የፊታችን ቅዳሜ በመቐለ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይካሄዳል

June 26, 2014

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ዓረና መድረክ ቅዳሜ ሰኔ 21, 2006 ዓም በመቐለ ከተማ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ያካሂዳል። ለሰልፉ የሚሆን ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል። የመቐለ ህዝብ በሰልፉ ለመሳተፍ ተዘጋጅቷል። ቅዳሜ ጥዋት ከአምስት ሺ በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሰልፉ የጠራንበት ዋነኛ አጀንዳ መድረክ በአዲስ አበባና በክልሎች ዋና ከተሞች እያደረገው ካለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ አካል ሲሆን የሰልፉ ዋነኛ አጀንዳዎች ደግሞ የፍትህ እጦት፣ የነፃነት እጦት፣ የዉሃ ችግር፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የመሬት ጉዳይ፣ የግብር ጉዳይ፣ የማዳበርያ ጉዳይ ወዘተ ናቸው።

ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትም ሰለማዊ ሰልፍ በማድረግ ይረጋገጣል። የትግራይ ህዝብ እስካሁን ድረስ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጎ ይገኛል። በአላማጣ፣ ኲሓ፣ አይናለም፣ መቐለ (ገፊሕ ገረብ)፣ ሓውዜን፣ ዓዲግራት ወዘተ ዜጎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መክረው በፌደራል ፖሊስ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተገድለዋል። ስለዚህ ቅዳሜ ጥዋት ሰለማዊ ሰልፍ የሚጀመርበት ታሪካዊ ቀን ይሆናል። በመቐለ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የተፈቀደ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ይደረጋል ማለት ነው።

ስለዚህ የመቐለው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ከዉሃ ጥያቄ የዘለለ ነው። የዉሃ ጥያቄ አንድ መሰረታዊ ጉዳይ ሁኖ ሌሎች አስቸኳይ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ። ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እየተገደሉ ነው። በሌሎች ክልሎችም እየተገደሉብን ነው። ንፁሃን ዜጎች ያለ ፍርድ እየታሰሩ፣ በድንጋይ እየተወገሩ፣ በፖሊስ እየተደበደቡ፣ በመርማሪዎች እየተገረፉ፣ ያለ ምንም ወንጀል በሽብር እየተከሰሱ ነው። ከዚህ በላይ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ የሚጠይቅ ጉዳይ የለም።

ከሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ከመገረፍ፣ ከመታሰር፣ ከመገደል በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? በሌሎችስ ከዚህ በላይ ምን ተደረገ? ስለዚህ የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ በቂ ምክንያት አለን። የመቐለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ በሰለማዊ ሰልፍ ማክበር አለበት። የመቐለ ህዝብ እንደነ አዲስ አበባዎች፣ ባህርዳሮች፣ ደሴዎችና ሀዋሳዎች የተቃውሞ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።

የመቐለ ህዝብ ነፃነት ይፈልጋል። ስለዚህ ይሰለፋል። የቅዳሜ ሰልፍ በገዥው መደብ ካልተስተጓሆለ በቀር ኃይለኛ ሰልፍ ይደረጋል። በአደባባይ ስለሚደረግም ማንም ሰው አይቶ ይመሰክራል። የትግራይ ህዝብ የህወሓት ደጋፊ እንዳልሆነ ያስመሰክራል። ፎቶዎችና ቪድዮች እንቀርፃለን። ትመለከታላቹ።
ሰልፉ ቅዳሜ ጥዋት በ3:00 ሰዓት ከአደባባይ ዘስላሴ (ባዛር) ተነስቶ በሓውዜን አደባባይ አልፎ ሮማናት አደባባይ አቋርጦ አብርሃ ካስትል ሆቴል ከደረሰ በኋላ ወደ ናሽናል ሆቴል ታጥፎ በጤና ጣብያ በኩል ላዕለዋይ ፍርድቤት ደርሶ ሮማናት አደባባይ ላይ ይጨረሳል። የመድረክ መሪዎች ንግግር ያደርጋሉ። በ6:00 ሰዓት ይጠናቀቃል።
ህወሓት የሀዋሳውን፣ የባህርዳሩን፣ የአዲስ አበባውን ወይ የደሴውን ያህል ከፈቀደልን የቅዳሜ ሰልፍ በእርግጠኝነት የተዋጣለት ይሆናል። እስቲ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ ሰልፍ ከፈቀደ እንይ። መቐለ ሰልፍ ልትጀምር ነው። ህዝብ ዓረና መድረክ ያለውን ድጋፍ ባደባባይ የሚገልፅበት ቀን: ቅዳሜ።
ህወሓት ሰልፉ እስኪጠናንቀቅ ድረስ ፀጥታ ካስከበረ ህወሓትን በፅሑፍ ነው የምናመሰግነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ አስከብሮለታል ማለት ነውና። ሰለማዊ ሰልፍ መፍቀድ በራሱ ጥሩ ነገር ነው። ሰልፍ ለትግራይ ህዝብ ተአምር ነውና። ምክንያቱም ተፈቅዶልን አያውቅም።
እስቲ ህወሓት ትፈተን። እስቲ ህወሓት የህዝብ ድጋፍ አለኝ ብሎ የሚተማመን ከሆነ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሰልፉን ለማየት ዝግጁ ይሁን።
ለማንኛውም ቅዳሜ እንገናኝ። የዉስጥ ለውስጥ ቅስቀሳው አልቋል። ነገ ዓርብ ፎርማል ቅስቀሳ ይደረጋል። በህዝብ ያለን ድጋፍ ለማወቅ ተከታተሉን።

