በኦሮሚያ መስተዳድር ቄለም ወለጋ ዞን፤ ሮቢት ገበያ ወረዳ ለምለም ቀበሌ ውስጥ በአማሮች ላይ አዲስ ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል

ወለጋ አሁን አማራውን እየጨፈጨፉ ነው፡፡ ሕጻናትንና ሴቶችን ነው በብዛት የሚገድሉት ሰዎች እንደዚህ እያደረጉ ያሉት የኦህዴድ መንግስት ድጋፍ ስላላቸው መሆኑ መርሳት የለብንም ንጹሃን ዜጎችን ፡፡ እነዚ ያንን በማድረጋችው ትንሽ እንኳን አይጸጽታቸውም፡፡ ጀግንነት የሰሩ ይመስል ነው በአድናቆት የሚያወሩት

የአብይ መንግስት የተፈጸመው ጄኖሳይድ እየሆነ ያንን ለመሸፋፈን፣ የሞቱትን ቁጥር በመቀነስ የነዚህ ሰዎች ወንጀልን ለማሳነስ በመሞከር፣ የችግሩን አስከፊነት ለመደባበስ ነው እየሰራ ያለው፡፡
አራት ኪሎ ቁርጠኛ የሆነ፣ የሕዝብ ስቃይ የሚሰማው መንግስት ቢኖር ኖሮ ፣ ለችግኝ ተከላ ያለውን ቁርጠኝነት አንድ አስረኛ እንኳን፣ “ሰው መሞት የለበትም” የሚል ቁርጠኝነት ቢኖረው ይሄ ሁሉ ጄኖሳይድ አይኖርም ነበር፡፡
ጭፍጨፋው ነገም፣ ከሳምንት በኋላም ይቀጥላል፡፡ እነ አብይና ኦህዴዶች የፌዴራል መንግስቱን እስከተቆጣጠሩ ድረስ ፣ በሩዋንዳስ ቱትሲዎች ካክሮች(ትንኝ) ተብለው ይጨፈጨፉ እንደነበረው፣ አማራው በኦሮሞ ክል መጤ፣ ሰፋሪ፣ ነፍጠኛ ተብሎ መጨፍጨፉ ይቀጥላል፡፡
አብይ አህመድ የኦሮሞ ጽንፈኛ ታጣቂዎችን አደብ ከማስገዛት፣ ሰራዊቱን አማራ ክልል ልኮ ሰላማዊ ዜጎች ላይ፣ ፋኖ ላይ ነው ጦርነት የከፈተው፡፡
ወገኖች ከዚህ በኋላ አፈሙዙን ወደ አራት ኪሎ በማድረግ ነው በኦሮሞ ክልል ያለውን አማራውንም ሆነ ሌላውን ማህበረሰብ ማዳን የሚቻለው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቀረቡትን የምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ እና ምክትል ከንቲባ ሹመቶችን አፀደቀ

1 Comment

  1. ወለጋ እውቅ የሆኑ ኢትዮጵያን የሚወድ ልጆች ያፈራች ምድር ነበረች። አሁን እንሆ አሜሪካና አውሮፓ ላይ ተቀምጠው የሚያታኩሱ የዚሁ አካባቢ ተወላጆችንም አፍርታለች። መግደል የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። እኔ ብቻ ልኑር፤ እኔ ብቻ ልብላ የሚለው ፈሊጥ ከአራዊቶች የተወሰደ ነው። እኔ አንዳንድ ጊዜ ሳስብ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር ሃገር ውስጥ ያለችም አትመስለኝም። ልክ እንደ ልጆቿ እቃዋን ጠቅልላ የተሰደደች አለያም ዲቪ ደርሷት በቃኝ ብላ የወጣች ይመስለኛል። በምድሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ሰቆቃ በየጊዜው ይፈጸማል። ሃገሬው ደንዝዟል። መሪዎቹ ፈዘዋል። ጠ/ሚሩ ሲናር መስማት ያስጠላል። ፍሬ የለሽ የቃላት ክምር። በቅርብ እንዲህ አለ ” በ 27 ዓመት ያልነበረ ኦነግ ሽኔ አሁን ከየት መጣ? በወለጋ የሞተው አማራ ብቻ አይደለም። ወለጋ ስልክ ሲቋረጥ የሚጮህ የለም። ትግራይ ሲሆን ጫጫታ” ይህ አባባል ከሚዛን የወጣ ሰውን ከሰው የሚያበላልጥ አነጋገር ነው። ቀጥሎ ሲናገር ” ትግራይ በነበርንበት ጊዜ 300 የኦነግ ሸኔ ሰልጣኞችን አግኝተናል” እና ታዲያ ወያኔ ብልጥ ነዋ። ህዝቡ ተመሮ መንግስትን እንዲያሽቀነጥር ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑ እንዴት መረዳት ይከብዳል። ሺህ ጊዜ ሰራዊቱ ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጅ ነው እያሉ ከመልፈፍ ይልቅ ለምን መቀሌ ገብቶ ዋናው የተንኮል ቋት ወያኔን መደምሰስና ህዝቡን ነጻ ማውጣት አልተቻለም? የኦነግ ሸኔና የሌሎች አጥፊ ሃይሎች መሰረቱ ወያኔ ነው ተብሎ ከታመነ ለምንድነው ወሎ ላይ ጦር አስፍሮ ዝም የተባለው?
    የሃበሻው ፓለቲካ በአስለቃሽና አልቃሽ የተሞላ ትብታብ ነው። ፈጣሪ ሰላምን ያምጣ፤ በቃ ይበለን እያለ የግል ኑሮውን በሰላም ለመምራት የሚታገል የሌላው ሰቆቃ የራሱን ቤት እስካላንኳኳ ምንም የማይሰማው የደነዘዘ ፍጥረት ሆኗል። ጥቂቶች ሲታሰሩ፤ ሲገደሉ፤ ለሃገር ለወገን ብለው በጫካና በገደል ሲንገላቱ የእኔ ድርሻ ምንድን ነው የማይል ህብረተሰብ የሚጠብቀው ሞትና ስደት ብቻ ይሆናል። ከድንዛዜው ብዛት ሰው በዘሩ ተለይቶ ተመነጠረ እሳት ገቢያውን በላው ምንም ደንታ የለውም። እንጸልይ ይላሉ። በጭራሽ ጸሎት እንጸልይ አትበሉ። ጸሎትና ምልጃ የሃገር ሰላም የሚያመጣ ቢሆን ኑሮ ድሮ ገና ምድሪቱ እፎይ ባለች ነበር። ቤ/ክርስቲያን ለመስራት የድሃዎችን ቤት ከሚንድ ድውያን መካከል ምን አይነት ፈጣሪ ነው የሚቆመው? ያበድነው በጋራ ነው። የምንድነውም በጋራ አስበን አሰላስለን ስንስማማ ብቻ ነው። ስለሆነም የባለ ሥልጣን ዲስኩርም ሆነ የእምነት ሰው ነን ባዮች ልመና ህዝባችን ከመከራ አያወጣውም። ለጊዜውም ቢሆን ራስን አደራጅቶ ከሞት ለመትረፍ መሰልጠን፤ መታጠቅ ብሎም ግፈኞችን መፋለም አስፈላጊ ነው። ወለጋን ለመውረር የመጡ ፈጤዎችን መግደል ልክ እንደሆነ ይናገራል። እንዲህ ያሉ እብዶች ያሉበት ሃገር ነው። ሰውን በመግደል መሰልጠን የኦሮሞ ገዳዮች መፈክር ሆኗል።
    ባጭሩ የመንግስት የተጋነነ ወሬ፤ ፈጨናቸው፤ ገደልናቸው፤ ደመሰስናቸው የሚለው ሁሉ ፈጠራ ነው። ያን እኮ ሰራዊቱ ትግራይ ምድር ባለበት ጊዜም ሰምተነዋል። ጠ/ሚ “ወያኔ የተበተነ ድቄት ነው” ብለው ነበር። ወቸው ግድ ጉራ ሌላ ሥራ ሌላ ከተበተኑ እንዴት ሽዋ ሮቢት ድረስ ገቡ? የአሁኑም የኦነግ ሸኔ አማራ ጨፍጫፊዎችን አጠፋን ደመሰስን የሚሉን ለፓለቲካ ፍጆታ እንጂ አንድም እውነትነት የለውም። ወለጋ ትላንትም ዛሬም የደም መሬት። ዋ በህዋላ ኦሮሞ ነኝ ለሚሉትም ቢሆን ይህች ምድር እሾህ ትሆናለች። ግፍ ይዘገያል እንጂ ግፈኞችን መልሶ ይበላል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share