አዲስ አበባ በስብሰባ ተጨናንቃለች (ነገረ ኢትዮጵያ)

ገዥው ፓርቲ በተለያዩ ጉዳዮች በተፈጠረበት ግፊትና ጫና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በመሰብሰብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቀሙ፡፡ በቅርቡ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ከተፈጠረው ችግር በተጨማሪ፣ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ፣ ተቃዋሚዎች የሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በመብራት፣ ውሃ፣ ቴሌኮሚኒኬሽና ዱቄት እጥረት የተማረረውን ህዝብ ለማለዘብና ከጎኑ እንዲቆም ለማድረግ በየወረዳዎቹና በየ ልማት ጣቢያዎቹ ስብሰባ እያደረገ እንደሚገኝ ምንጮቹ ጠቅሰዋል፡፡
በስብሰባዎቹም የሙስሊሙ እንቅስቃሴና ማህበረ ቅዱሳን፣ ማስተር ፕላኑን የተቃወሙት አካላት፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወቀሱና የሚወገዙ ሲሆን ህዝብ ከእነዚህ አካላት ልጆቹንና ራሱን እንዲያርቅ ማስፈራሪያ ጭምር እየተደረገበት እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ በሌላ በኩል ውሃ፣ መብራትና ቴሌኮም አገልግሎት እጥረት በተወሰኑ ኪራይ ሰብሳቢዎችና ከላይ ህዝቡ እንዲርቃቸው ከተጠቀሱት አካላት ጋር ግንኙት ባላቸው አመራሮች ችግር የሚመጡ እንደሆነ፣ እነዚህ አመራሮችም እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ችግሮችም በቅርቡ እንደሚፈቱ በመግለጽ ህዝብን በማባበል ላይ እንደተጠመዱም በስብሰባዎቹ የተሳተፉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ https://www.facebook.com/negere.ethiopia?ref=hl
ተጨማሪ ያንብቡ:  ባሶንዳ በተባለችዉ የሱዳን ጠረፍ ከተማ 77 ኢትዮጵያዉያን ተገድለዋል ተባለ

2 Comments

  1. Zehabeshoch bememaker weym besibseba wiyit sayhin ketema bemakatel sewoch b tyit endymotu new eyaberetatachihu yalachihut besew hiwet bemesewat siltan lemeyaz lemiyasbut meteememya bathonu betechale agerytua wede ers b ers tornet yematgebabebetin btikesekisu yehager fikir endalachihu lyasayen yichilal bie asbalehul.
    ETHIOPIA LEZELALEM TINUR

Comments are closed.

Share