አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት በገዢው ፓርቲ ተላልፏል ያለውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ። ውሳኔው፤ የአማራ ህዝብን “ያለ ተከላካይ ለዳግም ወረራ እና ጥቃት የሚዳርግ ነው” ሲል ፓርቲው ነቅፏል።
አብን በጉዳዩ ላይ ያለውን ተቃውሞውን ያስታወቀው፤ ወቅታዊ ጉዳይን በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 26፤ 2015 ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። ፓርቲው በዚሁ መግለጫው፤ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት ያህል አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደው የአብን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከተወያየባቸው “አንኳር ጉዳዮች” መካከል አንዱ የልዩ ኃይል ትጥቅ ማስፈታትን የተመለከተው አንዱ እንደሆነ ገልጿል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ ይታከልበታል]
ተጨማሪ ያንብቡ:  በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ በቋሚ ሲኖዶሱ አማካኝነት ድንገተኛ ስብሰባ ተቀመጠ | በፓትሪያርኩና በማህበረ ቅዱሳን ዙሪያ ይመክራል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share