October 24, 2022
9 mins read

የክፉዎች ፍልሰት ይሁን (Let Exodus of Evil be) – ሰማነህ ታ. ጀመረ-ዖታዋ፤ ካናዳ፤

ጥቅምት 14, 2015

በሰባዎቹ የጀመረው የፈላሻ ሙራ ወደ እስራኤል ፍልሰት እስካሁን አልተጠናቀቀም። ፍልሰቱ የተከናወነበት መርሃ ግብር ‘ዘመቻ ሙሴ’ (Operation Moses) ተብሎ ነበር። መንፈሳዊ ፍልሰት ስለነበር ሁሉም ተቀብሎታል።

እነዚህ ወገኖቻችን በሃይማኖት ምክንያት ይውጡ እንጂ ኢትዮጵያዊነታቸውን አዝለው ይዞራሉ። ኢትዮጵያ ስትነካ ይቆጣሉ፤ ስትደሰት ይደሰታሉ፤ ስታዝን ያዝናሉ፤ ስትጠቃ በ ጭት ዘብ ይቆማሉ።  በትግራይ በተነሳው ጦርነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው ለመዋጋት የኢስራኤልን መንግስት ፈቃድ እስከመጠየቅ ደርሰዋል። የቁርጥ ቀን ወገኖች ናቸው።

በአንፃሩ ከኢትዮጵያ ከአብራኳ የፈለቁ፤  በሃብቷ የተማሩና የበለፀጉ፤ ልጆቸ እያለች ያንቆለጳጰሰቻቸው ወያኔ የተባሉ የትግራይ ልጆች በዓለም አደባባይ ውድቀቷንና ስቃይዋን አብዝተውባት አይተናል።  እዚህ ላይ ወያኔ፤ ትህነግ፤ ሕወሃት በሚል መጠሪያ ብዙ ሰው ይጨነቃል። ለዚህ ፀሐፊ ግን ሁሉም የአንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች እንደሆኑ ስለሚአምን  ብዙ አያስጨንቀውም። አሳማን ምንም ዓይነት የከንፈር ቀለም ቀብተን ለማቆነጀት ብንሞክር ያው አሳማነቱን አይቀይረውም።

ወያኔም ሆነ ሕወሃት የውጭ ጠላት ሊአደርገው የማይችለውን ደባና ተንኮል በኢትዮጵያ ላይ ፈፅሟል። ለሃምሳ ዓመታት ኢትዮጵያን አድምቷል። ንብረቷን ያለገደብ ዘርፏል። ሕፃናትንና አዛውንቶችን በውጊያ አስጨርሷል። ዘግናኝ የሆነ የዘር ፍጅት ፈጽሟል። የሰባ ዓመት መነኩሲትና ለአቅመ ፍሬ ያልደርሱ እህቶችንና እናቶችን ደፍሯል። የጤና፣ የመብራት፤ የስልክ፤ የትምህርት፤ የመንገድ፤ የፋብሪካ የማህበራዊና የኢኮኖሚ አውታሮችን በግፍ ዘርፏል። መሸከም ያልቻለውን አውድሟል። ፋሽስት ኢጣልያ ያላደረገውን ወያኔ ፈጽሟል። የፈፀሙትን ግፍ ከመዘርዘር ያልፈፀሙትን መጥቀስ ይቀል ይሆናል።

ሌላው ቢቀር ጣሊያን መንገድና ድልድይ ሰራ እንጂ አላፈረሰመ፤ መነኩሲት አልደፈረም፤ የማረከውን አልጨፈጨፈም። ይህን የፈፀመው ይሉኝታቢሱ ወያኔ ነው። ከኢትዮጵያ የቀረውና የሚቀርበት ነገር የለም። ኢትዮጵያዊነቱን አሟጦ ጉድጓድ ከቷል። ይባስ ብሎ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር የለችም፤ ካለችም መውደም አለባት ሲል ዘምቷል። ከ110 ሚሊዮን  በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳዷል። ኢትዮጵያን በማዋረድ፤ በማውደም የእፉኝት በሐሪውን ስላሳየ የኢትዮጵያዊነት ስብዕናን አያሟላም።

ለትግራይ ነፃነትና ለትግራይ ሕዝብ ሕልውና እታገላለሁ እያለ የራሱን ሕዝብ በመንደርና በቀየ ሸንሽኖ ቁምስቅሉን አሳጥቷል። ለሰላሳ ዓመታት ሴፍቲኔት የተባለ መርሃ ግብር ዘርግቶ  ሕዝቡን  ሴፍቲውን አሳጥቶ ገዝቷል። የእርዳታ እህል ተቀባይ አርጎ በድህነት ሲአሰቃየው ኖሯዋል። በአንፃሩ ቡድኑ ከኢትዮጵያና ከትግራይ ሕዝብ በዘረፈው ሃብት እራሱን፤ ቤተሰቡን፤ ዘመዱን፤ በዓዳን ጓዶቹንና ጠበቆቹን በገንዘብ አንበሽብሿል።

በዘረፈው ሃብት በአሜሪካ ‘ተጋሩ ኢንቨስትመንት ቡድን’ (Tegaru Investment Group)  ብሎ ባቋቋመው ድርጅቱ አማካይነት የተንደላቀቀ ኑሮውን እያጧጧፈ እንደሆነ ያለሃፍረት  በቅርቡ አስመርቋል። ለዚህም በታሕሳስ 2014 መጨረሻ በካሊፎርኒያ፤ ሎሳን ጀለስ ከተማ የመሰረተውን የተጋሩ መንደር በሚል የገዛውን ሕንፃና መሬት ለደጋፊዎቹ አስጎብኝቷል። የትግራይ ሕዝብ ግን የሚጠጣው ውሃና የሚበላው አጥቶ በለስ እየተመገበ ይኖራል።

ወያኔዎች ከድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉሮሮ እየነጠቁ በሃብታም ሃገር የራሳቸውን ከተማ እና መኖሪያ እየገነቡ ከሆነ በግልጽ ኢትዮጵያዊነታቸውን አራግፈው ጨርሰዋል ማለት ነው። እነዚህ ክፉና የጊንጥ በሐሪ የተላበሱ ናቸው። ለኢትዮጵያም፤ ለትግራይም ለዓለምም የሚጠቅሙ አይደሉም። ስለሆነም ‘የክፉዎች ፍልሰት’ የሚል  መርሃ ግብር ቀርፀን ከኢትዮጵያ ወደ ሎሳንጀለስ ልናስተላልፋቸው ግድ ይላል። ወያኔ ከኢትዮጵያ ጋር የሚአመሳስለውን ስነምግባር፤ በሐሪና ስብዕና አሟጦ ጨርሷል። የኢትዮጵያ እዳነት እንጅ ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነት የለውም።

ይህ የአሸባሪ ቡድን (ሕዝብ አላልሁም) ከሃገራችን ይውጣ። ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዝንተ ዓለሙን ሲአልቀስ ይኖራል እንዲሉ፤ ወያኔ የሚባል አጋም ኢትዮጵያን በበቂ አስለቅሷል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቡድን ጋር ሕጋዊ ፍች በማድረግ ስርዬትን ታግኝ። ምስኪኑ የትግራይና የኢትዮጵያ ሕዝብም ሸክሙ ይቅለለው። ከተሸከሙት የዓለም ባንክ (WB) እና የዓለም ገንዘብ ተቋም(IMF) እዳ  ሸከም  በላይ የመሸከም አቅም የላቸውም። ወያኔ የሕዝብና የአገር ጀርባን በበቂ አጉብጧል። ከዚህ ዕዳና ፍዳ የሚገላገሉበት መፍትሔ አንድ ነው። ይህም ኢትዮጵያዊ አይደለንም የሚሉትን የትግራይ አሸባሪዎች ወደ አዘጋጁት የሎሳንጀለስ ቀያቸው እንዲፈልሱ እንፍቀድላቸው።

አሜሪካም በገቢር፤ በበሃሪ ትህነግን ስለሚመስሉና በአምሳላቸው የፈጠሯቸውም ስለሆነ አንቀበልም አይሉም። እነርሱስ ቢሆን ከእንግሊዝና ከአውሮፓ ፈልሰውና የሰው ሃገር ወረው ሰው ሆነው አይደል ዓለምን ዓለማችንን የሚአባሉት። አሸባሪው መለስ “መንገዱን ጨርቅ ያርግላችሁ” እንዳለው ወደ ሎሳንጀለስ የሚአደርጉትን ፍልሰት ‘የክፉዎች ፍልሰት’ በሚል መርሃ ግብር  ፍልሰታቸው ይመቻችላቸው። ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ፍችና ግልግል አይኖርምና ይፍለሱ። ኢትዮጵያም ከአመርቃዡ የመከራ ምጧ ትገላገል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን  ይባርክ፤

ሰማነህ ታ. ጀመረ-ዖታዋ፤ ካናዳ፤

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop