September 18, 2022
4 mins read

ኤርትራዊው ጄ/ል ስብሃት ኤፍሬም፡- አሁን ላይ ስላለው ወቅታዊ በሃገራዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አስመልክተው በሚገርም አማርኛ ያስተላለፉት መልእክት

307489131 831079798346800 7541339490424483233 n

307489131 831079798346800 7541339490424483233 nየቀድሞው የኤሪትሪያ መከላከያ የአሁኑ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም ይናገራሉ!

“ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ካለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!

የኢትዮዽያ መፍረስ ቀድሞ የሚጎዳት ኤርትራን ነው! እኛም ይህንን በመረዳታችን በኢትዮዽያ መቀጠል የማያወላውል አቋም ያላቸውን ወጣቶች ያለንን ወታደራዊ ክህሎት ለማካፈል ፈቃደኛ በመሆናችን የሚከፋ ከአለ የኢትዮዽያን መፍረስ የሚናፍቅ ብቻ ነው።

ከጥንት ጀምሮ ‘በኢትዮዽያ መቀጠል የማያወላውል አቋም አለው’ ተብሎ ከሚታመንባቸው ብሔሮች መካከል ግንባር ቀደሙ «የአማራ» ብሔር ነው።

ከነፃነት ኤርትራ በፊት በትጥቅ ትግሉ ወቅት የአማራ ብሄር አባል የሆነ ወይም በእናቱ ወይም በአባቱ የአማራ ዘር ያለበት ኤርትራዊ ሳይቀር የኤርትራን ከኢትዮዽያ መለየት ፈፅሞ የማይቀበለው መሆኑን ስለተገነዘብን ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል በአማራ ህዝብ ላይ ብዙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሰርተናል። በወቅቱ ትግሉን ውጤታማ ከደረጉልን ቁልፍ ስልቶች መካከል አንዱ ነበር።

ሆኖም ግን በቅርቡ ሁለቱ ሀገራት በዶ/ር አብይ ምክንያት ዳግም ሲገናኙ በመጀመርያ በአፋጣኝ ኢንዲታረም ያደረግነው ፤ ለትግሉ ስኬታማነት ለሰራነው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በይፋ ይቅርታ መጠየቅና «አማርኛ» ቋንቋ ኤርትራ ውስጥ በሚገኙት ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንዲሰጥ መወሰን ነበር፤ ተግባራዊ አድርገነዋል።

በመሆኑም አሁን በወያኔ የሽብር ድርጊት በቀጠናው በተከሰተው የሰላም መደፍረስ ምክንያት በተለይም ሱዳን፣ ኢትዮዽያንና ኤርትራን በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከኢትዮዽያ ጋር ከሚያዋስነን የአማራ ክልል ህዝብ ጋር በመተጋገዝና በመረዳዳት እየሰራን ነው።

የእኛ እቅድ የቀጠናውን ሰላም በጋራ ለመጠበቅ በአዋሳኝ ከሚገኘው ከአማራ ክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመተጋገዝ በሱዳን ኮሪደር የሚገቡ ማናቸውንም ፀረ-ሰላም የውጭ ኃይሎች መከላከል እንጁ በኢትዮዽያ የውስጥ ጉዳይ ፈጽሞ መግባት አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “ፍትህ ፍትህ” ሲሉ ስለፍትህ ሲጮሁ ዋሉ

ይህንን ተግባራዊ ስናደርግ በወያኔ ስርዓት በሴራ ፖለቲካ ተጠልፎ የተዳከመውን የአማራ የፀጥታ አካላትን ወታደራዊ ክህሎታችንን እና ልምዳችንን በማካፈል በቀጠናው ጠንካራ አቋም ያለው አንድነት መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ፤ ለኢትዮዽያ ቀጣይነት የማያወላውል አቋም ያላቸውን የአማራ ወጣቶች ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ በአሉበት ስፍራ ወይም ወደ ኤርትራ በመምጣት ወታደራዊ ክህሎት እንዲኖራቸው እናግዛቸዋለን። ” ብለዋል::

ነጋሪት

2 Comments

  1. ትክክል መናገር ጥሩ ነው። ወያነው ወደ ቁልቁለት ከከተተው ኣንዱ ምክንያት ውሸት ነው። ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ብትምህርት፡ ፖሎቲካ፡ ወታደራዊ ሳይንስ፡ ቁጠባ ብሁሉ ዘርፍ ብቁ ሰው ነው። እንደተባለው የተዛባ ንግግር ሊናገር ኣይችልም። ከሌላ የኢትዮጵያ ህዝብ ለኣማራ ብቻ ለይቶ ሊናገር ኣይችልም። የኤርትራ መሪዎች ኣንኳን ባልሆነ፡ በሆነ ነገርም ብዙ መናገር የማይወዱ ሚስጢሮኖች ናቸው።

  2. ተስፋይ ድጋፍ መሆኑ ነው? ባለፈው ቢቢሲ ወደ አስመራ ተጉዞ ጠቅላላ ህዝቡ ከ70 አመት በላይ ነው ብሎሃል ኤርትራ ካለው ኤርትራዊ ኢትዮጵያ ያለው ይበልጣል ተብሏል፡፡ የወደፊቷ ኤርትራ ምን ትመስልሃለች?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Tigray 1
Previous Story

የትግራይን እናቶች ከወላድ መካንነት ማዳን የጠ/ሚ አቢይ አህመድ መንግስት ታሪካዊ ሃላፊነት ነው!

Peace and reconcilation
Next Story

ለአቅመ አዳም ሳይደርስ የከሰመው የፕሮፌሱሩ የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር መድረክ ዲስኩር – ተዘራ አሰጉ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop