ጄኔራል ሰዓረና ጋዜጠኛ እስክንድር – ከኢየሩሳሌም አረአያ

June 15, 2014

ሰኔ 1 ቀን 1997ዓ.ም፤ በአዲስ ከተማ ት/ቤት የተጀመረው ተማሪዎችንና ንጹሃን ዜጐችን በግፍ የመግደል እርምጃ ተከትሎ አብዛኛው ባለስልጣናት ልጆቻቸውን ከየት/ቤቱ በአጃቢ ያስወጡ ነበር። ወደ ካቴድራል ት/ቤት በሁለት ኮብራ ተጭነው የተላኩ 20 ልዩ የፌዴራል ፖሊሶች የጄ/ል ሰአረና የጄ/ል ብርሃነ (ወዲ መድህን) ሴት ልጆችን አጅበው ሄዱ። ሁለቱ ሴት ልጆች በማግስቱ አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ተመቶላቸው ዓርብ ሰኔ 3 ቀን በረሩ። የብዙ ባለስልጣናት ልጆች በተመሳሳይ እንዲወጡ ተደረገ።

..29ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተርም እየተከፈለላቸው መማር ቀጠሉ። የአዜብ ልጅና የእህቷ ልጅ፣ (በነገራችን ላይ አርአያ መኮንን ይባላል፤ በ1995ዓ.ም ቦሌ ከሩዋንዳ ፊት ለፊት ጥቂት ገባ ብሎ አዜብ ለዚህ ወጣት በ7 ሚሊዮን ብር ቪላ ቤት ገዝታ በስጦታ አበርክታለች። የቪላው ኪራይ ሂሳብ በስሙ ባንክ ይገባለታል) ..የአርከበና ስብሃት ልጆች በቨርጂኒያ፣ የሽፈራው ጃርሶ ልጆች በካሊፎርኒያ፣ የፖሊስ ኮሚሽነር የነበረው ወንጀለኛውና 5ሚሊዮን ዶላር ሰርቆ የወጣው ተስፋዬ መረሳ ልጆች በኒዮዎርክ….ወዘተ በተቀማጠለ ኑሮና በውድ ክፍያ መማር ያዙ። ባለፈው አመት በነርስ የተመረቀችው የጄ/ል ሰአረ ልጅ ሐመልማል ሰዓረ የምርቃት ፕሮግራም ላይ ጄኔራሉ ተገኝተው ነበር።…ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንለፍ። እስክንድር በላባቸው ሰርተው ሃብት ካፈሩ ጥሩ ቤተሰቦች የተገኘ ልጅ ሲሆን የተማረው በሳንፎርድ ት/ቤት ነው። ከዚያም አሜሪካ መጥቶ ትምህርትና ህይወቱን ቀጠለ። “አገር አማን” ብሎ በዘመነ ኢህአዴግ አገር ቤት ገባ። ተደጋጋሚ እስርና ድብደባዎችን አሳለፈ። እነሆ “አሸባሪ” ተብሎ ከሌሎች ንፁሃን ጋር በእስር እየማቀቀ ይገኛል። እነ ጄ/ል ሰአረና መሰሎቻቸው በመቶ ሺህ በሚቆጠር ዶላር ልጆቻቸውን በአሜሪካና አውሮፓ ሲያስተምሩና ሲያንደላቅቁ፣ እንዲሁም ልጆቻቸውን ለማስመረቅ ሲገኙና ሲደሰቱ በአንፃሩ በመፃፉና ሃሳቡን በመግለፁ ብቻ እስር ቤት የተወረወረውና ናፍቆት ልጁን እንዳያሳድግ የተደረገው እስክንድር ነጋ ጭራሽ ቤተሰቡ ያወረሱትን ቤት በግፍ እንዲነጠቅ ተደረገ። በጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ ሰፈር ግን በሚሊዮን ብር የተገነባ ቪላ፣ ልጆቻቸው የሚንደላቀቁበት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር…ወዘተ አለ። ይህ ከህዝብ የተዘረፈ የአገር ሃብት ነው!! የጄ/ል ሰዓረ ባለቤት ኰ/ል ፅጌ በስማቸው በገርጂ የተገነባውና ሰባት ሚሊዮን ብር የፈጀው ቪላ ሲገኝ የሚገርመው የቅጥር ግቢው ወለል በእምነበረድ መሸፈኑ ነው። ሌላው በሙስና የታሰሩት የደህንነት ሹሞቹ ወ/ስላሴና ገ/ዋህድ..መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ቦንቦች እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና የቤት ካርታ ወዘተ መገኘቱን ገዢው ፓርቲ ይፋ አድርጓል። ዛሬ ጠያቂ ባይኖርም ቅሉ ነገር ግን ጄኔራሎቹና ባለስልጣናቱ እንደነ ወ/ስላሴ ዘርፈው ያካበቱት ለመሆኑ አያጠያይቅም። የሚገርመው መፅሐፍትና ጋዜጣ የተገኘበት የእስክንድር ቤት ሲወረስ በአንፃሩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና ሚሊዮኖች ተገኘበት ያሉትን የዘራፊዎቹን የሙስና ቤት አልነኩም።… እንደ እስክንድር ሁሉ አቶ አንዱአለም፣ አቶ በቀለ፣ ውብሸት፣ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ተወካዮች እነ አቡበከር.. በሙሉ ልጆቻቸውን እንዳያሳድጉ የተደረጉ የህሊና እስረኞች ናቸው!! እንዲሁም ጄ/ል ሰአረ በምሳሌነት ተጠቀሱ እንጂ የአብዛኛው ባለስልጣን ከዘረፋ የተገኘ ህይወት ተመሳሳይ ነው። የአንዳንዶቹ ባለስልጣናትና ልጆች የአሜሪካ ውሎና ኑሮ የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ እንዳለ ሳልጠቁም አላልፍም።…

(በፎቶው ጄ/ል ሰዓረ ሴት ልጃቸውን አቅፈው ሲያስመርቁና ሲደሰቱ- በአንፃሩ እስር ቤት ከጋዜጠኛ ሰርካለም የተወለደው ሕፃን ናፍቆት እስክንድር በጨቅላነቱ በስደት ያለ አባት እንዲያድግ ተፈርዶበት ይታያል..)

2 Comments

  1. I am very thankful for Jerusalem for writing the above article. It shows how the current Ethiopia treats two Ethiopians with two different political beliefs absolutely differently. You be the general or the ruling party politician in “high” standing, your kids attend American universities, paying 29,000 dollars for a semester. You be an Ethiopian who could not stomach the ruling party’s politics, like Eskinder, the house your parents built with their own hard labor would be taken away from you. Welcome to the new “democratic” Ethiopia. But I wonder. It is not a surprise that I do. How do those Ethiopians have got 58,000 dollars to pay for a single student in a year in a country where the majority of Ethiopians have a hard time having three meals a day? just wondering as usual.

  2. ወያኔ ማለት ሌባ ማለት ነው። ጻረ መኮነን የዝርፊያውና የግድያው አባሪ ናቸው። በሰሜን በትግራይ ዙሪያ እያሉም ዘራፊ ናቸው አሁንም በመዲና ከተማዋ ዘራፊ ናቸው። ፍትህ ያጣው ህዝባችን በሃብቱ የሚንደላቀቁበት እነዚህ አረመኔዎች ካለፈው የሃገሪቱ ታሪክ አይማሩም። መስሎአቸውን ነው እንጂ በፊትም ቢሆን ቀማኞችና ሌቦች ነበሩ። ፍጻሜአቸው ግን አላማረው። ማንም ቢሆን በሃገሪቱ ውስጥ እጅ በደም ሳይቀባ፤ ሳይሰርቅና ግፍ ሳይሰራ በሚሊዮን የሚያወጣ ቤት ሊሰራና ዘመድ አዝማድን በውጭ ማስተማር አይችልም። ጻረ መኮነንና ወያኔን ተጠግተው የሚዘርፉ ሁሉ ታሪክ ሊፋረዳቸው ጊዜአቸው ቅርብ ነው። በዕምነ በረድ የተሰራውን ቤትም ሌላ ይኖርበታ። ግፈኛ ትውልድ፡ መቼ ይሆን ያች ሃገር የሚያልፍላት?

Comments are closed.

Sheraton Addis Addis Ababa Ethiopia
Previous Story

የሸራተን ሆቴል ሰራተኞችና የማኔጅመንቱ ፍጥጫ ተባብሷል – አዲስ አድማስ ጋዜጣ

help
Next Story

ሱዳን ሃገር የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይን የሚዳሥስ አራተኛ ፁሁፍ (ካርቱም ሱዳን)

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop