November 4, 2022
2 mins read

“የታሪክ መዛግብት ሲፈተሹ ወልቃይት ማንነቱም ክብሩም አማራ ነው” መምህር ታየ ቦጋለ

313872430 1952415894933395 8618163750506169882 n

313872430 1952415894933395 8618163750506169882 nሁመራ: ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአሸባሪው ወያኔ የተከዳበት ጥቅምት 24 በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ታስቧል፡፡

የሰማእታቱ ቀን በታሰበበት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ቃብትያ ተገኝተው ስለ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ሕዝብ ሐሳባቸውን የሰጡት መምህር ታየ ቦጋለ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይ ሕዝብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጥቅምት 24ን አንረሳውም፣ ወልቃይትንም ብረሳሽ ቀኝ ትርሳኝ ያሉት መምህሩ በጋብቻ የተዛመደውን፣ ትምህርት ቤት የሠራውን፣ ድንበር ሲጠብቅ የነበረውን ሠራዊት መካድ የማይረሳ ነው ብለዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊትን የካዱት ግፈኞች እና ጨካኞች መኾናቸውንም አንስተዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊትን ሲክዱ ሕዝብ እና ኢትዮጵያን ወግተዋልም ነው ያሉት፡፡ የመከላከያ ሠራዊት ደም ፈስሶ አልቀረም ብለዋል፡፡

የታሪክ መዛግብት ሲፈተሹ ወልቃይት ማንነቱም ክብሩም አማራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ለ30 ዓመታት የተጫነበትን በዓለም ታሪክ በመራራነቱ ሊመዘገብ የሚችልን መከራ አስወግዶ በመስዋእትነቱ ማንነቱን አስከብሯል ነው ያሉት፡፡

ወልቃይት ኢትዮጵያውያን ደም የከፈሉባት ናት ያሉት መምህሩ ወልቃይት በጠላት እጅ ተይዛ ቢኾን ኖሮ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ይሰጡን ነበርም ብለዋል፡፡ኢትዮጵያም አደጋ ውስጥ የምትወድቅበት እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡ ወልቃይት ሳትደፈር የቆዬች፣ በትግል ጸንታ የኖረች ናትም ብለዋል፡፡

ከእውነት ፈላጊዎች እና ከተገፉት ጋር የሚቆሙት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ብለን አብረናችሁ እንቆማለንም ብለዋል መምህሩ፡፡

በታርቆ ክንዴ

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

https://fb.watch/gBJZ5xgM6U/

1 Comment

  1. መምህር ታየ ጊዜውን ሳያይ ከመጣው ንፋስ ጋር አብሮ የማይነፍስ እንዳንተ አይነት ዜጋ ያብዛልን። የሀይማኖት አባቶችን ቦታ ተክተህ ለተጎዳው ታዝናለህ የተጣመመውን ታቃናለህ ትልቅ ሰው ነህ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

haile larebo
Previous Story

ስለድርድሩ ባነሣሁት ነጥቦች ላይ ነቀፋም፣ ኂስም ሲነሡ ዐያለሁ – ፕሮፌሰር ኀይሌ ላሬቡ

Moresh
Next Story

ለዘላቂ ሰላም ትክክለኛ የዐማራ ሕዝብ ወኪል ተደራዳሪ ሆኖ እንዲቀርብ ማመቻቸት ግድ ይላል!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop