ይድረስ ለእነርሱና ለእኛ !!!

August 12, 2023

T.G

ሁል ጊዜም እንደማደርገው የማህበራዊ ሚዲያዎችን ስቃኝ “የኮሜዲኑ” (ዶንኪ ቲዩብ) የባህር ማዶ ገዳም መሬት ግዥና ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ዘመቻ እንደቀጠለ ተመለከትኩ።

መከረኛው የአገሬ ህዝብ ከሚገኝበት እጅግ መሪር የሆነ ሁለንተናዊ ሰቆቃ አንፃር እንዲህ አይነቱን ቅጣ ያጣ ዘመቻ ዝም ብሎ ማለፍ በምድራዊውም ሆነ በሰማያዊው ዓለም ፈፅሞ ትክክል አይደለምና የሚከተለውን አጭር፣ ግልፅና ቀጠተኛ ሂሳዊ አስተያየት ለመሰንዘር ወደድኩ።

እውነተኛውን ፈጣሪ ጨምረን ቅጣ ያጣው ፍላጎታችን ተባባሪ ባናደርገው ምን አለበት?

የአገሬ ህዝብ ባለጌ፣ ፈሪና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች የጫኑበትን መከራና ውርደት ማሸነፍ ያልተሳካለት ከሰው ሁሉ የተለየ ኅጢአተኛ በመሆኑና ፈጣሪም ሊቀጣው ስለወደደ ሳይሆን በዋናነት የገዛ ራሳችን ቅጥ ያጣ ውድቀትና ከውድቀትም ያለመማር ደዌ  ውጤት ነው!

ይህ አይነት አቅጣጫውንና የቅድሚያ ትኩረቱን የሳተ የገዳማዊነት ዘመቻም የዚሁ ውድቀት አካል ነው!

ይህንን ግልፅና ቀጥተኛ ሂሳዊ አስተያየቴን እንደ መርገምት ወይም መዓትን እንደ መጥራት በመቁጠር የውግዘትና የዕርግማን ናዳ የሚያወርዱ ወገኖች ቁጥር ቀላል እንደማይሆን በሚገባ እረዳለሁ።

ከዚህ አይነት እውነተኛው አምላክን ጨምረን የግልብና የትኩረት አቅጣጫውን የሳተ ዘመቻችን ተባባሪ ከማድረግ አስቀያሚ አስተሳሰብና አካሄድ ሰብሮ በመውጣት ወደ ትክክለኛው ለምንነትና እንዴትነት መምጣት ካለብን መነጋገር ያለብን በዚህ ልክ ነውና ርግማኑና ውግዙቱ አያስጨንቀኝም!

“ኮሜዲያኑ”- (ዶንኪ ትዩብ)  የባህር ማዶ የገዳም ቦታ ግዥና ግንባታ ዘመቻ አሁንም በዚህ እጅግ አስጨናቂና አስፈሪ በሆነ የወገን መከራና ሰቆቃ ወቅት የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ሰጠቶ መቀጠሉን ለተመለከተና ለሚመለከት ባለ ቅንና ሚዛናዊ ህሊና የአገሬ ሰው ባያስገርውም በእጅጉ ሳያዝነው (ህሊናውን ሳያስጨንቀው) የሚቀር አይመስለኝም። አዎ! እውነተኛውን ፈጣሪም ያሳዝናል እንጅ ፈፅሞ ደስ አያሰኘውም!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለአቶ ልደቱ አያሌው አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

አዎ! እውነተኛው ፈጣሪ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠውንና በአምሳሉ የሠራውን የንፁሃን ህይወት ለመታደግ የምንችለውን ሁሉ ከማድረግ ይልቅ በእንዲህ አይነት የባህር ማዶ ገዳም ምሥረታ ዘመቻ የመጠመዳችን ጉዳይ የጤንነት አይደለምና አደብ እየገዛን እንራመድ!

አዎ! በመከራ ውስጥ ከሚገኝ ህዝብ ጉሮሮ እየተሻሙ ገዳም የመገንባትን ዘመቻ (ያውም በባህር ማዶ) የትኛው እውነተኛ አምላክ ባርኮ እንደሚቀበለው እንኳንስ ለማመን ለማሰብም የሚከብድ ነው!

በዚህ ዘመቻ የተጠመዱትን ወገኖችና የሃይማኖት መሪዎች “እባካችሁ እንዲህ አይነቱ የቅድሚያ አቅጣጫውንና ትኩረቱን የሳተ ዘመቻ የሚቀበል እውነተኛ አምላክ የለምና አደብ ግዙ” የሚል  የአገር ሽማግሌና የሃይማኖት መሪና አስተማሪ ለምንና እንዴት አጣን??? ከባድ ግን ልንጋፈጠው የሚገባን ጥያቄ ነው!

በባለጌና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መግለፅ የሚያስቸግር የጭፍጨፋና የመከራ ናዳ እየወረደበት ስለሚገኘው የአገሬ መከረኛ ህዝብ ሲሆን ገዥዎችን ከመገሰፅ ካልሆንም ቢያንስ በለሆሳስ የፈጣሪን ድጋፍ ከልብ ከመጠየቅ ይልቅ አሁንም በባህር ማዶ የገዳም ሥራ  ዘመቻ ላይ መጠመድ እንኳንስ የእውነተኛው ፈጣሪ እውነተኛ ሰወኛ ሽታ (ጠረን) ፈፅሞ የለውም !!!

ዎ! ፈጣሪ በአምሳሉ የሠራው የንፁሃን ህይወት በጨካኝ ገዥዎች እየወደመ (እየተደረመሰ) ስለ ገዳም ግንባታ (በተለይም በተመቻቸ የባህር ምድር ስለ የሚመሠረት) እረፍት የሌለው ዘመቻ ማካሄድ እርግማን እንጅ ፈፅሞ በርከት ሊሆን አይችልም!!!

አዎ! ይህንን አይነት እጅግ ቅጥ ያጣ ብቻ ሳይሆን የትኩረት አቅጣጫውን የሳተ “ተውኔተ ገዳም” ግንባታ የሚባርክ እውነተኛ አምላክ ፈፅሞ የለምና ንስሃ ግቡና በእኩያን ገዥዎች ሁለንተናዊ መከራና ውርደት ለተጫነበት የአገራችን መከረኛ ህዝብ የምትችሉትን አድርጉ (የምንችለውን እናድርግ)! ያኔ ነው የእውነተኛው አምላክ በረከት እውን የሚሆነው!!!

ወገኖቼ ሆይ! ምነው ከእኛ አልፎ ፈጣሪንም ቅጥ ያጣ ፍላጎታችን ፈፃሚ ባናደርገው!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፋኖ አደረጃጀቶች አንጻራዊ ወሳኝነትና የእስክንድር ነጋ ወሳኝ ሚና

 

 

1 Comment

  1. እውነት ብለሃል ቅጥ ያጣ የባህር ማዶ የገዳም ግንባታ የሚመክር እና የሚገሰጽ መነኩሴ ጠፍቶ በፍቅረ ንዋይ የሰከረ በተለይም ይህንን ተግባር የጀመረው እና ለገዳሙ ያልሰጠ አይጸድቅም እየተባለ የሚሰብከው መነኩሴ፤ ጽድቅና ኩነኔም በጁ እንድያዘ የሚመጽደቀው ከንቱው መነኩሴ ሲሆን ሚዲያኑም እኮ በእንግሊዘኛ (ዶንኪ ዩቱብ )ይበለው እንጂ ሲያገኝ እያክላላ የሚሮጥ ሲያጣ ጀሮውን የሚጥል የአህያ ሜዳ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share