የሮብአም ጥፋት በአብይ አህመድ አይደገም ታላቆች ገስጹ

በአለም ታሪክ ቀደምት ከሆኑትና የሰው ዘር መነሻዋ የቀድሞው አለምአቀፍ ማህበር ሊግኦፍ ኔሽን የቀጣዩ የተባበሩት መንግስታት መስራቾች በመህን በሰላም ማስከበር ዘመቻ በኮንጎ በኮርያ በሶማሌና በሩዋንዳ ንቁ ተሳታፊ ቅኝ ተገዥነትን በጥበበኛው እጼ ምኒልክ አመራር ያላስተናገደች ሃገሬ ኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል::
ባለፉ ጊዜያት በምክክር ሊፈቱ የሚገባቸው የባድመ በቅርቡም የትግራይ  ጦርነቶች ጠባሳ ሳይሽር በዚህ ወቅት የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው ኢመደበኛ ያልሆነ ታጣቂን ትጥቅ ለማስፈታት በሚል የሚካሄደው ወረራ አመራር ሰጭ ዶክተር አብይ አህመድ አካሄድ የመጽሃፍ ቅዱሱ ሮብአም ቀጥታ ግልባጭ መሆኑን በጎ ህሊና ያለው የቅዱሳን መጽሃፍት/ኪታብ ተንታኝ ሁሉ ይረዳዋል::
ይህን በግልጽ የሚታይ ግድፈት እንደቀደሙት የኢትዮጵያ የእምነት ቆራጥ አባቶች የገሰጹትን አቡነ አብርሃምና ባልደረቦቻቸውን እያመሰገንኩ ሌሎቹም የእምነትና የማህበረሰብ መሪዎችና ታላቆች ድምጻቸውን ያሰሙ ዘንድ በትህትና ጥሪዬን አቀርባለሁ::
በሃገራዊ እርቅና ሰላም ጉባኤ በሽግግሩ  ወቅት ንቁ ተሳታፊ ለነበረችው የራሴው ወንጌላዊት የቀድሞ መሪና የወቅቱ በውጭ እማካሪ ለሆኑት ይህን ጥሪ ሳቀርብ በግዮኑ ሃገራዊ እርቅ ወንጌላዊት ትሳተፍ ዘንድ ሃሳቡን ያቀረቡ ዛሬ በህይወት የሌሉት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት እቶ መስፍን ልሳኑ እንደነበሩ የነገሩኝን ለወቅቱ መሪዎችና ለህዝባችን መልካም ምሳሌነታቸውን ማሳወቅ እፈልጋለሁ::
በኦነግ ትግል የቆዩትና በዚህ መሰል ሃገራዊ እርቅ የሚተጉት የአባጅፋር ልጅና ባልደረቦቻቸው ይህን በጎ ስራ ይቀጥሉ ዘንድ ማሳሰቢያዬ ይድረስልኝ ሁላችንም ፈጣሪን በመማጸን

ኢትዮጵያን እናድን::

ቻፕሊያን ኤዲ/አደፍርስ ሃብቴ መካሻ
የማህበረሰብ ክሚኒቲ መሪና የግጭት እፈታት አማካሪ
(2ኛ ዜና መዋዕል 10 8) እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ነገር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ተካበ ዘውዴ የእናንተን እርዳታ ይፈልጋል

3 Comments

  1. I sincerely believe that being great is not just a matter of being an age old or an educated or an articulated person! It is rather the combination of all the above and all -round patriotic personality !

  2. አባ ቢያ አባ ጆብር ማለትህ ነው? እውነትም ለኢትዮጵያ ቅን አሳቢ ነህ። ከከከከ የጩሉሌው አበዛዙ አይጣል ነው አቀራረቡም ልዩ ነው።

  3. ከተገቢው አክብሮት ጋር፦ ባለጌና ጨካኝ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት ገዥ ቡድን ለአምሥት ዓመታት እና አሁንም በባሰ ሁኔታ የመከራና የውርደት ቀንበር ተሻካሚ ያደረገውና እያደረገው ያለው ህዝብ “ትእግሥትም ልክ አለውና ከእንግዴህ በቃ!” ብሎ በመነሳቱ በመስቀል በዓል ላይም ይህንኑ የአትግደሉንና የአታሰቃዩን ብሶቱን ሊያስተጋባ ይችላል በሚል ያዘጋጀውን የወዮላችሁ አዋጅ በሃይማኖት መሪዎች በኩል እንዲተላለፍ ማድረጉና የሃይማኖትመሪዎችም ይህንኑ የቤት ሥራቸውን ከራሱ ከመንግሥትተ ብየው በተሻለ አቀራረብና አንደበት መወጣታቸውን ከምር ከመረዳትና ከአርበኝነት መንፈስ አንፃር ለሚታዘብ ሰው እጅግ ምስቅልቅል ስሜት ሊሰማው እንደሚችል ለመረዳት የሚቻል አይመስለኝም! እያልኩት ያለሁት የሃይማኖት መሪዎቹ ለምን በዓሉ በሰላም ይከበር ዘንድ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጡ ሳይሆን የእኩያን ገዥ ቡድኑን በሚያስንቅ አቀራረብና አገላለፅ (የወዮላችሁ የቋንቋ ቅላፄ) የገለፁበት ሁኔታ ቢያንስ ምነው ምን ነካንና ነው ይህንን ያህል እያደር በሁለመናችን እየኮሰመን በመሄድ ላይ የምንገኘው??? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው ለማለት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share