ሰኔ 15 የሰማታት ቀን ነው!

ሰኔ 15 የሰማእታት ቀን ነው። ሰኔ 15, 1980 ዓም በሐውዜን ከ2500 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአንድ ፀሓይ የተጨፈጨፉበት ቀን ነው። ጭፍጨፋው የህወሓት እጅ እንደነበረበት ይነገራል። ይህ ማለት ቦምቡ የጣሉት ጀቶች የህወሓት ነበሩ ማለት አይደለም። ህወሓት በግዜው በሓውዜን ከተማ ጉባኤ እንደሚያደርግ ሆን ብሎ (የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት) ለደርግ የሐሰት መረጃ አስተላልፏል። ብዙዎቹ የደርግ ጀነራሎችና መርማሪዎች የህወሓት “ስርዒት” ነበሩ። የአብዛኞቹ የደርግ ባለልስጣናት ፀሓፊዎች የህወሓት ስርዒት (ሰላዮች) ነበሩ። (አግአዚ ኦፕሬሽን ፊልም ይመልከቱ)። ለህወሓት የሚሰሩ ወታደራዊ መኮነኖችና ፓይለቶች ነበሩ።

የሐውዜን ደብዳብ የታቀደ ድራማ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ደርግም ሐላፊነት ይወስዳል። ደርግ መንግስት እስከነበረ ድረስ ህዝብን ማዳን ነበረበት፤ መረጃው ማስተካከል ነበረበት። ሲጨፈጨፍ የነበረው ሰለማዊ ሰው እንጂ ታጣቂዎች እንዳልሆኑ ይታወቅ ነበር። ስለዚህ ሁለቱም ሐላፊነት ይወስዳሉ።

ህወሓት መጥፎ ተግባሩ እንዳይታወቅ በመስጋት ድራማውን የሚያውቁ ታጋዮች እንዲረሸኑ ተደርጓል። ከድር የተባለ ታጋይ “ምን ስንል ነበር? አሁን ምን እያደረግን ነው?” ብሎ በመጠየቁ ተገድሏል። ዳዊት የተባለም “በሐውዜን የተደረገው ነገር ስህተት ነበር” ብሎ በመከራከሩ ምክንያት ተረሽኗል። ከዛ ጦፍ ተልኳል ተብሏል።

አሁንም ይሄ ጉዳይ አለ። በሐውዜን ጉዳይ ጥናት ያደረገ የሐውዜን ተወላጅ የሆነ ጋዜጠኛ አፈወርቂ አርአያ የሐውዜን ጉድ በማጋለጡ ምክንያት ታስሮ ነበር፤ አሁን ደብዙ ጠፍቷል። ሚስጥር ያጋልጣል በሚል ስጋት እንዲጠፋ ተደርጓል (የት እንዳለ የምታውቁ ንገሩኝ)። ሌላ ገብረአነንያ ገብረስላሴ የተባለ የሐውዜን ተወላጅ “ሓመድ ሓውዜን፡ መን ንመን?” በሚል ርእስ ብዙ ሚስጢሮች በማጋለጡ ምክንያት በሰበብ አስባቡ በመቐለ ከተማ ዓዲሓቂ ፖሊስ ጣብያ ያለ ምንም ፍርድ ለሦስት ወራት ታስረዋል፤ አሁንም እዛው በእስር ይገኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ጋር የተደረገ ውይይት (OBN)

ህወሓት ከደሙ ንፁህ ከሆነ ስለጉዳዩ የሚናገሩ ሰዎችን ማሳሰርና እንዲጠፋ ማድረግ ለምን ፈለገ? የሐውዜን ጉዳይ አልፏል። ማስታወስ አንፈልግም፤ ይሰማናልና። ለፖለቲካ ፍጆታ መዋልም የለበትም። ግን የእስርና እንግልት ምንጭ ደግሞ መሆን የለበትም። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሰዎች መታሰር የለባቸውም።

የሆነ ሁኖ አልፏል። የኛ ያሁኑ ጉዳይ የሐውዜኑ ዓይነት ጨፍጫፍ በሰዎች ላይ እንዳይደገም መከላከል ነው። ዳግም ደም መፍሰስ የለበትም። ስለዚህ ህወሓትም ይፈፅመው ደርግ መደርጉ ስህተት ነው። ስሀተት በስህተትነቱ እናወግዘዋለን። ያሁኑ ጉዳይ ማነው የፈፀመው አይደለም። ያሁኑ ጉዳይ መፈፀም የለበትም፣ አልነበረበትም ነው።

ክብር ለሰማእታት! It is so!!!

1 Comment

  1. ውድ አብርሃ – ዶ/ር ማርክ የተባለ የለንደን ሰው ያጫወተኝን ላካፍልህ። የሃውዜን እልቂት በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ ነበር። ጉዳዪ እንዲህ ነው። ወያኔ ከወራታት ቀደም ብሎ በአንድ ስፍራ ድግስ ደግሶ ከበሮ እያስመታ እያለ ሳያስበው ጀቶች ይመጡና ብዙ ሰው ያልቃል ድግሱም ሳይበላ ይቀራል። ይህ የሆነው ጉዳዪን የሚያውቅ የወያኔ ታጋይ መቀሌ በመግባት እጁን ሰጥቶ ስፍራውን በማሳየቱ ነው። በዚህ ጥቃት የተበሳጩት የወያኔ መሪዎች አንድ ሌላ ታጋይ እጁን እንዲሰጥና የተሳሳተ መረጃ ለደርግ እንዲያቀብል ይደረጋል። ባለፈው ጥቃት ስኬት የሰከረው የደርግ አመራር ደግሞ አሁን የተገኘውንም መረጃ ሳይመረምር ሃውዜን ገብያ ቀን ፍጅቱን ያከናውናል። ወያኔም ድጋፉ እየመነመነ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ይህን እልቂት የጉልበቱ ማጠናከሪያ አድርጎ ተጠቀመበት። በሃውዜን እልቂት የወያኔ እጅ እንደነበረበት አንዳች ጥርጥር የለውም። ዶ/ር ማርክ በትግራይ በረሃዎች ከወያኔ ጋር አብሮ የሰራ በዙ ግፎችን የሰማና በአይኑ ያየ የህክምና ዶክተር ነው። ታዲያ ዛሬ የትግራይ ተወላጆች በሃውዜን ጉዳይ ጥያቄ ሲያነሱ፤ ሲመራመሩ መሰወራቸውና መታሰራቸው ወያኔ በትግራይ ህዝብ ምን ያህል እንደነገደበት አሁንም በስሙ ግፍን በሌሎች ላይ እንደሚያዘንብ ያመላክታል። የትግራይ ህዝብ በረሃም ሆነ በከተማ በወያኔ ሰንሰለት የታሰረ ህዝብ ነው። ነጻነት ለሃገራችን ይምጣ!

Comments are closed.

Share