አሸባሪው ሕወሓት የአማራን ሕዝብ ከጎኑ እንዲሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ – ቀቢጸ ተስፋ

ከአማራ ሕዝብ ሂሳብ አወራርዳለሁ ያለው የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ዛሬ ላይ ደግሞ የአማራን ሕዝብ ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው የሴራ እንቅስቃሴ ቀቢጸ ተስፋ መሆኑን በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፖሊሲ ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገለጹ።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ አንተነህ መሉ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው ሕወሓት አማራ ክልል አካባቢ ያሉ የፖለቲካ ሁነቶችን በራሱ ዓላማ ለመጠምዘዝና ወደ ራሱ ሁኔታ ውስጥ ለመውሰድ የሚፈልግባቸው አማራጮችን እየሳየ ነው።

ቡድኑ ሕዝቡ ከእሱ ጋር እንዲሰለፍና በራሱ መንገድ እንዲሄድ የሚያደርጋቸውን ጥረቶችም እያሳየ ይገኛል። ይህ ቀቢጸ ተስፋና የትም የማያደርሰው ሴራ ነው።

እንደ ረዳት ፕሮፌሰሩ ገለጻ፤ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሕዝብ ላይ እያደረሰ የነበረው ግፍ የሚታወቅ ነው።

አሁንም ጦርነት እያካሄደ ባለባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል። ለሕዝብ አዛኝ ያልሆነ ቡድን ሕዝብን የትግል አጋር ለማድረግ መሞከሩ ተስፋ የለሽ ያደርገዋል።

ከዚህ ቀደም ከአማራ ሕዝብ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን ባሉበት አንደበት ዛሬ ደግሞ ከአማራ ጋር ጸብ የለንም ሲሉ ይደመጣል።

ነገር ግን በተጨባጭ ከዚህ ቀደም በደረሱባቸው አማራና የአፋር አካባቢዎች ያደረሱት ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እጅግ ዘግናኝ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ቁስል ሳይሽር ሌላ ጥፋት ለመፈፀም ሦስተኛ ዙር ወረራ በመፈጸም ይህንኑ የግፍ ሥራቸውን ተያይዘውታል። ይህ በሆነበት ሁኔታ ጸብ የለንም የሚለው ፕሮፓጋንዳ «ዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ» ዓይነት ቀልድ ነው።

ሕወሓት ወደዓላማው የሚያሻግረውን መንገድ አሊያም አንድ ግብ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ዕድል የመጠቀም ሁኔታን በሰፊው የለመደ ነው፤ ገና በትጥቅ ትግል በነበረበት ወቅት እንኳን ለሰላማዊ ውይይት የጠራቸውን የሌሎች የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በጅምላ በመጨፍጨፍ ጭካኔውን በተግባር ያሳየ፣ በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን የመፍታት ልምድ የሌለው ቡድን ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምዕራብ ጎንደር የገጠር ቀበሌዎች የቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል:

አሁንም በዚህ ደረጃ መምጣቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ የሚደረጉ የሰላም ጥሪዎችን ሲያበላሽ የከረመና አሁንም ትግራይ ውስጥ ያለውን ቆይታ ለማራዘም በሕዝቡ ዘንድ የተጠላ መሆኑ እየታወቀ ሕዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ መሞከሩ ተስፋ መቁረጡን ያሳያል ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓት በማጭበርበር በኩል በመጥፎም ይሁን በጥሩ ይጠቅመኛል ያለውን ለመጠቀም መሞከሩ የተለመደ ባህሪው ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህ የራሱን ፍላጎት ሊያሳካለት የሚችለውን ማንኛውንም ቀዳዳ የመጠቀም ባህሪው ከበፊት ጀምሮ የመጣ እንደሆነ አመላክተዋል። ሆኖም ግን ይህ አካሄድ እንደማይሳካለት ተናግረዋል።

ለትግራይ ሕዝብ ትልቅ ዋስትና ሊሆን የሚችልና በአካባቢውም ሠላማዊ የሆነ መረጋጋትን ለማምጣት በተከታታይ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው አሁንም ተጨማሪ ጥፋቶችን እየፈጸመ የሚገኘው አሸባሪው ሕወሓት፤ አሁን እየተከተለ ያለው አካሄድም መላ የጠፋበት ስለመሆኑ እንደሚያሳይ ነው ረዳት ፕሮፌሰሩ ያብራሩት።

የአማራና የትግራይ ሕዝብ ካላቸው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ ግንኙነት አንጻር የሕወሓት አካሄድ ጠቀሜታ የሌለው ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ፤ አካሄዱ ሁሉ የዜሮ ድምር የጥፋት አካሄድ ነው። ይህም ቡድኑን የትም አያደርሰውም ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ በሁለቱም ሕዝቦች ዘንድ በወጣቶችና ሕፃናት ላይ የሚያደርሰው ችግር ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ፤ እንደ አገርም ሆነ ለሕዝብ ቢያስብ ኖሮ ብዙ የሰላም አማራጮችና መንገዶች ይከትል እንደነበር ጠቅሰዋል፤ በሰጥቶ መቀበል መርህም ሆነ በሠላማዊ መልኩ የተጀመሩ የድርድር ጥረቶችን ተቀብሎ ገፍቶ መሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ከፍተኛ እንደነበርም ጠቁመዋል። ነገር ግን ሕወሓት ለአገርና ለሕዝብ ደንታ የሌለው ድርጅት መሆኑን የሚፈጽማቸው ግፎች ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ሕወሓት እያደረገ ያለው ሕዝባዊ ማዕበል የውጊያ ስልት ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል። ሕፃናትን በአጠቃላይ ትግራይ ውስጥ ያለውን ወጣት ሲያሰለጥንና ሲያስታጠቅ ነው የከረመው። ይህ አገር ተረካቢ ትውልድ እያሳጣ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለአብይ አህመድ መንግስት የፌደራል ፖሊሶች ነፍስ የዶሮ ነፍስ ነው ማለት ነው?

ገና በአፍላ ዕድሜ የሚገኙ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ በርካታ ሥራዎችን መሥራት የሚችሉ ትውልዶችን በእንዲህ ዓይነት የሕዝባዊ ማዕበል ጦርነት ማሳተፍ አስነዋሪና ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ያሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም የተኮነነ ድርጊት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ ነገር እንዲወገዝና ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚገባም ተናግረዋል። በዚህ ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ አገር ቤት ባሉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ዘንድ ተገቢ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢፕድ

1 Comment

  1. ትግሬ ሞኝ ነው ማለት ነው? ይህን ሁሉ ግፍ ከፈጸመ በኋላ አሁንም የአማራን ልብ ሊያማልል ይዳዳዋል? አይ ቀልድ እይታቸው አጭር ነው፡፡ጎበዝ ተመስጌን ደሳለኝና አቶ ታዲዎስ ታንቱን አንርሳቸው፡፡ አይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን ያፈረሱ በኢትዮጵያውያን ታክስ ከፋዮች ተንቀባርረው ሲኖሩ (ሌንጮ ለታ፤ዳውድ ኢብሳ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ዲማ ነገዎ እያለ ይቀጥላል እረ አቶ መራራ ጉዲናስ ከነሱ የተለይ ለዚህ አገር ምን አደረገ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share