የዐማራ ሕዝብ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መውጣት ነው

 ገብሩ ተንሳይ እና አይደፈር አስፋው

ምስል 1. ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ኢትዮጵያ እና አስራ አምስት የኢትዮጵያ የኮንፌደሬሽን  መንግስት አስተዳደራዊ ክልሎች እና ዝርዝር ዞኖች አመላካች ካርታ

 

የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) እ.ኤ.አ በ1975 ዓ.ም. ተመሠረተ። በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ  ተራሮች ለ14 አመታት ከኢትዮጵያ መንግስት  ጋር ሲፋለም ቆይቶ እ.ኤ.አ. በ1989 ዓ.ም. የኢህአፓ ቅሪት ከሆነው ኢሕዴን ጋር በመጣመር ኢህአዴግ በመባል የሚታወቀውን ቅንጅት ፓርቲ መሰረተ። እ.ኤ.አ. በ1991 ዓ.ም. የኢትዮጵያን በትረ መንግስት ጨብጦ የነበረውንና  ደርግ ተብሎ የሚታወቀውን ወታደራዊ ቡድን በማሸነፍ ስልጣኑን ተቆጣጥሮ የጎሳ ፌዴራሊዝምን በኢትዮጵያ ዘረጋ። ይህም ሆኖ ሳለ ፓን-ኢትዮጵያዊነት እስከ እ.ኤ.አ. 2005 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ታዋቂነት ያለው ጽንሰ-ሀሳብ ሆኖ ቆይቷል። ይህንንም ሁኔታ ለመረዳት የ ቅንጅትን (CUDን) ተሞክሮ ጨምሮ ካለፉት የፖለቲካ መዛግብት በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በሟቹ ሃይሉ ሻወል የተመራው ቅንጅት (CUD) ፓርቲ በኦሮሚያ ብዙ ከተወራለት እና በመረራ ጉዲና ከተመራው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ፓርቲ የበለጠ ድምጽ አግኝቷል።

 

እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. በተካሄደው ሃገር አቀፍ ምርጫ በህወሓት የበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፍተኛ ሽንፈትን ተከትሎ ገዥው ፓርቲ የምርጫውን ውጤት በኃይል በመቀየር፤ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን በማሰር እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዳይሰሩ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበቡ አፋኝ ህጎችን አወጣ። ከምርጫው ማግስት ብዙም ሳይቆይ ከዴሞክራሲና ከመልካም አስተዳደር ይልቅ ልማት የገዥው ፓርቲ የእለት ተእለት መፈክር ሆነ። ኢህአዴግ በ2010 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ሀገራዊ ምርጫ 99.6% ድምጽ አገኘሁ በማለት እውነተኛ የህዝብ ወኪል እኔ ነኝ ብሎ መመጻድቁን ቀጠለ። ህወሓት በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ ሽፋን፤ የፓርቲውን የአመራር ቁንጮ መዋቅር በትግራይ ልሂቃን በማስያዝ በኢህአዴግ ውስጥ በተሳካ ሁኔታ የበላይነቱን ማስጠበቅ ችሏል።

 

በዚህ ስልት ህወሓት የተሳካ ስራ ቢሰራም እንደ ህውሓት ላለ በአናሳ ብሄረሰብ ለሚደገፍ ፓርቲ ለዘላለም በስልጣን ላይ እንዲቆይ ሁኔታዎች የሚደግፉ አልነበሩም። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ከኮንፌዴሬሽን አደረጃጀት ጋር ይመሳሰላል፣ እናም ይህ አደረጃጀት ከጊዜ በኋላ ታይቶ የማይታወቅ የርዕዮተ ዓለም ጥንካሬ አግኝቷል። በሂደት በተለያዩ የኮንፌዴሬሽኑ ክልሎች ውስጥ ያሉ ልሂቃን በክልሎቻቸው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ብቸኛ ተዋናይ አድርገው ራሳቸውን መመልከት ጀመሩ። በዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት ስም ከ1991 እስከ 2017 ዓ.ም. ድረስ ኢትዮጵያን በጉልበት አፍኖ የገዛው ህወሓት ቀስ በቀስ የውሳኔ ሰጭ ሥልጣኑ እየተሸረሸረ ሄደ፤ በመጨረሻም በ2017 ዓ.ም. መገባደጃ ላይም አገዛዙ መፈራረስ ጀመረ።

 

ከ2017 ዓ.ም. በፊት የኢትዮጵያን የፖለቲካ የሃይል አሰላለፍ የቀየሩ ሁለት ወሳኝ ክስተቶች ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም. የወልቃይት ዐማራ ንቅናቄ መሪ የነበሩትን ኮረኔል ደመቀ ዘውዱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የትግራይ መንግስት ፖሊሱን እና ሚሊሻውን በላከ ጊዜ ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ በጎንደር ከፍተኛ የታጠቀ ተቃውሞ ገጥሞታል። በዚህ አጋጣሚ ጠንካራና የተፈራ ፓርቲ ተደርጎ ይታይ የነበረው ኢህአዴግ አሁን የማይሸነፍ ድርጅት ሆኖ አልታየም። ያ ክስተት የህወሀት ወሳኝ ደጋፊዎች ለህይወታቸው በመፍራት እና በዐማራ ክልል የወደፊት ተስፋ እንደማይኖራቸው በማመን በሺዎች ቁጥር ሆነው የጎንደር ከተማን ለቀው እንዲወጡ ምክንያት ሆነ። ከጎረቤቶቻቸው ከዐማሮችም ምንም እንድማይሆኑ ማረጋገጫ ቢሰጣቸውም ሊሰሙ አልፈቀዱም።  በጎንደር  ከተማ በኢህአዴግ  ላይ የደረሰው ሽንፈትን ተመርኩዞ  ሁለተኛው የተቃውሞው ወጀብ በኦሮሞዎች ተቀሰቀሰ። በከተሞች የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች እና እግረኛ ወታደሮቻቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ በብዛት እየተደራጁ በመምጣት  ፋብሪካዎችን በማቃጠል፣መንገዶችን በመዝጋት እና የአቅርቦት መስመሮችን በመዝጋት በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ተቃውሟቸውን ገለጹ። በዚህን ጊዜ በኢህአዴግ ውስጥ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ግራ ተጋብተው ምን ማድረግ እንዳለባቸው መላ አጡ፣ እናም ሀይለማርያም ደሳለኝ በመጨረሻ በወርሃ መጋቢት 2018 ዓ.ም. የችግሩ የመፍትሄ አካል ለመሆን በማለት ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመልቀቅ ወስነው በምትካቸው አብይ አህመድ ተሹመዋል።

 

በ2018 ዓ.ም. አብይ አህመድን ወደ ኢትዮጵያ የስልጣን እርከን ያመጣው ለውጥ ክጅምሩ ብዙ የተደነቀ እና የመላው ኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ ያገኘ ቢሆንም በጥቂት ወራት ውስጥ መንገዱን ከመሳት ባለፈ ሙሉ በሙሉ አቅጣጫውን በ180 ዲግሪ ቀየረ። በኢትዮጵያ ፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ እንዲመጣ ማድረግ ይቅርና ዛሬ ለፓን-ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በትግራይ እና በኦሮሚያ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ እንኳ ፈጽሞ የማይቻል ነገር ሆኗል። ዛሬ በመዲናይቱ አዲስ አበባ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንኳን ማድረግ የማይችሉበት ሁነታ ተፈጥሯል፤ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቀትተኛ ተእዛዝ በፖሊስ በከፍተኛ ደረጃ አፈና እየተደረገባቸው ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲም ሆነ መልካም አስተዳደር ፈጽሞ አይታሰብም። ዛሬ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል እና አንዳንድ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዐማራ ዘር ያለው ሰው አጥንትና ስጋ መፍጫ ማሽን ሆነዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለኦርቶዶክስ ስኖዶስ

 

ኢትዮጵያ (120 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት) አንድ አካል ሆና መቀጠሏ ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ወይም ብሔረሰብ የሚጠቅም ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ታዋቂነት እና የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት እያደገ ይሄዳል፣ እናም የአፍሪካ መግቢያ እና አስታራቂነት ቦታዋ በፕላኔታችን ላይ ባሉ ሀይሎች ሁሉ እንደሚነገርና እንደሚሰማ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ያ ሚና በልሂቃኑ የጎሰኝነት አስተሳሰብ ምክንያት ለኢትዮጵያ ያለፈ ታሪክ እና የመከነ እድል ሆኗል። የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ወደ ጎሳ መከፋፈል እና ምናልባትም የፍቃደኞች ጥምረት መፍጠር ነው። ባሁኗ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የየብሄረሰቡ ባለቤት ለመሆን ሲነሳሱ የዐማራ የፖለቲካ ልሂቃን ግን ከእውነታው የራቁ ሆነዋል። ለነሱ በህልማቸውም በቁማቸውም ያለቺው ኢትዮጵያ ናት። እኛ ደግሞ ይህን ቅዠት እንለዋለን። በዐማራው ለቀጠለው የኢትዮጵያዊነት ትርክት ምክንያቶቹ  ብዙ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ይገኙበታል።

 

የዐማራው ያልተጨበጠ ተስፋና አጉል ምኞት

የዐማራ ልሂቃን ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዐማራዎችን ጨምሮ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን እንደሚወዱ እና አንዱ ለአንዱ እንደሚተሳሰብ አድርገው ያምናሉ። በዚህ ምናባዊ እና የማይጨበጥ የምኞት አስተሳሰብ ምክንያት ተራ ዐማራዎች ህይወታቸውን ጨምሮ ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ኢትዮጵያውያን በሚሳተፉበት የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈጣን ቅኝት ቢደረግ በተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች ልሂቃን መካከል ያለው አጠቃላይ እይታ እና የሚያሳስባቸው አብይ አጀንዳ የየራሳቸው የጎሳ መንደር ብቻ እንደሆነ መገንዘብ ቀላል ነው። ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ሳይመጡባቸው የመንደራቸው፣ የዞናቸው እና የክልላቸው ብቸኛ ባለቤት ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ለሦስት አስርት ዓመታት በህወሓት ተቋማዊ ፕሮፓጋንዳ የተነሳ፣ እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ዐማሮች በአንድ የተማከለ አገር፣ አንድ ቋንቋ፣ እና አንድ ሃይማኖት የሚያምኑ ሕዝቦች ሆነው ይታያሉ። ይህ አስተሳሰብ በብዙ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ልሂቃን አእምሮ ውስጥ ሥር የሰደደ እና በተለይም በኦሮሞዎችና በትግራይ ልሂቃን ዘንድ የተለመደ የመነጋገሪያ ርእስ ነው። እንደምናውቀው፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሥርዓት በመጨረሻ የሚወስነው በየጎሳው ልሂቅ እና በጽንፈኛ ቡድኖች ነው። ይህ በተለይም  በኢትዮጵያ የአስተዳደር ልምድ የታወቀ ጉዳይ ነው።

 

እውነትን ያለመመርመር እና ያለመቀበል የዐማራዎች አባዜ

ዐማራ ከመሆኔ በፊት ኢትዮጵያዊነቴ ይበልጥብኛል የሚለው ፅንሰ-ሀሳብ እና እምነት በዐማራዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፣ የዐማራ ልሂቃን ይህንን እውነታ የተረዱት አይመስሉም። ብዙም ይሁን ምንም የፖለቲካ ግንዛቤ እና ወገኝተኝነት የሌላቸው ተራ ዐማሮች ንብረቶቻቸውን እና ከሁሉም በላይ ውድ ህይወታቸውን እየተነጠቁ ነው። በፖለቲካ ቅስቀሳ እና በተሳሳተ የፖለቲካ እምነት ዐማራ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸው አገር ዜጋ የሆኑ ዐማሮችን እያጠቁ ነው። እውነታው ግን ኢትዮጵያ በዐማራ ባልሆኑ ኢትዮጵያውያን አእምሮና ልብ ውስጥ የለችም። ዐማራዎች ውዷ ኢትዮጵያ የነሱ የምናብ አስተሰባሰብ ፍጥረት መሆኗን ተረድተው ከዚህ አስተሳሰብ በፍጥነት ካልወጡ በደመና ላይ ተንጠልጥለው የራሳቸው ብለው የሚጠሩበት አገርና መሬት አይኖራቸውም። የኢትዮጵያ ጉዳይ ተዘግቷል። ኢትዮጵያ ብትፈርስ አማራው በተለየ ሁኔታ የሚደርስበት ችግር የለም። እንዲያውም ነጻ ይወጣል። ኢትዮጵያዊነትን ከሞት ማዳን ካስፈለገ ዐማራ ያልሆኑት ሁሉ አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ አለባቸው። ከዚህ ባለፈ የዐማሮች የቤት ስራ መሆን የለበትም።

 

ለስድስት አስርት አመታት ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲመጣ የዐማራው ጥያቄ ነበር። ዐማሮች በማንኛውም አይነት ኢአፈና ወይም ኢፍትሃዊ እንቅስቃሴ ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበሩ። የዐማራ መምህራንና ተማሪዎች ለእኩልነት እና ለፍትህ ሲሉ የገዛ ወላጆቻቸውን ንብረት እንዲወረስ ድጋፍ እስከማድረግ ደርሰዋል። ዐማራዎች ለመላው ኢትዮጵያዊያን መብት ሲባል የህይወት መስዋዕትነት ቢከፍሉም የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ለዐማሮች ግድ እንድሌለው ሊገነዘቡት ይገባል።

 

ዐማራው ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰማህ ወይ የነፍጠኛ ልጅ! - በላይነህ አባተ

ዲሞክራሲና ፍትህ ሊሰፍን የሚችለው በህብረተሰቡ ውስጥ የጋራ መግባባት ሲኖርና ሲፈጠር ነው። ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት እና የፖለቲካ ውድቀት ሲከሰት መጥፎ መሪዎችን ከስልጣን ለማንሳት መግባባት ሊኖር ይገባል። ይህን ለማድረግ ከብሄር አስተሳሰብ ፈጽሞ መውጣት ያስፈልጋል። የብሄር ፌደራሊዝም እና ዲሞክራሲ እርስ በርስ የሚጋጩ ናቸው። በእንደዚህ ዓይነት አስተዳደር ውስጥ የፖለቲካ መሪዎች ተጠያቂ አይደሉም። ይልቁንም የብሔር ማንነትን መግለጽ፣ ማግለል እና አድልዎ የአምባገነንነትና የጎሰኝነት ስርአት መለያና የጉልበት በትሮች ናቸው። ይህ ሲባል ግን ዐማራዎች አሁን ከሚሰቃዩበት አንዱ ከሆነው የብሔር ጭቆና የሚያመልጡበት መንገድ የለም ማለት አይደለም። ብሄርን መሰረት ባደረገ መጥፎ አስተዳደር ስር ለዘላለም መገለል እና መጠቃት የሚፈልግ ዐማራ ማነው? ዐማራዎች ከ32 ዓመታት በላይ ከከፈሉት መስዋዕትነት እጅግ ጠቃሚ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል። የዐማራ ልሂቃን የኢትዮጵያዊነትን አስተሳሰብ ሙጥኝ በማለታቸው እና ለህዝባቸው የሚሆን መላ ባለመፍጠራቸው የጅምላ መፈናቀል፣ የዝርፊያ እና የግድያ ሸክሙን የተሸከሙት ተራ ዐማሮች ሆነዋል። በሚኖሩበት የአማራ ክልል እንኳን የህይወት ዋስትና እያጡ ያለበት ሁነታ መጥቷል። የዐማራ ልሂቃን በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ከቀጥሉ ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት እየሰሩ ነው። ይህ አስተሳሰብ አማሮች ስለ ርስቶቻቸው እና በሱዳን ስለተወረረው መሬታቸው እንዳያስቡ እያደረገ ከሞሆን አልፎ ህይወታቸውን እንዳይታደጉ እያዘናጋቸው ነው።

 

ዐማራዎች ለራሳቸው የሚጨነቁበት፣ የምኞት አስተሳሰብን የሚጥሉበት እና እውነታውን የሚቀበሉበት ጊዜ አሁን ነው። እውነታውን ሲቀበሉ መፍትሔው ግልጽ ነው፤ የሚያስፈልገው በምስል 1 ላይ እንደተገለጸው ዐማሮች የአባቶቻቸውንና የታሪክ ግዛቶቻቸውን  በመጠየቅ (ዳሞትን፣ ሸዋን እና ደዋሮን ጭምሮ)፣ በሉአላዊ የአማራ ግዛት ዉስጥ ያሉ የአናሳ ብሄረሰብ መብቶች ተከብረው፣ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ እንደ ገለልተኛ አገር የራሳቸውን መንግሥት መመሥረት ነው ያለባቸው። ዐማራ ያልሆኑ በቅንነት ኢትዮጵያ እንድትኖር የሚፈልጉ ካሉ፣ ለዚህም ጥረት ካደረጉና ዐማሮችን ከጋበዙ፣  ዐማሮች በኢትዮጵያ ህገ መንግስት በአንቀፅ 39 ላይ የሰፈረውን መብት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብለው  የራሳቸውን ክልል ጸጥታ በራሳቸው ጦር አስከብለው በፌደሬሽን ሳይሆን በእውነተኛ ኮንፌደሬሽን ማእቀፍ ውስጥ አብሮ ለመኖር አይቸገሩም።

 

በኛ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ አክትሟል። በአንድ ትሪሊየን ቤተመንግት አንጾ በድሃ ህዝብ ላይ ተንቀባሮ ለመኖር የቆረጠ አገዛዝ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደርን ለኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣል ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ እሱ ከእውኑ አለም በእጅጉ የራቀ ነው። ዐማሮች ማወቅ ያለባቸው የኢትዮጵያ አካል ሳይሆኑ የበለፀገ የዐማራ አገር መገንባት መቻላቸውን ነው። የዐማራ ምድር ስትራተጂካዊ አቀማመጥ፣ ታታሪ ገበሬዎቹ፣ ሰፊ የውሃ ሃብቱ፣ ማራኪ መልክአ ምድሩ፤ የቱሪዝም መስብ የሆኑት ታሪካዊ ቅርሶቹ እና ለም የእርሻ መሬቱ ለዐማራው አስቻይ ሁኔታዎችን ይፈጥርለታል። አንድ አራተኛውን የዐማራን መሬት የቆዳ ስፋት እና ግማሽ ያህሉን የዐማራ ሕዝብ ብዛት ያላት ኔዘርላንድስ እ.ኤ.አ. በ 2022 ከግብርና ኤክስፖርት ብቻ 49.6 ቢሊዮን ዩሮ ገቢ አስገኝታለች። ታታሪ አርሶ አደሮች ያሉት የዐማራ ክልል የራሱን ሀገር ለመገንባት ከመረጠ በሁለት አመታት ውስጥ ብቻ ረሃብንና የምግብ እጥረትን በማስወገድ ታሪክ ሊሰራ ይችላል።

 

አሁን ዐማሮች ሊያተኩሩበት የሚገባው እንደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ ካሉ አገሮች ጋር መወዳጀትን ነው። የዐማራውን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ከሱዳንና ግብጽም ጋርም ቢሆን መነጋገር ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክልሎች ደግሞ እንደ ሶማሊ፣ አፋር እና በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉ የተመረጡ ብሔረሰቦች (ለምሳሌ ጉራጌ፣ ጋምበላ፤ ጋሙ፣ ወዘተ) ጋር የመደበኛ ግንኙነት፣ የጸጥታ እና የንግድ ስራ ግንኙነት መፍጠር ያስፈልጋል። ከ60 አመታት በላይ በጥላቻ ተወጥሮ ለመላው ዐማራ ባልተኛው በጽንፈኛ የትግሬ ልሂቅ ከምትመራው ትግራይ እና ለአምስት አመታት የዐማራውን እርድ ስታስተናግድ ከኖረችው እና ጽንፈኞች ከተቆጣጠሯት ኦሮሚያ ጋር ዐማሮች በአንድ አገር ውስጥ አብሮ ለመኖር አስቻይ ሁኔታ የለም። አንድ ጽንፈኛ የኦሮሞ ልሂቅ የኦሮሞ ጥያቄ አልተመለሰም ሲልህ ዐማሮች ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል መንግስት ቢሮክራሲ ተጥራርገው ይውጡ፤ ከአዲስ አበባም ለቀው ይውጡ፣ አማርኛ ከፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋነት ታግዶ በኦሮምኛ ይተካ፣ በአዲስ አበባ አማሮች ስለሚበዙ ለሱዳን እና ለግብጽ ውሃ በነጻ እየሰጠንም ቢሆን አዲስ አበባ ግን ትክፈለን፣ በነጻ ገበያ አዲስ አበባ ላይ ለምንሸጠው  አሸዋ ጠጠር ድንጋይ ሌላም ሌላም ነገር የአዲስ አበባ አስተዳደር ተጨማሪ ገንዘብ ይክፈለን  ማለቱ እንደሆነ ስንቶቻችን እናቃለን? የጤነኛ ሰው አስተሳሰብ አይመስልም። ግን ያለው ዕውነታ እሱ ነው።  ምቀኛ በራሱ ማግኘት ሳይሆን በሌላው ማጣት ይደሰታል እንዲሉ፣ የትግራይ እና የኦሮሞ ጽንፈኛ ልሂቃን በአማር ኪሳራ በእጅጉ ይደሰታሉ። አማራው በሁሉም አቅጣጫ ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ  ጦርነት ተክፍቶበታል። አንድ ዐማራ በኢትዮጵይያዊነቱ በሌሎች ክልሎች መኖር ካልቻለ፣ በመንግስት እና በግል ስራ ተቀጥሮ መስራት ካልቻለ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ከተከለከለ፣ በአዲስ አበባ በብሄሩ ተለይቶ ቤቱ ከፈረሰበት፤ በብሄሩ ተለይቶ የባንክ አካውንቱ ከተዘጋበት፣ ልሂቃኑ እየታደኑ ከታሰሩ የራሱን አገር ከመፍጠር ውጪ ሌላ ምን አማራጭ አለው? የገጥመን ህይወትን እና ሃብትን የሚነጥቅ ወንበዴ እንጂ ሰርቶና አሰርቶ አገር የሚያበልጽግ አስተዳደር አይደለም። ጎበዝ እንንቃ! ይበቃል!

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቁጥር ጨዋታ?! – ፂዮን ግርማ

 

ሁላችንም በአንድነት እንንቀሳቀስ

እ.ኤ.አ. መጋቢት 21 ቀን 1960 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ሻርፕቪል በምትባል አንድ የጥቁሮች ከተማ ውስጥ የነበሩ የፖሊስ መኮንኖች ጨቋኝ ህግን በተቃወሙ ሰላማዊ ጥቁሮች  ላይ ተኩስ ከፍተው  69 ሰዎችን ገደሉ። ያ ግድያ መላው አለምን አነቃነቀ። አፓርታይድ ደቡብ አፍሪቃ በጽኑ ትወገዘች።በዚህ ምክኛት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሻርፕቪል እልቂት እየተባለ መጋቢት 21 ቀን  አመታዊ ክብረ በዓል ሆኖ ለብዙ ዓመታት ሲታወስ ኖሯል። በኦሮሚያ ክልል አማራዎች በቤታቸው ተቀምጥው በሺዎች ቁጥር በአንድ ቀን ጀምበር እየተገደሉ እና በሚሊየን ቁጥር እየተፈናቀሉ ዘረኛው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትርና ዘረኞቹ የኦሮሚያ መሪዎች አልተጠየቁም፣ አልተወገዙምም። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጸመን ዘግኛኝ የአማሮች እልቂት እንኳን ሊከበር አለም እንደ ቀላል ትራጀዲ እንኳ ሊያየው አልፈቀደም። ይህም አልበቃ ብሎ የሃገሪቱ ህግ ከሚፈቅደው ድንጋጌ ውጪ አብይ አህምድ የህገሪቱን ግዙፍ የመከላከያና የኦሮሚያ ልዩ ሃይላት ልኮ በአማራ ክልል የሰላማዊ ሰዎችን መንደሮች በከባድ መሳሪያ እያቃጠለ፣ አርሶአደሮችን እየገደለና እየአፈናቀለ አሁን ላይ 40 ሚሊየን ያህል የሚገመተውን የአማራ ህዝብ ለረሃብ አጋልጦ በሞት አፋፍ ላይ ጥሎታል። አብይ አህመድ ባልተገባም መንገድ ቢሆን የአማራን ህዝብ እንዳልነበር ማድረግ እሱ ለኦሮሞ ህዝብ  ትቶት የሚያልፈው ትልቅ ትሩፋት ነው ብሎ አምኗል፣ በዚህም የመጀመሪያው ታላቅ እና ድንቅ ኦሮሞ ተብዬ፣ ስሜም በወርቅ ቀለም ተጽፎ በታሪክ ስታወስ እኖራለሁ ብሎ ከወዲሁ ራሱን አሳምኗል።

 

ዐማሮች ራሳቸውን የሚከላከሉበት ወቅት፣ ግዛታቸውን (ዳሞትን፣ ሸዋን እና ደዋሮን ጭምሮ) የሚይዙበትና የዐማራ መንግሥት ለመመስረት የሚዘጋጁበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው (ምስል 1) ዐማራ ያልሆኑ በተልይም የመንግሥት ዋና ተዋናዮች ትልቁ ዓላማቸው ዐማራውን በሙሉ ከሥፍራው ማፈናቀል፣ መንቀል እና ማጥፋት ነው። የዐማራው ምርጫ ወይ መጥፋት ወይም ለህልውናው መታገል ነው። ይህን ተገንዝበው ዐማራዎች የኢትዮጵያ ጠበቃና ጠባቂ መሆንን የሚያቆሙበት ጊዜው አሁን ነው፤ በዚህ አስተሳሰብ ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሏል፣ እናም የስካሁኑ  በቂ መሆን አለበት። የደርግ በሕወሃት መሸነፍ እና የአብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ተቀዳሚ ምክንያቶች ዐማሮች ስለራሳቸው ለማሰብ ያሳዩት ቸልተኝነት እና ዝንጉነት መሆኑን መረዳት አለባቸው።

 

ዴሞክራሲ እንኳን ባይሳካ ሰላም ያለው፣ የበለፀገ የዐማራ አገርና ሕዝብ እንዴት እውን መሆን እንደሚቻል መላው የዐማራ ልሂቃን ውይይቱን አሁኑኑ እንዲጀምሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የዐማራ ባለሙያዎች ለዚያ ግብ የሚሆኑ ማዕቀፎችን ለመዘርጋት የሚያስፈልገውን ዝርዝር ጥናትና እቅድ እንዲያወጡ እናበረታታለን። የሁሉም የትምህርት ዘርፍ መሐንዲሶች፣ የሀብት ስፔሻሊስቶች፣ ኢኮኖሚስቶች፣ የፋይናንሺያል ኦፊሰሮች እና ለሎችም ባለሙያዎች ጥልቅ የፖሊሲ ሰነድ ማደራጀት እንዲጀምሩ እናበረታታለን።  እንደ መነሻ ሃሳብ ከወልዲያ/ሃራ ገበያ ወደ አሰብና ጅቡቲ የአውራ ጎዳና መንገድና የባቡር መስመር ይከፈት፤ ከሁመራ እስከ ምጽዋ ያለው መንገድ ከኤርትራ ጋር በትብብር ይታደስ። ከጎጃም ባህርዳር፣ ከጎንደር ሁመራ፣ ከወሎ ኮምቦልቻ እና ከሰሜን ሸዋ አረርቲ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ይደረጉ።

 

ዐማራን እግዚአብሔር ይባርክ!!!

8 Comments

 1. አማራ ከፌደረሸኑ የወጣ ቀን ለመቶ ዓመታት ኢትዮጵያን ሲያሰቃይ የነበረ መከራ አከተመለት ማለት ነዉ። ብትወጡ ለሎች ሕዝቦች ተልቅ ዉለታ ዋላችሁ ማለት ነዉና ከፍተኛ ሽኝትና ምስጋን ይቸራችኋል። ግን ልብ የላችሁምና አታረጉትም።

 2. ቦቅቧቃ ነገር ነህ አማራማ ከነምናምንህ ተሸክሞህ ነው የኖረው. አማራ የስነልቦነው ስሪት እንዳንተ የላሸቀ አይደለም እድሜ ጠገቡ አማራ ነው ያሰለጠነህ፡ አንተ ለሌሎች ግድ የማይልህ ልበ ትንሽ ነህ ፡አማራን የምትጠላው ካንተ ላቅ ያለ አስተሳሰብ ያለው አስተዋይ ስለሆነ በምንም ጉዳይ ክርሱ ጋር ቁጭ ብሎ ነገሮችን መከወን ብርክ ብርክ ስለሚልህ ነው፡ ስለዚህ እንደፈለግህ በህዝብ ላይ እንድትባልግና እንድትፈነጭ ስስማይፈቅድልህ አማራን ትጠላዋለህ፡ እሱ ግን እየጠላከው ይወድሃል፡፡ አሁን ግነ የነብር አራስ ሆኖ መጥቶልሃል

  • አማራ ማለት እኮ ልብስ መልበስን ከ ኦሮሞ የተማረ ህዝብ ነዉ ጥርግ በሉ ሸፋፋ ሁላ

   • ህ ህ ህ ህ ! ኦቦ ጅረንያ፣ ቀልደኛ ነህ። አሁን ያለው የኦሮሞ መነሻው ጉጂና ቦረና ናቸው። በአሁኑ ሰአት ሁለቱም የከብት ጭራ ተከትለው ሲዞሩ የሚውሉ ናቸው። ወደ ሰሜን የፈለሰው ቀሪው ኦሮሞ ደግሞ ከደጉ የአማረ ህዝብ የእርሻ ስራ እና የምግብ አዘገጃጀት ተምረው ሰልጥነዋል። አንዱ ከአንዱ ይማራል ችግር የለውም። አማራም ቢሆን ከሰለሞን ስርወ መንግስት የውሰደው ጥበብ ነው ከፍ ያደረገው።

 3. Write your comment…፨ይህ የተሻለ አማራጭና ዘመናዊ ስልጡን ሀሳብ አይደለም። ችግሮች ሊኖሩ ቢችሉም በሰላማዊ ትግል ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በመምከር ካልሆነ በተቀየሰ የግዛት ስልቀጣ የትም መድ ረስ የሚቻል አይመስለኝም። ሌላው ህገመንግስቱ አሁኑኑ ይቀደድ ብላችሁ እንዲሻሻል እንኳን ሳትፈቅዱ አንቀፅ 39 ላይ ዘላችሁ ቁብ ማለት ያስተዛዝባል። በኔ አስተያየት ኢቶዮጵያ…ኢትዮጵያ እያልን እየዘመርን እናንተም ኢትዮጵያን ጠፍጥፈን ሰራናት እያላችሁ ዛሬ ደግሞ እንገንጠል ማለት ብቻ አይደለም ማሰቡ እንኳን ያስተዛዝባል ያሳፍራል። ባይሆን ሰላማዊ ትግላችሁን አጠናክሩና ለምክክር ዝግጁ ሁኑ ።

 4. የአገውን የላሊበላ ስልጣኔና የትግራይን የአክሱም ሃይማኖት በመዋስ የራሱ ለማድረግ የሚሰቃየው፣ የኢትዮጵያ የዘመናት ነቀርሳ ሆኖ የቆየው ራስ ወዳዱ፣ ፅንፈኛው አማራ ከፌደሬሽኑ ወጣ ማለት ሌላው ህዝብ ሰላም ኣገኘ ማለት ነው። ድል ባለ ድግስ እናሰናብታችሁ ነበር። ለራሳችሁ የምትመች ኢትዮጵያውያ ስትመስላችሁ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ጠባቂዎች። ሲከፋችሁ፣ ወደ ጎሳ መደበቅ። የወሸትንስ የቅሚያ ታሪክና ማንነት።

 5. Blessings in disguise for Ethiopians.
  Ethiopia has only one problem, Amhara. If Amhara elite leave, the rest of us will have no problem living in harmony and peace.
  We will every thing to make sure your dreams come true.

 6. የአማራዋ ኢትዮጵያ እንዳል ነበር የሆነችው የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት እንደፈረሰ ነበር:: የአሁኗ የብዙ ብሔረሰቦች ናት:: የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች አንድነት ለዘለዓለም ይኑር!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share