June 5, 2014
2 mins read

በወላይታ አፈናው ቀጥሏል

በወላይታ ዞን ተቃዋሚዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚደረገው አፈና ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ እንደ ፓርቲው አመራሮች በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች ተንቀሳቅሰው ለመስራት አለመቻላቸውንና ከፍተኛ ጫና እንደረሰባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህልም በዛሬው እለት ቴዎድሮስ ጌታ የተባለ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ዳሞቶ ፋላሳ ወደተባለ ወረዳ ለማደራጀት በሚንቀሳቀስበት ወቅት እንደታሰረ ተገልጾአል፡፡

አመራሩ ሶዶ ከሚገኘው የፓርቲው አደረጃጀት በራሪ ወረቀት መመዝገቢያ ቅጾችን ይዞ ሲሄድ ወሎ ዋርዲራ የተባለ ቦታ ላይ ከእሱ ጋር ሲጓዙ ከነበሩ ሌሎች አምስት ጋር መታሰሩ ታውቋል፡፡ ሌሎቹ ሰዎች የፓርቲው አባላት አለመሆናቸው በመታወቁ ሲፈቱ አቶ ቴዎድሮስ በአሁኑ ወቅት ሳንቶ ከተማ ውስጥ ታስሮ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

በሌላ በኩል በወላይታ የተለያዩ ቦታዎች ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አለመቻላቸውን አመራሮቹ ገልጸዋል፡፡ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው አቶ ወጨፎ ታዳሞ ‹‹በሶዶ ከተማ ለበርካታ ጊዜ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ጥረት ብናደርግም አዳራሽ እንዳናገኝ ተከልክለኛል፡፡ ህዝብን ለማደራጀትና ፕሮግራማችን ለማስተማር አልቻልንም፡፡ በወላይታ ያለው አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡›› ብለዋል፡፡

Previous Story

በሁለት ዙር የሰለጠኑ 235 የድረ ገፅ መረጃ ማዛባት የሚችሉ ፕሮፓጋንዲስቶች በስራ ላይ መሆናቸው ታወቀ፡፡

Next Story

ደብረማርቆስ አዳማ እና ቁጫ ሰኔ አንድ ቀን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዱባቸዋል።

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop