንላቸው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

በዞን ላይ ላይ የቀረበው የአገዛዙ የሽብር ክስና የዓለም አቀፍ ሰባዊ ቡድኖች ተቃውሞና የ ማሪያኑ የፍርድ ቤት ውሎ(ልዩ ዘገባ)

የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበር ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህንን እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪአንን ሸለመ (የበዓሉን ጥንቅር ይዘናል)

ሌሎችም አሉ

ዜናዎቻችን

* በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተቀናበረው አዲሱ ፊልም በሳቸውና በሌሎች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ አጋለጠ

– በፊልሙ ላይ ከአቶ አንዳርጋቸው ጀርባ ሱስት ጊዜ የሰቆቃ ድምጽ ይሰማል

– ፊልሙ ተቆርጡ ለመቀጠሉ በግልጽ ያስታውቃል

በባሌ በሲዳማ ተወላጆች ላይ ለደረሰው ችግር ኦነግና የሲዳማ ነጻነት ግንባር የህወሃት አገዛዝን የከፋፍለህ ሴራ መሆኑን በጋራ መግለጫ ገለጹ

* አቶ በረከት ስምዖን ሳውዲ አረቢአ ሆስፒታል ገቡ

– ከምርጫ 97 በሁዋላ በአእምሮ ህመም ደቡብ አፍሪካ መታከማቸው መዘገቡ ይታወሳል

ድምጻችን ይሰማ የኢዱን ተቃውሞ የአገዛዙን የሽብር ድርጊት ለማክሸፍ በሚል መሰረዙን አስታወቀ

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ታደሰን ተረባርበን ለሀገሩ እናብቃው!!

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ ሳውዲ ውስጥ ራሱዋን ማጥፋቷን የአገሬው ጋዜጣ ዘገበ

ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም እንድትቀንስ ተጠየቀ

የዋጋ ግሽበቱ የሰራዊቱን አቅም እተፈታተነ መሆኑ ተገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

1 Comment

  1. “ግንቦት ፯ ለግንቦት ፳ ድራማ ክፍል ሁለት”
    >>ይህ ካለፈው የቀጠለ ድራማ መሆኑ ነው? እንዴት አንድ መንግስት ለዚያውም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ታጋይና ልመታዊ መንግስት ይቺን በመሥራት ግዜውን ያባክናል?የአንድ የታላቅ ሀገር የቲቪ ጣቢያ ክህሎቱንም በዚች ፉገራ ያስገመግማል? ካለፈው “አኬልዳማ”.. “የካድሬ ሃረካት” ከሚሉ አጫጨር ግን አስቂኝ ክስተቶች አሁንም አልተማሩም? ኦሮሞይ እያሉ በጣም የወረደና የዘቀጠ ጭራሽ በጣም አስፎጋሪ የሀሳብ መቆራረጥ አንዱን ጅምሮ አንዱን ጥሎ ሌላውን የሚቀባዥር ቆርጦ ቀጥል የልጅ ሥራ እያሳዩ IT(PHD)ካላቸው ምሁራን ጋር መጋፋት አይደብርም!?። የአንድአደርጋቸው ቱታና የውሃ ላስቲክ ብልጭ ጥፍት ስትል ቪዲዮው ሲንሸራተት ይታያል። ግን ግለሰቡ በአንድ ኢንተርቪ ሁለት ቱታ ሁለት ካኒቴራ የለበሰው መንግስትን እንክብካቤ ለማሳየት ነውን? ከቃለመጠይቁ በስተጀርባ የሚሰማው ድምፅ የሚገረፍ ሰው ስቃይ ባይሆንም በእስር ላይ ያለ የአዕምሮ በሽተኛ አንደሆነ ግልፅ ነው።አንድአድርጋቸው የሥራ ባልደረቦቹን ዘረዘረ ማለት ሚስጥር አደለም። ጫካ አልተደበቁም፣ በዐላም ዙሪያ ስብሰባ እየጠሩ፣ በመንገድ እየተሰለፉ፣ በድረ-ገፅ እየጻፉ፣ በቲቪ በሬዲዮ መግለጫ እየሰጡ፣ ኢህአዴግን በተለያዩ ሥራዎቹ ለዓለም መንግስትና ህዝባዊ ተቋማት ፊት እየሞገቱት ይታገሉ የለምን? ለመሆኑ ግንቦት ፯ በአንድአድርጋቸው ብቻ የቆመ ከሆነ በ፪ወር ግዜ ውስጥ የሚወድቅ ከሆነ ኢህአዴግ ምን አስፈራው? በቀጥታ ፓርላማ ገብቶ ግንቦት ፯ ፈርሷል ከአሸባሪነት ተሰርዧል ብሎ መግለጫ መስጠቱ አይቀልም? የሚገርመው ” የሰጠኋችሁ ላፕ ቶብ ምንም መረጃ የለውም… ፍላሹም ቢሆን ብዙ ነገር የለውም አዲስ ነው።”ጋዜጠኛው ከየት አምጥቶ ነው መረጃ ሰጠ ሚስጥር ኮድ ሰጠ የሚለው? አሁን ኢህአዴግ ከራሱ ሰዎችም ሰው አይተርፈውም ገና ይችን ተጠቅሞ ከፍተኛ ፕወዛ ያደርጋል…የበሉ የሚበሉም አይጠፉም… ምርጫ አስኪያልፍ ጥሩ ማደናገሪያ አገኘ መብራት አይጥፋ እንጂ በእየሳምንቱ የ፲ ደቂቃ አስገራሚ! አስደናቂ! ሰበር ዜና!አጋለጠ፣ዘረዘረ፣ ተረተረ፣ የሚል “ግንቦት፯ ለግንቦት ፳ ድራማ” እየቆራረጠ እየቀጣጠለ ያሳየናል… (ሰው ለሰው ድራማ አለቀ!?) ወይስ ቻይና ሊጨርሰው ተስማማ? አሁን አንድአድረጋቸው የአየር ሰዓቱን ወሰደ ።ለግንቦት ፯ በነፃ ማስታወቂያ ይሰራበታል። ኢህአዴግ ከስሕተቱ ይማራል? ወይስ ስሕተቶቹን አሻሽሎ ይጥላል? ?

Comments are closed.

Share