አስቂኝ ዜና!

በናዕዴር ዓዴት (አክሱም ዙርያ) “ሰመማ” ተብሎ በሚጠራ የገጠር ከተማ የሚያስተምሩ መምህራን “የዓረና በራሪ ወረቀት ተቀብላቹ አንብባችኋል” በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ወረቀት መቀበል ይሁን ማንበብ መብታችን ነው ብለው ቢከራከሩም ያከባቢው አስተዳዳሪዎች ግን ማስፈራራትን ተያይዘውታል። የዓረና ወረቀት አንብባችኋል ተብለው ከተከሰሱ መምህራን አስራ ስምንቱ (18) “እንዳውም ዓረና ነን። ለነፃነታችን እንታገላለን!” ብለው የዓረና አባላት ለመሆን ትናንት ፎርም መሙላታቸው ያከባቢው የዓረና አስተባባሪ በስልክ ገልፆልኛል። የናዕዴር ወላጆች ልጆጃቹ ወደ ዴምህት ልካችኋል እየተባሉ ብዙ ግፍ እንደሚፈፀምባቸው ይታወቃል። አዎ! እንደነዚህ ቆራጥ መምህራንም አሉ። ዓረና ናችሁ ሲባሉ ዓረናን የሚቀበሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የትግራይ ቀዉስ፤ በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል ወይስ በትግራይና በአማራ ህዝብ መካከል?

1 Comment

  1. አንተ ደልቶሃል ወዳጄ!! እኛ እንፈናቀላለን እናንተ ለትግራይ ከህወሃት እና ከ ዓረና የትኛው ይሻላል በሚል ትወዛገባላችሁ:: እስኪ ይሁና……..!አንገት እንደደፋን የምንቀር መስሎህ ነው

Comments are closed.

Share