June 27, 2014
2 mins read

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበርኞች ግንባር ሰራዊት በወልቃይት ድል መቀዳጀቱን ገለጸ

arbegnoch

አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የይስሙላውን ምርጫ በመጪው ዓመት እንደተለመደው ግልጽና ፍትሃዊ ባልሆነ መልኩ ለማከናወን ሲል ገና ከአሁኑ ለለውጥ የተነሳሱ ዜጎችን በማሰርና በማሳደድ ብሎም ደብዛቸውን እያጠፋ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የወገን ደራሽ ጥቃቱን በጎጠኛው ቡድን ታጣቂዎች ላይ መውሰዱን ቀጥሏል።

በሰኔ 16/2006 ዓ/ም በወልቃይት አድነጣ በተሰኘ ስፍራ በስርዓቱ የሚሊሻ ታጣቂ ላይ በወሰደው ወታደራዊ እርምጃ አስራ ስምንት(18) ገድሎ ሁለት(2) ማርኳል የምርኮኞቹ ስም1ኛ- ቻለው ሲሳይ 2ኛ- ተጫነ ንጉሱ ሲሆኑ ሠራዊቱ ለሁለቱም ምርኮኞች ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለ ድርጅቱ አላማና ግብ በማስተማር ለቋቸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰኔ 18/2006 ዓ/ም ነበልባሉ የኢትዮጵያ ሕዝበ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ከወያኔው የልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር በወልቃይት አወርቂ በተባለ ቦታ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ለአራት ሰዓት ያህል ባካሄደው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሰላሳ ስድስት(36) ገድሎ አርባ ስምንት(48) በማቁሰልና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸውና ትጥቃቸው ጋር ማርኳል።

ውጊያው በተካሄደበት አከባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችና በ2007 ዓ/ም ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የምርጫ ድራማ ሳቢያ ከፍተኛ እንግልትና ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙ ወገኖች የተሰማቸውን ደስታ ከመግለጻቸውም ባሻገር የወያኔን ቡድን በጥይት አረር ለመፋለም ግንባሩን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

Source: Amharatimes

2 Comments

  1. ere gud new ers bers metelalek ende jegninet mekoteru yeman hager sew yimslachihuwal yemotew lik ende ensisa sew eyegedelu mefoker yawum yehagerun zega bemechefchef . ethiopiachin min yishalishal beyegizew yemiyademash atachim yawum wud yehonutin zegochishin eyechefechefu mefoker

Comments are closed.

Previous Story

ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ (ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ)

Next Story

የታላቁን ወር ረመዳን መግባት አስመልክቶ ከታሳሪ ጀግኖቻችን የተላለፈ አጭር የ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› መልእክት – ከድምጻችን ይሰማ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop