ካዛንቺስ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት የአንድነት አመራሮችና ጋዜጠኛ ፍ/ቤት ቀርበው የ11 ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ፣አቶ ዘላለም ደበበ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የፍኖተ ነፃነት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ እንዲሁም የመኪናው ሹፌር ነፃነት ዘገየ ሜክሲኮ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዛሬ ቀርበው ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ለመኪና ቅስቀሳ አልተፈቀደም ፤ ቅስቀሳውን የደረጉት የተከለከለ ቦታ ነው ድርጊቱም ያደረጉት ሆነ ብለው ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት ነው፣ የዋስትና ቢሰጣቸው ከግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን ሁከት ያስነሳሉ በማለት የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው የ11 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ መለስ ልጅ መንግስትን በጣልቃ ገብነት ተቃወመች፤ የመለስን ፎቶ ካለ ፈቃድ መጠቀም ሊከለከል ነው
Share