3 Comments

  1. The People of Mekele would demonstrate that they are not accomplice of the heinous crime committed on the people of Ethiopia by TPLF/EPRDF in their name and the people of Ethiopia would prove that the people of Mekelle in particular and Tigray in general are not accomplice of TPLF/EPRDF elites who are bending to obliterate anybody who stands against them. Most of our people have considered that the people of Tigray are supporting the crime committed by the TPLF/EPRDF authorities and its security forces in different regional state in Ethiopia. And Mekele would prove that they are not accomplice of the heinous crime committed by EPRDF/TPLF authorities and its security forces.
    Saturday will be eventful day for us!!! Long Live Arena….Long Live Mekelle. The dictatorial, divisive and ethnocentric regime couldn’t divide us because our blood is mixed and we are you and you are us.

  2. የተፃፈው መልእክት ትክክለኛና ተገቢ ነው፣ ነገር ግን ህወሃት ይንን ሰልፍ ፈቀደማለት በሬ ወለደማለትነው በኔ እምነት፣ ኣብራሃ ደስታ ይህንን ፅሁፍ በትግራይ ውስጥ ሁነህመፃፍህ በጣም ጀግና ነህ ቀጥልበት ያልከውን ነገር ላለመድገም እንዳለ ትክክል ነው።

  3. ዋው! አብርሽ ጥሩ ነው። ግን ለወያኔ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ የለባችሁም። ስለምን ሰላማዊ ሰልፍ የማደረግ ሙሉ መብት አላችሁና! ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ብሎ ከደማ ከቆሰለ ስለምን ምስጋና ያስፈልገዋል? አይመስልህም ታናሼ?! ደግሞስ ነፃነትህን እንዴት ለወያኔ ትሸልመዋለህ? ስለምንስ እስከ ዛሬ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡት ላይ ወያኔ በትእቢት ያፈሰሰው ባሩድ፤ የዘረጋው ሰንሰለት፤ የተዘጋው ቤት፤ ያፈሰሰው ደም፤ የዘረፈው የደም ጥሪት፤ የቀማው መሬት፤ ለባዕድ የሰጠው አፈርና ክብር፤ ሲበድል የነበረውን ነገር ሁሉ ታጸድቅለታለህ? – አወና! አብርሽ ምስጋና ከፃፋችሁ ለእኔ የሚሰጠኝ ምላሽ እንደዚህ ነው። ለበደሉ ዕውቅና መስጠትና አሁን ወያኔ ተሻሽለሃል ማለት እኮ ነው። አዬህ አብርሽ ወያኔ የማይድን አሲድ ነው። ከዚህ መንፈስ ተነስተህ ውስጠ ዕቃውን ስትፈትሽወ ወያኔ እስከ ቅል ቋንቁራው መወገድ ያለበት እንጂ ትንፋሹን እንዲሰበስብ ምስጋና ሊሸለመው አይገባም – በፍጹም። ሁሉም ነገር ከሉዕላዊነት በላይ ነውና! ሁሉም ነገር የሰው ልጅ በአምሳሉ ከፈጠረው የሰው ልጅ የመኖር ክብር ነው። ታውቃለህ አብርሽ አሁን እኮ በልዕልት ኢትዮጵያ „መኖር የለም“ ልድገመው ወንድምዬ „መኖር የለም“ ቁልምጥ – ልምምጥ – ለስላሳ ትግል አይደለም መፍትሄው „እንዲህ ወያኔ በቃህን ብለህ አስገደደህ ጥላቻህን ስታጎርሰው ነጻነትህን በድርጊት ትወልደዋለህ፣ በስተቀር ግን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው“ ከሁሉ በላይ ዛሬ ያለው የነፃነት ትግል በትግርይ ወገኖቻችን ላይ ወያኔ በፈጠረው መጠራቅቅ እዬዳማነ ያለውን ንጹህ የኢትዮጵዊነት የአብሮነት መንፈስ በፍጹም ሁኔታ ማዳን የሚቻለው በዚህ መልክ ከመሰረቱ መነሳት ሲቻል ብቻ ነው። አገም ጠቀም ለዕለት ኑሮም አይሆን እንኳንስ ነገን ለማሰንበት። ብዙ የቆሰሉ መንፈሶችን ለመፈወስ ተግባር! በወያኔ ላይ መንፈስን ሙሉ ለሙሉ ማሸፈት – ንክኪውን ሁሉ መጸዬፍ። ልክ አንተ አይሁዲትን ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደተጸዬፍካት ሁሉ „አጀንዳችን አይደለችም“ ነው ያልከው አይደል? ወያኔም ለትግራይ ህዝብ አጀንዳው ሊሆን አይገባም ባይ ነኝ። …. ተግባባን አባቱ። ጥሩ ምልክት ነው – ወቅቱንም ማዬት የቻለ። በርታ!

    እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Comments are closed.

31651
Previous Story

በእየሩሳሌም ከተማ ከኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ አባላት ጋር የተካሔደ ስብሰባ (Video)

Next Story

ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የተወረወረች ቀስት ማን ላይ ታርፋለች?

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop