በሊቢያ በርካታ አስከሬኖች ተገኙ

May 31, 2014

ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በርካታ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ስታምራ በሰጠመችው ጀልባ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አስከሬን መገኘቱን የሊቢያ የአደጋ መከላከ ሰራተኞችን በመጥቀስ ዓለማቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።

የሊቢያ አደጋ መከላከል ሰራተኞች በጀልባዋ ከ150 በላይ ስደተኞች ተሳፍረው እንደነበር ለ አል ጀዚራ የገለጹ ሲሆን፤ እስካሁን የተገኘው ግን የ 20 ዎቹ አስከሬን

አበዛኞቹ ተሳፋሪዎች ከአፍሪካ የመጡ እና በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን ለመሻገር የሞከሩ ስደተኞች እንደሆኑ ተመልክቷል።

እስካሁን 20 አሰከሬኖችን ከባህር ውሰጥ ያወጡት የሊቢያ አሰከሬን ፈላጊዎች፤ ቀሪዎቹን ወደ 130 የሚገመቱ ተሳፋሪዎች አስከሬን ለማውጣት እርዳታ ይደረግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

ቢቢሲ ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደዘገበው በዚህ ዓመት ከመላው ዓለም ወደ አውሮፓ የሚሻገሩ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ እና በአስደንጋጭ ደረጃ ጨምሩዋል።

ካላፈው የፈረንጆች ዓመት መግቢያ እስከ አፐሪል ድረስ ባሉት አራት ወራት ብቻ 42 ሺህ ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ መሻገራቸውን ያመለከተው ቢቢሲ፣ከነኚህ መካከል 25 ሺ 650 የሚሆኑት በሊቢያ ድንበር አድርገው ወደ ጣሊያን የገቡ መሆናቸውን ጠቀሱዋል።

በተለይ በሰሜን አፍሪካና በአረቡ ዓለም የተቀጣጠሉት አብዮቶች ለስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመር ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተጠቅሱዋል።

 

1 Comment

 1. bnu Munewor
  ሰሞንኛው የ ISIS ዘግናኝ ድርጊትን በተመለከተ ጥቂት ያቅሜን
  ልበል!
  በረጂሙ የኢስላም ታሪክ የሌሎች እምነት ተከታዮችን አስገድዶ
  ወደ ኢስላም ማስገባት አልተመዘገበም፡፡ ይሄ ሙስሊም ያልሆኑ
  ነ/ግን ሚዛናዊ የሆኑ ምሁራን ሳይቀር በጥናቶቻቸው ያሰፈሩት
  ሐቅ ነው፡፡ ሙስሊሞች እስፔንን ለ736 አመት ተቆጣጥረዋት
  ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን አስገድዶ ማስለም ቢኖር ኖሮ አንድም
  ክርስቲያን እንዳይቀር ማድረግ በቻሉ ነበር፡፡ ህንድን ከአንድ ሺህ
  አመት በላይ ሲገዟት ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን አስገድደው ሰዎችን
  ወደ ኢስላም እንዲገቡ አላደረጉምና አሁንም ድረስ ሙስሊሞች
  ቁጥራቸው ከጠቅላላው ህዝብ አንፃር ሲታይ እጅግ አነስተኛ
  ናቸው፡፡ በአለም ላይ ትልቁ የሙስሊም ህዝብ ያለባት ሀገር
  ኢንዶኔዢያ ነች፡፡ ነገር ግን አንድም የሙስሊም ወታደር እግር
  አልረገጣትም፡፡ ማሌዢያ ብዙሃኑ ህዝቧ ሙስሊም ነው፡፡ ነገር
  ግን አንድም የሙስሊም ወታደር እግር አልረገጣትም፡፡ በአረቡ
  አለም በርካታ ሚሊዮን ክርስቲያኖች ዛሬም ድረስ አሉ፡፡
  ሙስሊሞች በታሪካቸው አስገድደው ያሰልሙ እንዳልነበር ህያው
  ምስክሮች ናቸው፡፡ የፀረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ ከፍቶ የሁዶች
  ከአውሮፓ ምድር ሲፈናቀሉ በብዛት ወደ ሙስሊሙ አለም
  ሲጎርፉ ነበር፡፡ እምነታቸውን በግድ ሊቀይሯቸው ቀርቶ
  ተቀብለው ነበር ያስተናገዷቸው፡፡ ሙስሊሞች ይህን ሁሉ
  ሲያደርጉ የነበረው “በሃይማኖት ማስገደድ የለም!” የሚለውን
  ቁርኣናዊ መልእክት እየተገበሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ለገዛ
  እምነታቸው ባይተዋር በሆኑ ደም በጠማቸው ሰው-በላ
  ጭራቆች እየተፈፀመ ያለው ሰቅጣጭ ድርጊት ሳቢያ እምነታችን
  ጥላሸት እየተቀባ ነው፡፡
  እናዝናለን!!
  በግፍ ለተገደሉት አካላት እናዝናለን፡፡ እሱን አይተው
  ለተሳቀቁትና ቅስማቸው ለተሰበሩ ሁሉ እናዝናለን፡፡ እነዚህ
  ነቀርሳዎች ፈፅሞ ከአለም አቅም በላይ አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን
  ከስር ነቅሎ ለመጣል በመስራት ፋንታ ያለ ሃላፊነት ወሬ
  ማራገብን በመረጠው አለም እናዝናለን፡፡ ከከንፈር መምጠጥ
  ያለፈ ነገር ማድረግ ባለመቻላችንም እናዝናለን፡፡
  የነዚህ ነቀርሳዎች ዳፋ የሚተርፈው ከማንም በላይ
  ለሙስሊሞች ነው፡፡ አንድ ቂላቂል ፂማም ባፈነዳ ቁጥር
  በአለም ላይ ያሉ ፂማሞች ሁሉ የሰቀቀን ህይወት ያሳልፋሉ፡፡
  በበቀል እርምጃ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ የፈረንሳዩን አደጋ
  ተከትሎ አሜሪካ ላይ የተፈፀመውን እናስታውሳለን፡፡ አንዲት
  ቂላቂል ከሰላማዊ መሃል እራሷን አጥፍታ በምትፈፅመው
  አረመኔያዊ ተግባር በመላው አለም ያሉ እህቶቻችን ለፈተና
  ይጋለጣሉ፡፡ መውጫ መግቢያ ያጣሉ፡፡ የሚገርመው ደግሞ
  ብዙዎቹ ይህን ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት የሚፈፅሙት አካላት
  ከሃይማኖቱ ጋር ይሄ ነው የሚባል ትውውቅ የሌላቸው መሆኑ
  ነው፡፡ አዎ እነዚህ ሰላማዊ ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ እያጠቁ
  ያሉቱ አካላት በኢስላም ስም ከማስተጋባታቸው ባለፈ አብዛሃኞቹ
  ኢስላማዊ ነፀብራቅ እንኳን አይታይባቸውም፡፡ ፂማቸውን
  የላጩ፣ ልብሳቸውን የሚጎትቱ፣ አልፎም በሚገርም ሁኔታ
  ጆሯቸው ላይ ሎቲ ያንጠለጠሉ ሁሉ አይተናል፡፡ ገፈቱ
  የሚተርፈው ግን እነዚህ ኢስላማዊ ነፀብራቆች ለሚታዩበት
  ሙስሊም ነው፡፡ በጣም እናዝናለን!! ይሄ ሸውራራ እይታ ይበልጥ
  ችግሩን ሲያውሰበስብ በገሃድ እየተመለከትን ነው፡፡ መቼስ
  ሰላም ዜና አይሆንምና የቢሊዮኖች ሰላማዊነት አልፎም
  ድርጊቱን ማውገዝ ሳይሆን የነዚህ ነቀርሳዎች ድምፅ ነው
  ከእምነታችን ጋር ተያይዞ ጎልቶ የሚሰማው፡፡
  ከምንም በላይ ከሙስሊሙ የሚጠበቅ ሃላፊነት አለ!!
  የአስተሳሰብ ወረራን መመከት ከባድ ነገር ነው፡፡ ይሄ ጭራቃዊ
  አስተሳሰብ ከናካቴው ቦታ እንዳይኖረው የምንችለውን ሁሉ
  የማድረግ ሃላፊነት አለብን፡፡ ይሄ መርዛማ አስተሳሰብ
  ከእምነታችን ጋር እንደማይሄድ በቅድሚያ በውል ልናውቅ
  ይገባል፡፡ ከማንም በበለጠም ልናወግዘው ይገባል፡፡ ይሄ ደም-
  መጣጭ አስተሳሰብ ከሌሎች በበለጠ ኢላማ የሚያደርገው
  ሙስሊሞችን ነው፡፡ ይህን ደግሞ በተለያዩ ሀገራት በተግባር
  ሲፈፀም አይተነዋል፡፡ መስጂድ ውስጥ ሶላት ላይ ያሉ ሰጋጆችን
  እንኳን በጅምላ ከመጨፍጨፍ እንደማይመለሱ በተጨባጭ
  አረጋግጠናል፡፡ እነዚህ ነቀርሳዎች ለሐጅ በሚጓዙ ሰዎች ላይ
  ሳይቀር ሲዝቱ ታዝበናል፡፡ እነዚህ ሰው-በላዎች ጥፋታቸውን
  የሚያጋልጡ ታላላቅ ዑለማዎችን ጭንቅላታቸውን እንቆርጣለን
  እያሉ በትዊተር ሲዝቱ ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ አደጋው ከማንም
  በላይ የራሳችን አደጋ ነው፡፡
  ትላንት ጋዜጦቻችን እንደ ቢላደን ያሉ የጥፋት አውራዎችን ጀግና
  እያደረጉ ሲያቀርቡልን ነበር፡፡ ከእምነቱ ቀኖና ይልቅ ለስሜታቸው
  ያደሩ መሀይማን እይታን በማስቀደም የበርካቶችን አስተሳሰብ
  ሲበርዙ ቆይተዋል፡፡ የትላንቱ ሸውራራ ስብከት ሰለባ የሆኑ
  አካላት ከእምነቱ ታላላቅ አስተማሪዎች ይልቅ የአጥፊዎቹ
  ድምፅ ከፍ ብሎ ይሰማቸዋልና አስተሳሰባቸውን የመግራት
  ሃላፊነት አለብን፡፡ ህዝባችን የግል ኪሳቸውን ከማድለብ ባለፈ
  ብዙም የማያሳስባቸው የነገር አውታሮች ሰለባ እንዳይሆን ብዙ
  ልንሰራ የግድ ይለናል፡፡
  የዚህ ቆሻሻ አስተሳሰብ ተከታዮች በእምነታችን ውስጥ ፍፁም
  ቦታ የላቸውም፡፡ የዚህን የጥፋት አንጃ ተከታዮችን ነብዩ
  ሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የጀሀነም ውሾች” ሲሉ ነው
  የገለፁዋቸው፡፡ ህይወት እንኳን ቢያስከፍል እስከ ደም ጠብታ
  ልንታገላቸው እንደሚገባም አበክረው አሳስበዋል፡፡
  ሙታኖቻቸውንም “ከሰማይ በታች እጅግ ክፉ ግዳዮች” ሲሉ ነው
  የገለፁዋቸው፡፡ እነሱን እየታገለ ለሞተም እድለኛ እንደሆነም
  ጠቁመዋል፡፡ የፈለገ አምልኮትን ቢያበዙ፣ የፈለገ ፈሪሀ አላህ
  ቢመስሉም እምነት ከጉረሯቸው ያልወረደ ጥራዝ ነጠቆች
  እንደሆኑም ነው አስረግጠው የነገሩን፡፡
  በዘመናችን ተመሳሳይ አስተሳሰብ የያዙ አንጃዎችንም ታላላቅ
  ዑለማዎች አጥብቀው ነው የኮነኗቸው፡፡ ታላቁ ሙፍቲ
  ዐብዱልዐዚዝ ኢብኒ ባዝ (አላህ ይማራቸውና)፡ ኡሳማ ቢን
  ላደንን የጥፋት መንገዶችን ሆን ብሎ የሚከተል በምድር ላይ
  ጥፋትን ለማንገስ ከሚጥሩ ሰዎች አንዱ እንደሆነ ነው
  የገለፁት፡፡ ግና ይህን ሐቅ ምን ያክሉ ህዝባችን ነው
  የሚያውቀው፡፡ የዋህነት ይበቃናል! አሜሪካንን ያወገዘ ሁሉ ልክ
  አይደለም፡፡ ቂልነት ይበቃናል!! የእምነታችንን ቀኖና እየጣሱ
  ለእምነት መቆርቆር የሚባል ሳይንስ የለም፡፡ እንጂማ እስኪ
  የትኛው የቁርኣን አንቀፅ ነው ሰላማዊ ህዝብ መሃል ቦምብ
  ታጥቆ በመግባት ህፃን ከአዋቂ፣ ሴት ከወንድ፣ ሳይለዩ በጅምላ
  መጨረስን ጂሃድ የሚያደርገው? እስኪ የትኛው ነብያዊ
  አስተምህሮ ነው ሰላማዊ ተማሪዎችን ምንም በሌሉበት በጅምላ
  መጨፍጨፍን ቅዱስ እልቂት የሚያደርገው? እስኪ የትኛው
  ኢስላማዊ ማስረጃ ነው የሆነ ሀገር ሙስሊሞችን ስላጠቃ ብቻ
  ምንም ንክኪ የሌለውን የዚያችን ሃገር ዜጋ ገድለህ ጎትተው፣
  አስከሬኑን አቃጥለው የሚለው? ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
  ለዘመቻ የሚያሰማሯቸው ሶሐቦቻቸውን እንኳን “ሴቶችን፣
  ህፃናትን፣ ሽማግሌዎችን፣ በአምልኮት ቦታዎች የተገለሉ
  አካላትን እንዳይነኩ አላዘዙምን? ሌላው ቀርቶ ዛፎችን እንኳን
  እንዳይቆርጡ አላሳሰቡምን? ታዲያ ኢስላማዊውን ህግ እየጣሱ
  ለኢስላም መቆርቆር አለን? እነዚህ የደም ጥማት ያሰከራቸው
  ጀዝባዎች ግን የእምነቱን ህግ እየጣሱ ስለ እምነቱ
  ይደሰኩራሉ፡፡ “በእሳት የሚቀጣው የእሳት ጌታ (አላህ) ብቻ
  ነው” የሚለው የሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምህሮ
  ሳያቆማቸው ከነህይወት በእሳት ያቃጥላሉ፡፡ ግና አያፍሩም
  በእምነት ስም ጥፋታቸውን ይነዛሉ፡፡
  ይህን ፅሁፍ ለሚያነቡ በተለያየ መልኩ ሀላፊነት ላይ ላሉ ሁሉ!
  1. የነዚህ ሰው-በላዎች ድርጊት አብዛሃኛውን ሙስሊም
  እንደማያስደስት አታጡትምና ስለዚህ ልደሰኩር አልፈልግም፡፡
  ነገር ግን የህዝባችንን አስተሳሰብ ይበልጥ ለማጎልበት ግልፅ
  የውይይት መድረኮች ቢኖሩ፣ በዚያውም ላይ የእምነቱ
  አስተማሪዎች ለህዝባቸው ጥፋቱን የሚኮንኑበት አልፎም
  እውነቱን ግልፅ የሚያደርጉበት ሁኔታ ቢኖር መልካም ነው ባይ
  ነኝ፡፡
  2. ከዚህም ባለፈ ጉዳዩ ሰሞንኛ ብቻ እንዳይሆን የዚህ አይነቱን
  ጠርዘኛ አካሄድ በተመለከተ በሚደረገው የመፍተሄ ማፈላለግ
  ስራ ላይ ንቃት ያላቸው፣ እንደ አሕባሽ ያሉ ህዝብ ዘንድ የተተፉ
  ሳይሆኑ ሙስሊሙ ጆሮውን የሚሰጣቸው አስተማሪዎች ትርጉም
  ባለው መልኩ ተካፋይ ሊሆኑ ይገባል፡፡
  3. የሚዲያ ሰዎችም እንዲሁ ሀላፊነት ባለው፣ በተረጋጋና
  አሳታፊ በሆነ መልኩ እውነቱን ሊጋፈጡት የግድ ይላቸዋል፡፡
  4. ህዝባችንም አልፎ አልፎ እንደሚስተዋለው ምንም
  የማይገናኙ ነገሮችን እንደ ፂም፣ ልብስ ማሳጠር እና ኒቃብ
  መልበስ ያሉ ኢስላማዊ መገለጫዎችን ከሽብር ምልኮቶች ጋር
  በማቆራኘት ሰዎችን በሌሉበት ከማሸማቀቅ ሊርቅ ይገባል፡፡ ይሄ
  ከምንም በላይ ከሁሉም አቅጣጫ አጉል ድምዳሜ ላይ
  ያደርሳል፡፡
  5. ከዚህ ባለፈ በጦር ሜዳ ውሎ ላይ ስላሉ ክስተቶች
  የሚያትቱ የቁርኣንና የሐዲሥ ጥቅሶችን በተሳሳተ መንገድ፣
  የእምነቱ አስተማሪዎች ከሚተነትኑት በተለየ ሁኔታና ተንኳሽ
  በሆነ መልኩ የሚተነትኑ አካላት አካላሄዳቸው ለማንም,
  ስለማይበጅ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ የቻልነውን ሁሉ
  ልናደርግ ይገባናል፡፡
  6. ሙስሊም የሃይማኖት አስተማሪዎች በየአጋጣሚው እንዲህ
  አይነቱን ድርጊት አጥብቀው ሊኮንኑ እንዲሁም በእምነቱ ቦታ

  እንደሌለውም ሊያስረዱ ሃላፊነት አለባቸው እላለሁ፡፡
  ከስራ መሃል ሆኜ ስለፃፍኩት ብዙ የሀሳብ መንዛዛት
  እንደሚኖረው ይሰማኛል፡፡ አላህ ሁላችንንም እውነቱን ያሳየን፡፡
  አጥፊዎቹንም ወይ ልቦና ይስጣቸው፣ ወይ ጀርባቸውን ሰብሮ
  ይገላግለን፡፡
  ሰላም

Comments are closed.

74
Previous Story

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እሥራቶች መካሄዳቸውን የኦፌኮ መሪ ገለፁ

Next Story

Health: HPV ክትባት አብዛኛውን የአባለዘር እከክ (Genital Warts) እና አብዛኛውን የማኅጸን ነቀርሳ (Cervical Cancer) ለመከላከል ያስችላል

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop