May 7, 2023
1 min read

ሸገር የሚባለው አዲስ “ፕሮጀክት” ላይ በርካታ መስጊድ እየፈረሰ ነው። ውስጥ እየሰገዱ ላያቸው ላይ አፍርሰውባቸዋል።

345661778 679732273910132 4564763441425778178 n 1
#image_title

345661778 679732273910132 4564763441425778178 n 1

ውሃብያ ፀጥ ረጭ!
የሙፍቲ ጊዜ ቢሆን ከቤታቸው አውጥተው “አስጠቃኸን” ብለው ይገድሏቸው ነበር። ከምንም በላይ እንኳን አማራ ክልል አልሆነ! ያኔ ቱርክን ጭምር መግለጫ አስወጥተዋል። በየመስጊዱ ጎንደር እና ሞጣን አውግዘዋል። አማራ እንደ ህዝብ ተወግዟል። አላማቸው እምነት ቢሆን አሁንም ይጮሁ ነበር። አላማቸው ጥላቻ ነው።
ውሃብያ ስል የሚከፋህ ካለህ ጉዳይህ ነው። ሌባ! ቀጣፊ!
ጌታቸው ሽፈራው

4 Comments

  1. ለዚህች ኢትዮጵያ ለምትባል ሃገር ሸሁ ከመስጊድ፤ ቄሱ ከመቅደሱ፤ ገበሬው ከእርሻውና ከኑሮአቸው ላይ ተነስተው ምድሪቱ በውጭ ሃይል እንዳትደፈር በዘመናት መሃል ደማቸውን አፍሰዋል። ውሻን ውሻ እየተካው የመናከስ የዘርና የቋንቋና የፓለቲካ ማጥ ውስጥ ሃገሪቱ ከተጣለች በህዋላ ግን ሰው በሰውነቱ መመዘኑ አክትሟል። አሁን በሃበሻ ምድር የምናየው ከድሮው በከፋ መልኩ የአፓርታይድ አገዛዝን ነው። በቅርቡ ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዲህ ይለናል። ” ብልጽግና በሰራው ግፍ የኦሮሞ ህዝብ ስም መጥፋት የለበትም ይለናል” የኦሮሞ ህዝብ አብሮ መኖርን የሚያውቅ፤ ለሌላው አዛኝና አቃፊ እንደሆነ በስማ በለው ሳይሆን በውስጡ ኖረን እናውቃለን። የኦሮሞ ህዝብ ችግር ነጻ እናወጣሃለን እያሉ በስሙ የሚነግድት የእድሜ ልክ የብሄር ሰካራም ፓለቲከኞች ናቸው። ኦፌኮ የኦነግ ሰራዊት በወለጋና በተለያዪ የኦሮሚያ የአፓርታይድ ክልል ሰው ሲገልድልና ሲያፈናቅል ድምጽን አላሰማም። በአዲስ አበባ በሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ቤታቸው እላያቸው ላይ ፈርሶ ሜዳ ላይ ሲጣሉ ምንም አላሰማም። አሁን ዞሮ ተመልሶ እኛ ሳይሆን ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽሙት የብልጽግና መንግስት ነው ማለት አውራ እጣትን ከአመልካች እጣት ጋር አወዳድሮ እንደመፈረጅ ይቆጠራል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፓለቲካ ጊዜ የሰጣቸው የኦሮሞ ፓለቲከኞች በህዝብ ላይ መከራ አዝናቢዎች ናቸው። ይህ ሲባል አማራው፤ ትግሬው ሌላውም በየጎሳው በክልል የተሰባሰበው ክንፍ ያበቀለ መልአክ ነው ማለት አይደለም። ሁሉም የፓለቲካ ጉንድሽ ነው።
    በምንኖርበት ዘመን የማይቀየር፤ የማይረሳ ምንም ነገር የለም። የሰውም እድሜ በዛ ቢባል 80 ዓመት ነው። ከዚህ በዘለለ ከተቆየም ድካምና መከራ እንጂ መኖር አይባልም። ፈላስፎች የሰው ልጅ ሶስት ጊዜ ይሞታል ይላሉ። እኛ ሃበሾች ግን አራት ጊዜ የምንሞት ይመስለኛል። ስንወልድ፤ ሞተን ስንቀበር፤ ለስማችን ያቆምነው፤ ያፈራነው ሃብት ሁሉ ፈራርሶ ስንረሳ ሶስተኛ ሞት ሲሆን አራተኛው ሞት ከትውልድ ትውልድ የፈጠራ ቂም የሚቋጥር እንደ ሃበሻ ያለ ህዝብ በምድር ላይ የለምና አራተኛው ሞታችን ትውልዳችን እየተሰላ የቆመን ሁሉ በቂም የሚበቀል የሙት መንፈስ በሃገሪቱ ላይ መኖሩ ነው። እውን የሰው ህይወት በፍትሃዊ ሂሳብ ከተተመነ ባንድ ቀን ተወልደው ኑሮው ዓለማቸውን አይተው እንደሚያልፉት በራሪ ፍጥረቶች ጋር ይመሳሰላል። ይህ አይነቱ ስሌት ግን ለእድሜ ልክ ፓለቲከኞች አይገለጥላቸውም። የዛሬ 50 ዓመት ሲጨፍሩ በኖሩበት ታምቡር ዛሬም ህዝብን ያማታሉ፤ በህዝቡ ስም ይነግዳሉ፤ ደም ያፈሳሉ፤ ደማቸው ይፈሳል። ይህ የዝንተ ዓለም የፓለቲካ አተካራ ሃገሪቱ ባለችበት እንድትሄድ ካደረጋት ዘመን ተቆጥሯል። ፍትህ ስንፈልግ በጉቡ፤ በማስፈራራት፤ በመግደል፤ በማሰር ዝም ለማሰኘት የሚደረገው ወሽካታ የፓለቲካ አካሄድ ብዙ እንደማያስኬድ ከቀደመው የሃገሪቱ ታሪክ አልተማርንም። ዛሬም ያዘው ጥለፈው፤ በለው በላት የቀን ሥራ ሆኖ ምድሪቱን እያተራመስን እንገኛለን።
    አሁን በወንድምና እህቶቻችን መስጊድ መፍረስን እያየ ዝም ያለ ነገር የራሱ ቤት ላለመናድ ዋስትና የለውም። ሲጀመር ኦሮሚያ፤ አማራ፤ ትግራይ የሚባል ምድር የለም። ምድር ሁሉ በህግ ለሚኖሩ ኢትዪጵያዊያን/ዊቶች እንጂ የአንድ ብሄርና ጎሳ ሥፍራ አይደለም። እነዚህ የብሄር ነጻነት ጡሩንባ ነፊዎች ያመጡብን መከራ እንጂ ምድሪቱ ሰፊ ለሁሉ የምትበቃ ናት። ትላንት “ዓለም አቀፍ ውዝ አደሮች ተባበሩ” ባለበት አንደበቱ አሁን ተገልብጦ ሰለ ብሄሩና ቋንቋው ሲዘላብድ መስማት ያንገፈግፋል። መንግስት ይዋሻል፤ ጋዜጠኛው፤ ጦማሪው ይቀባጥራል። መንግስት እነርሱ ብቻ በስለላው የተካኑ ይመስል (የሰላይ ተሰላይ) መኖሩ ጠፍቷቸው ህዝብን በፈጠራ ወይም (Deepfake) ለማማታት ሞክረዋል። ወያኔ ከጣሊያን በገዛው የስለላ ሶፍትዌር ህዝብ ይጠልፍና ይኮንን እንደነበረው የድህነቱ መንግስት ደግሞ አሁን በሁለት ፋኖዎች መካከል ከአቶ የሺጥላ ግርማ ግድያ በህዋላ የተደረገ ንግግር ነው በማለት ለጥፏል። እውነትነት አለው? ዘመኑ እንዲህ በቀላሉ የሰው ልጅ የሚታለልበት ነው? አይደለም። እኔ የጄ/ጻዕረ መኮነን ገዳይም የታሰረው ወታደር እንዳልሆነ ነው የማምነው። ለምን ነበር ከግድያው በፊት ለመዛወር የጠየቀውና የተከለከለው? ብቻ ፓለቲካው በዘርና በቋንቋ ጡዞ እየነደደ በመሆኑ የኢትዮጵያ የወደፊት እድል ፈንታ ከሱዳን፤ ከሱማሊያና ከሌሎችም ፍርስራሽ ሃገሮች ተርታ የተለየ አይሆንም። ሞኝና ወረቀት ያስያዙትን አይለቁም እንደሚባለው የብሄር ትርክተኞች በጭራሽ ከሰፈራቸው ውጭ ሌላ ዓለም ያለ አይመስላቸውም። የመስጊድ ማፍረሱና ሰውን ማዋከቡም ከዚሁ አፋርሽ የፓለቲካ ቡድን የመነጨ የጥፋት መንገድ ነው። በጊዜ ሊታረምና ሊቆም ይገባል። በቃኝ!

  2. እውነት አልመሰለኝም ይሄ ዜና አማራ ክልል ያልተቃጠለ መስኪድ ተቃጠለ ብሎ በሃሰት አገር ምድሩን ጤና የሚነሱት አህመዲን ጀበልና አቡበከር ማነው የተባሉ ጽንፈኞች የታሉ ታዲያ? ቤተክርስቲያኑን ችቦ በችቦ አድርጉት ሲሉ ለነሱም ቡልዶዘር ታዝዝ?የብርሃኑ ነጋን መግልጫ ማዳመጥ ነው እንግዲህ

  3. ” ብልጽግና በሰራው ግፍ የኦሮሞ ህዝብ ስም መጥፋት የለበትም ይለናል” የኦሮሞ ህዝብ አብሮ መኖርን የሚያውቅ፤ ለሌላው አዛኝና አቃፊ እንደሆነ በስማ በለው ሳይሆን በውስጡ ኖረን እናውቃለን። የኦሮሞ ህዝብ ችግር ነጻ እናወጣሃለን እያሉ በስሙ የሚነግድት የእድሜ ልክ የብሄር ሰካራም ፓለቲከኞች ናቸው። ኦፌኮ የኦነግ ሰራዊት በወለጋና በተለያዪ የኦሮሚያ የአፓርታይድ ክልል ሰው ሲገልድልና ሲያፈናቅል ድምጽን አላሰማም።”

    Amen.
    Since Jawar Mohammed and other IFLO members joined the OFC, the F has come to stand for Fascist (and not Federalist). Let alone condemn the massacre of civilians on ethnic bases, OFC has been issuing genocidal coded statements or cover-ups for those committing the massacre. OFC has sunk so low as to issue fabricated and false statements to incite violence against the unarmed non-Oromo civilians in Oromia.
    That is how Merera Gudina is ending his formerly moderate Oromo nationalist career: dirtied in the genocidal mud and smeared in the blood of innocent civilians slaughtered, looted, burned by the collaboration of radical Oromos within and outside the state apparatus.

  4. ጁዋር ጩሉሌ የከተማ ልጅ ነች ዛሬ ቢጠሯት የማትሰማ ቱጃር ነች ፖለቲካውን ያዝ ለቀቅ የምታደርገው የዲያስፖራ ቄሮ ያዋጣነው ገንዘብ ከምን ደረሰ እያለ ስለጨቀጨቃት እንጅ ነገሩ በሚገባ ገብቷታል። የአሜሪካ ፓስፖርቷንም አልመልስም ብላለች። ዛሬ ሰማዩን በካልቾ እየመታች ነው መኖር የምትፈልገው። ይኸው መራራ ምን አገኘ ሽመልስ መሰለኝ ከህዝብ ገንዘብ ዘግኖ ቤት የሰራለት ሌንጮም አብይ ጡረታ ባይቆርጥለት ምን ይሆን ነበር?፡ዳውድ እንኳን ብልህ ነው ጎበዝ ሲራራ ነጋዴ ነበር ይላሉ ኤርትራም እያለ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182334
Previous Story

የአብይና የነ ደመቀ ፍጥጫ | “ወደዳችሁም ጠላችሁም በድሮን አፈርሰዋለሁ” ዐብይ | “ያንተ ብልፅግና ይፍረስ ” ደመቀና መላኩ |Ethio 251 ኢትዮ

Fekadu ethiopian Point
Next Story

ሽምግልናና ድርድር ብሎ ነገር የለም! ጦርነቱ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ስራ-አስፈጻሚ የሆነውን የአቢይ አህመድ አገዛዝንና ግብረ-አበሮቹን በማስወገድ ፍጻሜ ማግኘት አለበት!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop