የአዲስ አበባ መስተዳደር አንድነት ፓርቲ የጠራውን የእሪታውን ቀን ሰልፍ አቅጣጫ ከቀየራችሁ እፈቅዳለሁ አለ

ከዳዊት ሰለሞን

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ ለመስጠት ህጋዊ መስመሩን ለመከተል ተስኖት የቆየው የአዲስ አበባ መስተዳድር ዛሬ ማለዳ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ መጋቢት 28 በሌሎች መርሐ ግብሮች የተያዘ በመሆኑ ተለዋጭ ቀንና ቦታ እንድታቀርቡ ይሁን ብሏል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ለተጻፈላቸው ደብዳቤ ምላሽ ለመስጠት በአሁኑ ሰዓት በውይይት ላይ ይገኛሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዋሽንግተን ዲሲው የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በላቲን ቲቪ ተዘገበ (Video)

1 Comment

  1. 1. ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡-
    ሀ. በኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ቦታና የመኖሪያ ቦታ፣
    ***ከቀበና አሰከ አራት ኪሎ ምንም ኤምባሲ የለም ግን አምባሲ ዓይነት ኑሮ የሚኖሩ ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ምንአልባት!
    ለ. በቤተክርስቲያን፣ በመስጊድና በመሳሰሉት የጸሎት ቤቶች እንዲሁም በሆስፒታልና በመካነ መቃብር ዙሪያ
    ****ከቀበና ወንዝ እስከ “ቤተ ኅብረት አማራር ቢሮ” ድረስ ቤተክርስቲያን መስጊድ ሆስፒታል የለም ምንአልባት ሥላሴ የተቀበረውን ራዕይ እንዳይናወጥ ይሆን?
    ሐ. በገበያ ቀን ሰላማዊ ሰልፎችን ወይንም የሕዝብ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ አስቸጋሪ በሚሆኑ የገበያ ቦታዎች
    ***በቀበናና አራት ኪሎ መካከል ገበያ የለም ከቀበና ጀርባ ሾላ ገበያ ከአራት ኪሎ ወደፊት መርካቶ አለ ግን ልማታዊ የነጋዴዎችን መኖሪያ ቤት እንዳይረብሹ ማለት ይሆን? አራት ኪሎ ቅዳሜ ገበያ…ሀሙስ ገበያ ተባለ እንዴ?
    2. ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በጦር ኃይሎች በጥበቃና የሕዝብ ሰላምና ደህንነት በሚቆጣጠሩ የመንግስት የሥራ ክፍሎች አካባቢ 500 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡፡
    ***እንግዲህ ለታጋይ ባለሥልጣናት(ሕዝቦች) ቀብር… ዕርቀት… ክልል… ቀንና…ሰዓት… ሳይወሰንለት ሀዘኑ መራርና እረጅም እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በባርኔጣ፣ በካኒቴራ፣ በሻርብ፣ ተጠፍሮ፣ ሲረገድ… ደረት ሲደቃ… ንፍሮ ሲወቃ… ለመጨፈር ለምርጫና ለለቅሶ ድምፁና ቁጥሩ የሚፈለግ ብሔር ብሄረሰብ…
    የእሪታው ቀን….. የእልልታ ይሁን!******************
    ——————–_____________________——————–
    …”ትራፊክ ፍሰት፣የተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ትላልቅ የመንግሰት ተቋማት የሚገኙባቸው በመሆኑና በተመሳሳይ ቀን ሌሎች የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስለአለ እውቅና አልተሰጠውም! ስለዚህ ሌላ ተመራጭ መስመርና ቦታ በመጥቀስ የምታካሂዱበትን ሌላ ቀን ጭምር እንድታሳውቁን እንገልፃለን።” ****(አበጀሽ አማርኛ! )ይህ ደብዳቤ ከፍተኛ የሰዋሰው ስሕተት አለው። ብሄራዊ እግር ኳስ ብቻ ብሔርተኛ ታማኝ ካድሬና ባለሀብት ሳይሆን የሚያግባባን ብሔራዊ ዓላማና ቋንቋ ግድ ይላል!*************

    ***መንግስት የተቃዋሚ ክልልና ድብቅ ሥፍራ ብሎ ያወጀው ጃንሜዳ ይመስለላል እንግዲህ በአንድ የፖለቲካ ጥላ ሥር ያልታቀፉ ጥንት ያልነበሩ በእኛ ዲሞክራሲ ያገኙ በእኛና ለእኛ ብቻ የሚኖሩ ያለእኛ የሚጠፉ አልቅሰው ለምነው ይፈቀድላቸዋል!።

    ***ሕዝቡ ሌት ወጥቶ መጓጓዣ አያገኝ…የሰልፍ እለት የትኛው መኪናና ሕዝብ ነው የሚፈሰው?ይህ ሰልፍ አቅጣጫውን ቢቀይር (ቢያዞር..ኮከበ ፅብሐ ት/ቤት…የራሺያ ፣የኬንያ፣የቤልጂግ፣ እንግሊዝ፣ ሁጋንዳ… ኤምባሲዎችን..አልፎ ጭራሽ ትዝብት ውስጥ አይጥልምን!? ደግሞስ ከራሱ ኢህአዴግ በበለጠ በሀገሪቱ አሉ ኤምባሲዎች ሰላማዊ ሰልፉን ኣላማና ሀገሪቱን የተለጠጠ ኢኮኖሚ ድቅት አይረዱምን!? ሰውዬው ግመል ሰርቆ እሱ አጎነበሰ አሉ…ልክ እንደ ኢህአዴግ መሆኑ ነው።…”ሌሎች የህዳሴ ግድብ ፕሮግራም ስለአለ” ግድቡ ቤንሻጉል መሆኑ ቀረ!? ቀበና ወንዝ ላይ ሆነ እንዴ!? ወይንስ አባይ መገደቡን ለቀበና ወንዝ ሊያረዱ ቅዳሜ ጠዋት ሽማግሌ ይላካል!? አባይማ ዓለም አውቆታል ፴ ከመቶ ተሰርቷል ግብፅም ቦንድ ልግዛ፣የወደፊት የግድቡን ውጤት ተጠቃሚነቴን ማረጋጋጫ የምስክር ወረቀት ይሰጠኝ ሟች ተጠቅላይ ሚኒስትር በገቡልን ራዕይ ‘ሰጥቶ መቀበል’ መርህና ራዕያቸውን እናስፈፅም!” ሲሉ ድሮ በሚስጠር የተቆሉበትን ዛሬ በገሃድ አውጥተው ተናግረዋል።
    **አሁን የህግ፣ የምህድስናና የውጭ ግንኑነት ዲፕሎማት ባለሙያዎች ከሁሉም ጎራ የሚያስፈልገን የሰላምና አንድነት ማናከር የህዝብ ቅሬታን በቅንነት ተቀብሎ፣ ንቀትን፣ ጥላቻና ዘረኝነትን አስወግዶ…ጭፈራን ቀነስ ብልሃትና ሀገራዊ ምክርን ማጎልበት፣ ክልላዊ ጽንፈኝነትን ማጥፋት የግድ ይላል። ባይፈፀምም ማዳማጥ ብልሃት ነው። ሕዝብ ይናገር! ይሰብሰብ! ይደመጥ!በለው!!!

Comments are closed.

Share