አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ተቃውሞ ገጠማቸው (ቪዲዮ ይዘናል)

አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው። በቪድዮ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሠረት ምዕመናኑ “ጎጃም ላይ የተሰረቀው ገንዘብ ሚኒሶታ ላይም አይደገምም” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተውባቸው አንዳችም ንግግር ሳያደርጉ ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ እንዲወጡ መደረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ሲያስተምሩ “በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ካልገባችሁ ኢትዮጵያ መቀበር የለም”፣ የሚሶታውን መድሃኔዓለም ቤ/ክ “በረት” ሲሉ ገልጸውታል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰባቸው አቡነ ዘካሪያስ ከአቡነ ማርቆስ ጋር በመሆን ቤተክርሲያኑ በመንታ መንገድ ላይ ባለበት ሰዓት የመጡት ለመከፋፈል ነው በሚል ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን ይከሳሉ። የአቡነ ዘካሪያስን የአቡነ ማርቆስን የሚኒሶታ ደብረሰላም ቤ/ክ የተቃውሞ ውሎ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ፤ ከታች ደግሞ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ም ዕመናን ያቀረቡትን ወቅታዊ ጽሁፍ ይመልከቱ አቡነ ዘካሪያስ የጎጃምን ሃገረ ስብከት በሚመሩበት ወቅት ስላጎደሉት ገንዘብ በቪኦኤ ሲጠየቁ “ገንዘቡ ጎሎብኛል፤ ለምኜ እከፍላለሁ” ማለታቸውን ብዙዎች ያስታውሱታል።

አቡነ ዘካሪያስን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ እንዳገኘናቸው ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።

በእግዚአብሔር ስም አሜን። 4/5/2014

ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን
አንድነትን፣እርቅንና ሰላምን ከራሳችሁ ጀምሩ!

በኢተዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ዘመን ትልቁ ትንሽ የሆነበት ኃይማኖቱን በእለት ጥቅምና ሹመት ለውጦ ሁሉም ከትልቅ እስከትንሽ ለሆዱ ያደረበት ጊዜ የለም። የቀደሙት አባቶቻችን የቤትከርስቲያንን መብትና ሉአላዊነት ከማስከበር አልፈው ለአገራቸውም አርበኛና ሰማዕታት በመሆን
በታሪ የላቀች ሉዐላዊት ሃገርንና ርትዕት ኃይማኖትን አቆይተውልናል። ራቅ ያለውን ታሪክ ትተን የቅርቡን የጣሊያን ፋሺስት ወረራ ዘመን እንኳን ብናስታውስ ብዙ ካህናት አባቶች ከጀግኖት አርበኞች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል። ታላቁ ጻድቅና
አርበኛ ሰማእት ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ የሰሩት እጅግ አስደናቂ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድነት ፓርቲ በደሴ ያካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ክፍል 1

መንጋውን እንዲጠብቅ በወንጌል የታዘዘ እረኛ ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣልና ኅዝቧም ምድሪቷም አይገዙልህ ብለው ጠላትን በማውገዝ በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎን በደም ቀለም ጽፈውልን አልፈዋል። ዛሬስ? ንዑዳን ክቡራን የተባሉ አባቶች ለስማቸውና ለክብራቸው የሚገባ ሥራ እየሰሩ ይሆን?

በአደባባይ ቤተክርስቲያን በአላውያንና በመናፍቃን ሹማምንት ስትሰደብ፣ገዳማቶቿ ሲደፈሩና ሲቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነች ሃገርን ያቆየች ቤተክርስቲያን እንደወፍ ዘራሽ የትም ከበቀሉ ድርጅቶች ጋር ትቆጠሪያለሽ እንደ አዲስ ተመዝግበሽ ፈቃድ አውጥተሽ ብቻ ነው
መንቀሳቀስ የምትችይው ስትባል፣ ቤተክርስቲያን የነፍጠኛ ዋሻ ናት እያሉ በገሃድ አላውያኑ ሲሳደቡ፣ መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋል እየተባለ ሲፎከር የዛሬዎቹ አባቶች ጳጳሳት ምን እየሰሩ ነበር? ይሆን? እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለት ለምእመናን ብቻ የተጻፈ የወንጌል ቃል ነው እንዴ?

ሰሞኑን በዚህ በሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በጥቂት አማጽያን ግለሰቦች የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማደፍረስ ተጠንሶ እየተካሔደ ባለው ስርዓት አልበኝነት አንዳንድ ከኢትዮጵያ የመጡና እዚሁ የከረሙ ‘ጳጳሳት’ ቢመከሩና ቢዘከሩ እምቢ ብለው በእሳት ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ መጥተዋል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ለ3 አመታት ያህል ሲለፋበትና ከፍተኛ ውጣ ውረድ ሲደረግበትቆይቶ ወደ ፍጻሜ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲይያን የሰላምና የእርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ካለው ኃይል ጋር በመሆን ካፈረሱ በኋላ አሁን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ፈላጊ መስለው ምእመናንን ለመከፋፈልና የቤተክርስቲያንን ችግር ከድጡ ወደማጡ ለማውረድ የሾማቸውን ኃይል ተልዕኮ ለመፈጸም እየዳከሩ እገኛሉ።

በቤተክርስቲያን አባቶች ዙሪያ ያለው ልዩነት በግልጽ በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የችግሩን መንስዔ በመሸፋፈን ምእመናን እውቀት አንሷቸው የቤተክርስቲያን ስርአት የተበላሸ ይመስል የራሳቸውን ጥፋትና ችግር የችግሩ መንስ ኤ የሆነውን ኃይል
በሚቃወሙ ምእመናን ላይ በመላከክ ለማጭበርበር ሲሞክሩ ይታያሉ። ወያኔ ያበላሸውን ቀኖና ቤተክርስቲያን ወደጎን በመተው፤ ለሥልጣንና ለጥቅም አድረው ዋናውን ችግር ለመፍታት ከመንበርከክ ይልቅ እናንተም እንደእኛ ለሆዳችሁ እደሩ፣ ባንዳ ሁኑ እያሉ የማይገባ ነገር ሲናግሩና ሲሰሩ ማየት እጅጉን ያሳዝናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: ከሶፖት ሻምፒዮና ከአትሌቶቻችን ምን እንጠብቅ?

በመሰረቱ አባቶች እንደ አባቶች ሊከበሩና ሊታዩ የሚችሉት እንደ አባት ሆነው የሃገርና የቤተክርስቲያን ጠላት ከሆነው ኃይል ራሳቸውን ሲያገሉ አልያም ያልፍርሃት ክፉ ስራውን ሲቃወሙ ነው። ቄሱም ዝም መጽሐፉ ዝም ከሆነ ግን ቄሱም ቄስ አይደለም መጽሐፉም መጽሐፍ አየደለም!!!

በፖለቲካኖች ታቅዶ ቤተክርስቲያናችንን ለመንጠቅ እየተካሔደ ያለውን ታላቅ ሴራ ለማክሸፍ እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ላይሁላችሁም በመገኘት ምንደኞችን እንድናሳፍር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

8 Comments

 1. I know Abune Zekarias, he is not corrupted person; He his the truth monk, I think somebody took that money without his knowledge. Based on my knowledege about Abune Zekarias, I cannot believe he did that. Please, try to understand about a person before allegation.

 2. It is really sad that church fathers are corrupt, and they wear skin of ship and want to stand among the sheep while they are wolves. Let God give them their judgement.
  By the way it is really upsetting and so disgusting that every riff-raff who has a piece of electronics: give it a name: pokes up his pone or ipad and makes pictures than attending the church service. Everyone is taking pictures, and who is devotedly attending the church services. Is everyone coming to church to take a picture of deacons and priests praising God. We know that people have evil purposes too. I strongly believe that this has to be stopped except few people who are authorized to. it is also illegal in the US to take someone’s picture without their concent. Orthodox christians, stop this pestering, ungodly, filthy thing. Beten yengd bet aderegachihut yemibalew zemen eko yih new……!!!!

 3. እነዚህ ገለልተኛ እና በሃገር ቤት በወያኔ የተሾሙ የሲኖዶስ እግዚሃብሄርን የማይፈሩ መሪዎችን የሚከተሉ በውጭ ያሉ አማኞች ነን የሚሉ ሰዎች በባህር ላይ የተንሳፈፉ እና ወዴት እንደሚጓዙ አብዛኞቹ የሚያውቁ ከፊሎቹ እያወቁ ማወቅ የማይፈልጉ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምእመናን በገዛ ሀብታቸው የታሰሩ ማለትም መዋዕለ-ንዋይ በወያኔ አገዛዝ ሃገር ውስጥ ያፈሰሱ እንደ ቤት ንግድ የመሳሰሉ በግልጽ የምናውቀው የእምነትና የሞራል ግዴታቸውን ያሰረባቸው ሲሆኑ ጥቂቶች ደግሞ የወያኔ አጥፊ ተቀጣሪ ሰላዮች እና እምነት የሌላቸው ናቸው። ዘካሪያስም ሆኑ ሌላው እጃቸውን ውጪት ውስጥ የነከሩ ሽማግሌዎች በህጋዊ መንገድ የተመረጡትን ህጋዊ ሲኖዶስ አባት መከተል ሲገባቸው እምነታቸውን ያሳደፉ ማእረጋቸውንም ዝቅ ያደረጉ መሆናቸውን የቀድሞ ጠቅላላ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይኔ የሰጠውን የእምነት ምስክርነት ብቻውን በቂ ነበር። እባካችሁ ወደ ሃይማኖታችሁ ተመለሱ ይምረን ዘንድ አብረን እንጸልይ።
  እሽቴ

 4. ለመሆኑ አባ ዘካሪያስ በረት ነው ያሉት ቤተክርስቲያን ምን ሊያደርጉ መጡ? ማንም ደብተራ ያመጣው ታቦት ያልተባረክ ታቦት ያሉት ታቦት ፊት ምን ሊያደርጉ ቆሙ? አባ ማርቆሥ ያሳማ ማጎሪያ ያድርጉት ያህያ ጉርኖ ያድርጉት እያሉ ሲሰድቡት በዋሉትን ቤተክርስቲያን ምን ሊሰሩ መጡ? እውነት ካላቸው እውነት ‘አባቶች ከሆኑ ያገር ሽማግሌዎች ሊያነጋግሯቸው ሲፈልጓቸው ለምን ተደበቁ? እንደዚህ ቤተክርስቲያን እንዲበጠበጥ ማድረግስ ከአባቶች ይጠበቃል? በዚህ አይነት አካሔድስ የቤተክርስቲያን ችግር ይፈታል? ወይስ የወያኔን አላማ ህዝብን የመከፋፈል ተልእኮ እየፈጸሙ ነው? አይ ዘመን? ትልቁ የቀለለበት ደረጃውን ያላወቀብት ከማንም ኩታራ ጋር ሆኖ ቤተክርስቲያንን እያመሰ ያለበት ዘመን!

 5. Abat alachu, Abat ema yelem. Enjhi ortodox haymanoten yarekesu wenjelejoche Ye weyane bucheloche kirstos meatun yaweredebachw.

  Ahum ahum yetem, bota ortodox teketayoche mejemria betekirstiyan siyakomo ye west denbachewen mejemeria kalseru ye weyane mechawecha nacew.

 6. I know aba zekarias for years, he is not politician he is a servant of God.please Ignore those derg soldiers , medhanealem is not a political hall it is a church.if you really fight one more time with eprdf and need financial assistance let us know.zeraf zeraf mpls Strafanzeige !!!!

 7. I know aba zekarias for years, he is not politician he is a servant of God.please Ignore those derg soldiers , medhanealem is not a political hall it is a church.if you really fight one more time with eprdf and need financial assistance let us know.zeraf zeraf ayawatachihum

 8. Houston,
  Who are you telling about Zekarias? Banda always Banda! Wie Are Living in Free Country. Forget about your Strafanzeige .eprdf(Weyane) followers are Wirtschaft Kriminal. Weit, One Day You will be stand on a Court!!! One by One!

Comments are closed.

Share