ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም! (ግንቦት7)

April 5, 2014

የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።

ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።

ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።

እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነት ፓርቲ የሰኔ አንድ ሰማዕታትን በህዝባዊ ንቅናቄ ሊዘክር መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ

ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።

ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።

ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

3 Comments

  1. ዘረኝነት ማሀፀን ውስጥ ተረግዘው ጥላቻና ሰይጣናዊ መንፈስ የተጠናወታቸው የትግራይ ፋሽስቶች ዘረኝነትን እምነትና መለስ ዜናዊን ሀይማኖት አድርገው የተቀበሉት ወያኔዎች ኢንተርሃሞይነታቸውን አባብሰው ቀጥለውበታል፡፡
    አማራውን ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት ያለፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ነገር ግን አማራ ምን አድርጓቸው ይሆን ብለን ስንጠይቅ ወይም ታሪክ ስንመረምር የምናገኘው መልስ አማራ በታሪክ የትግራይ ህዝብን የበደለበት ወቅት የለም፡፡
    በተገላቢጦሽ የትግራይ ገዥ መደብ የነበረው አጼ ዮሐንስ በአማራ ላይ በርካታ ዘግናኝ ወንጆሎችን ፈጽሟል፡፡ የሚከተሉትን ወንጀሎች እንመለከት
    • አጼ ዮሐንስ የእንግሊዝን ጦር እየመራ መቅደላ ድረስ በመሄድ አጼ ቴዎድሮስን አስገድሏል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ንዋየ ቅድሳት የሆኑትን የዎርቅ መስቀል፣ የወርቅ ጽላት፣ የወርቅ ጽናጽል፣ ልዩ ልዩ የብራና መጻህፍት ወዘተ ለእንግሊዝ ጦር አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ 
    • ድርቡሾች ጎንደርን ያቃጠሉት በባንዳው ዮሀንስ እኩይ ተግባር ምክንያት ነው፡፡
    • ወሎ ላይ ደሴ አካባቢ በኮይ ከሚባል ቦታ በአንድ ቀን 30 ሽ ወሎዮችን ገድሏል፡፡ በሰራዊቱ ሴቶችን አስደፍሯል፡፡ የበርካታ ወሎየወችን ምላስ ቆርጧል፣ አፍንጫ ፎንኗል፣ እጅ ቆርጧል፡፡ በአጠቃላይ ዘግናኝ ግፍ ፈጽሟል፡፡ የሚገርመው ግን በአሁኑ ሰዓት አንድም ወሎየ ትግሬዎች ታሪካዊ ግፍ ፈጽመውብናል አለማለቱ/ቷ ነው፡፡ ለምንድን ነው ወሎዮች የትግራይ ገዥ መደብ ታሪካዊ ግፍ ፈጽመውብናል የማይሉት ብለን ብንተይቅ፡ መልሱ ታሪካዊ ቁርሾን በማብጠልጠል የዛሬ አንድነትን ማዳከም ሲለሚሆን ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡
    • በጌምድር ላይ አጼ ዮሃንስ የፈጸመው ታሪካዊ ግፍ እንደዚሁ ከልክ ያለፈ ነው፡፡ አንድም ጎንደሬ ግን ትግሬዎች ግፍ ፈጽ መውብናል ብለው አለማውራታቸው ነው፡፡ ለዚህም መልሱ ከላይ እንዳልኩት ነው፡፡
    • ጎጃም ላይ ባንዳው ዮሃንስ የፈጸመው ግፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሚባል ነው የሚገለጸው፡፡ ቀሳውስትን ቤተክርስቲያን ውስጥ አቃጥሏል፡፡ ጽላት ሳይቀር አቃጥሏል፡፡ ገበሬዎች እርሻ እያረሱ እያሉ ገሎ በሬያቸውን አርዶ ሞፈርና ቀንበራቸውን ፈልጦ ጠብ ለሰራዊቱ ያበላ መሆኑን ታሪክ ምስክር ነው፡፡ አሁንም የሚገርመውና የሚደንቀው አንድም ጎጃሜ ትግሬዎች ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው ብሎ አለማዉራቱ ነው፡፡ ይህም ምክንያቱ ጥንት ታሪካዊ በደልን ማረገብ ለዛሬ አንድነት ጠንቅ ነው በለው ስለሚያምኑ ነው፡፡

    በተመሳሳይ በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት አማራውን ያወደሙት የግራኝ ወታደሮች ብዙዎቹ ሶማሌዎች ነበሩ፡፡ አደሬዎችም፣ አፋሮችም፤ አረቦችም ነበሩ፡፡ አማራውን እነዳልነበረ አድርገውት ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድም አማራ ሶማሌዎች እንድሁም አደሬዎች ታሪካዊ በደል ፈጽመውብናል የሚል አንድም አማራ የለም፡፡ ታሪኩ ጠፍቶት ሳይሆን የጥንት በደልን ማራገብ የዛሬን አንድነት ማምከን ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡
    በተመሳሳይ በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ኦሮሞዎች እስከ ትግራይ ድረስ ሲሄድ ወርቅ እያዘነቡ አልነበረም፡፡ የአማራውን ባህል፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት፤ መሬት እያወደሙና እየወረሩ ነበ፡፡
    አሁን በምሰራቁ የወሎ ክፍል በራያ፣ በየጁ በአምባሰል ፤ በቃሉ፤ በቦረና፤ በወረኢሉ ወዘተ እነድሁም በጎጃም በይልማና ዴንሳ ወዘተ ያሉ ቦታዎች ስያሜያቸው ኦሮምኛ መሆኑን ዓለም ያውቃል፡፡ የሚገርመውና የሚያስደንቀው እንድሁም የሚያሳዝነው ወያኔ መራሽ አፓርታይድ ስርዓት የወለደው እብደት ህሊናን እንደሚያስት መረዳት የቻልኩት ኦህደድ/ወያኔ /ኢሀደግ ዓለማያን—– ሀሮማያ፣ አሰበተፈሪን—- ጭሮ፣ ናዝሬትን– አዳማ፣ ዝዋይን– ባቱ፣ ደ/ዘይትን– ቢሾፍቱ ወዘተ እያለ ስም ሲያስቀይር እንደምክንያት የሚያቀርቡት እነዚህ ቦታዎችን አማራዎች ናቸው ስም ያወጡላቸው የሚል ነው፡፡ አማራ ሰፊና አርቆ አሳቢ መሆኑን አዚህ እንረዳለን፡፡ ምክንያቱም ኮመቦልቻ፣ ቆቦ፣ ይልማና ደንሳ ወዘተ የኦሮማ ቃላትን ናቸው ይቀየሩልን አላለም ለወደፊትም ሊል አይችልም፡፡ ምክንያቱም የግራኝ ወረራም ይሁን የኦሮሞዎች መስፋፋት እንድሁም ያጼ ዮሀንስ ዘር ማጥፋት ወንጀል አዋሃደን እንጅ አላጠፋንም፡፡ የኢትዮጵያውያን የዘር፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የሃይማት ውህደት የጦርነት ውጤት ነው፡፡ ታድያ በዘር፤ በሀይማኖት፤ በቋንቋ፣ በባህል ተዋህደን እያለ ለምንድን ነው ወያኔ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ተግቶ እየሰራ ያለው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ወያኔ የጣሊያኖችን ተልኮ ሊያስፈጽም የተፈበረከ ቅኝ ገዥ ቡድን በመሆኑ ነው፡፡

  2. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)
    Please Ginbot 7, first your Andaragachew need to apologize for the service he gave to TPLF by publishing anti Amhara book that ignited hate against Amhara population and those who said they are nothing but ‘Ethiopian’.
    Andaragachew Tisge an Oromo ethnic (he confessed to us he is an Oromo by ethnic) was principal TPLF/EPRDF elected cadre to preach hate against what he and his masters call “NefTenga: Amhaa”. It was at the time when Andaragachew was preaching hate against Amhara that the notorious murder, breast amputation and ethnic cleansing act was carried against thousands and thousands of Amhara in Oromo area.

    Andaragachew is one of the TPLF/EPRDF criminal cadre official as “EPRDF cadre chief” (his own word) who will be and should be indicted for provoking ethnic cleansing propaganda when he was TPLF/EPDF official.
    He was gathering thousands (at times 40 thousand audiences in many gatherings- told us on his own word) workers, mothers, young audiences to preach TPLF policy of hate. And he wrote a book and went back gave it to his bosses as a gift to get power, a book that preach humiliation and insult of Amghara society. This fellow now is with Isyas Afewerki acting as his own personal cadre, preaching the anti Amhara lunatic Isayas Afewerki as pro humanity and pro Ethiopia who is treating Ethiopians in Five star hotels. That Five star hotel for Ethiopians that this criminal is playing funny is the “underground prison” and “digging and cleaning roads of the notorious NaKfa and Sahil mountains in Eritrea as chained as slaves” (I have seen that video- I think I spread that video to Ethiopians a log time a go). Now, Ginbot 7 is also torturing Ethiopians in Eritrea collaborating with Shaabiya.Ginbot 7 is now acting as Amhara defender? What a joke.

    Andargachew as defender of Amhara? He is one of the criminals with OLF. Check this document (scan and copy if this website can allow you- it is hard to copy and scan) First let Andaragachew apologize for his hate book than to tell us “ Ahunim MTshafun MeTsafen Ikorabetalehu” . First, he admitted reason for this ugly book to write was “the period of confusion and he too was confused by the politics of the time”. And at the same time, when TamanG Beyene asked him if any rumors or apology he felt; he said “Ahunim Yemikorabet MeTshaf Nnew”. How now then Ginbot 7 is accusing only TPLF when its own main cadre Andaragachew Tsige (Nick named Betinachew Tsige) was part of the game of the Amhara insult and humiliation when he was with his personal friend and schoolmate Meles Zenawi. Even Berhanu Negga was playing part of the Amhara hate game on Hailu Shaul. “Hailu Yemibal Amara”- Remember that speech? Look at the Ginbot 7 title. Who sow the seed of hate? Andargachew was part of the group of the group of elements who sow the seed of hate. Read his book as evidence “Ye Amara Hezb Keyet Wedyet”.

    http://www.assimba.org/Articles/geno44.pdf

    Thanks GETACHEW REDA

Comments are closed.

Share