ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህነንት የበታች ሃላፊዎች በአቶ ኢሳያስ ጠባቂዎች መገደላቸው ተዘገበ

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው፦

ባለፈው ማክሰኞ ከምሽት ጀምሮ ቦሌ መስመር ወሎ ሰፈር ከአይቤክ ሆቴል ፊትለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በተፈጠረ የፖለቲካ አለመግባባት ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊ ጠባቂዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህንነት የበታች ሃላፊዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ታውቋል።

በአማራው ክልል ያሉ እና በህግ በተመዘገቡ ፓርቲዎች ሽፋን የህገወጥ ዲያስፖራ ፓርቲዎችን አላማ የሚያራምዱ የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ከምርጫው ቀደም ብሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ለመወያየት የተሰበሰበው የደህንነት ጓድ በስብሰባው ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ከአዲስ አበባ ከ13 አመት በፊት ተመልምለው ወደ አማራው ክልል የተላኩት በክልሉ ምስጢራዊ የሆኑ የግድያ እና የአፈና እንዲሁም የስለላ መመሪያዎችን በመቀበል ለጽጥታ ሃይሎች በማስተላለፍ ሲያስፈጽሙ እና ሲፈጽሙ የነበሩ እና በደህንነት ኮድ ስማቸው (አለልኝ እና ብቸናው) የተባሉ የደህንነት የበታች ሹሞች እዛው ስብሰባው መሃል በጸጸት እና በብሶት በቁጣ የተሞላ ጠንካራ ጥያቄዎች በማቅረባቸው በተፈጠረ አለመግባባት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል።

የሕወሓት የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች ምን ያህል በጥጋብ እና በትእቢት እንደተወጠሩ የሚያመለክተው ይህ ግድያ በስብሰባው ላይ ያሉትን የደህንነት ጓዶች ለማሸበር እና ለመጪው ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳያነሱ እና አለመግባባት እንዳይፈጥሩ ለማስደንገጥ የተደረገ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰራዊቱ ውስጥ እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአገር በሚወጡበት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ሃገር ቤት እንደማይመለሱ ታውቋል። ባለፈው አመት ለደህንነት ትምህርት ወደ እስራኤል ከተላኩ 67 ጓዶች ውስጥ 23 ወዴት እንደጠፉ የማይታወቅ መሆኑን መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን ገልጸውልናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በደቡብ ኢትዮጵያ ባስኬቶ ወረዳ የመኢአድን ቢሮዎች በካድሬዎች ተሰበሩ

4 Comments

  1. ክፉ ለክፉ እዚያው ይወለካከፉ። ጥፉ ለጥፉ እዚያው ይጠፋፉ ነውና ነገሩ የኢትዮጵያ አምላክ የሰው ልጆችን ጠላቶችና ደህንነት ተብዬዎችን ያባላቸው። ድሮስ እርኩስና ስንኩል ሃሳብና ተግባር ውጤቱስ ይኽው አይዶለም። እኔ በበኩሌ ይህ ክስተት ባመከሰቱ እንዲደገም ለአያው ስም አይጠሬ ጥሩ ነጭ የኦጋዴን ዕጣን አጨሳለሁኝ። ያፋጃችሁ የኢትዮጵያ አምላክ። ሰይጣን እኮ የተጠላው በገዛ ክፉና ርኩስ ተግባሩ ነው።

  2. ደግ ሆነ እኔም ይኸውኑ ነበር የተናገርኩት እርስ በርሳቸው ይባሉ ገናም ይባላሉ::

  3. በትክክል ይገባችዋል ሲጀመር የወያነ አገልጋዪች አልነበሩም.ገና ወያነ እሰበሱ ይባላል የኢትዮፕያ ህዝብ እምባ ይፋረዳቸዋል

  4. ofcourse Tigres have no respect for Amharas as they hate Amharas and see them their number one enemy ( according to the book IDENTITY JILT)they will use any opportunity to kill and displace Amharas and that is what they have been doing and they will continue,,,,,,

    Tigres as they are greedy and cruel they will kill millions to sustain their Tigre led Apartahid regime and their Gestapo Agents will kill even children and young girls mercilessly it was the mistake of God who let these Cruel people to be a leader of Ethiopians they are unethiopian and cruel like an animal they have no humanity if they think someone is a threat to their Aparthaid regime

Comments are closed.

Share