June 17, 2014
2 mins read

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉት ዜጎች ለክስ የሚያበቃ በደል አልደረሰባቸውም አለ

ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሰረቱት ክስ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛ ፍትሃ ብሄር ምድብ በዋለው ችሎት የታየ ሲሆን ፣ በቀረበው ክስ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና የቤንሻንጉል ክልል መንግስት መልስ ሰጥተዋል።

ከሳሾች ለበርካታ አመታት ከኖሩበት ቀየ በህገወጥ መንገድ በመፈናቀላቸው ሃብትና ንብረታቸውን ማጣታቸውን በጠበቃቸው አማካኝነት ተናግረዋል።

የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ከሳሾቹ ቤት ንብረት አለማፍራታቸውን ጠቅሶ፣ ምንም ለክስ የሚያበቃ ነገር ሳይኖራቸው ጉዳያቸው ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ያነጋገርናቸው ጠበቃው ዶ/ር ያእቆብ ሃይለማርያም የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‘ጉዳዩ የሚመለከተው የክልሉን መንግስት እንጅ የፌደራሉን አይደለም’ በማለት የሰጠው መልስ ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል። የህገመንግስቱ አንቀጽ 52 ማንኛውም የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲፈጸም የፌደራል መንግስቱን እንደሚያገባው፣ በዚህም የተነሳ የፌደራል መንግስቱ አይመለከተኝም ማለት እንደማይችል ገልጸዋል።

ዶ/ር ያእቆብ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ‘ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ያደረጉትን ለፍርድ እናቀርባለን’ በማለት ተናግረው እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን እየታየ ያለው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ነው ሲሉ አክለዋል።

Source: Ethsat

1 Comment

  1. TPLF has a grand plan of eliminating Amharas ድሮስ ወያኔ እና ትግሬወች ዋና አላማቸው አማራውን ከምድረ ግጽ ለማጥፋት ሆኖ እያለ እንዴጥት ለተገደሉ እና አላግባብ ንብረታቸው ተዘርፎ ለተፈናቀሉ አማሮች ፍትህ ይሰጣሉ ተብሎ ይገመታል?????
    በነገገራችን ላይ አማሮችን ያፈናቀሉት ባለስልጣናት ላይ እርምጃ ተወስዱአል ብለውን ነበር እኮ ቅቅቅቅ እና ባለስልጣኖቹ ሳያጠፉ ነበር የተቐጡት ማለት ነው? አይ የውያኔ ፍትህ? አማራ ከትግሬ ውያኔውች ፍትህ መጠበቅ አልነበረበትም

Comments are closed.

Previous Story

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም ….ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Next Story

ኢትዮጵያ: አሁንስ ተስፋሽ እግዚአብሔር አይደለምን? ዶ/ር ዘለዓለም እሸቴ ይመር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop