ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን በድጋሚ መሪ አድርጎ መረጠ

July 3, 2022

Birhanu 1ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ለመጪዎቹ ሶስት ዓመታት እንዲመሩ በድጋሚ ተመረጡ። በእርሳቸው የአመራር ስብስብ ስር ሆነው ለውድድር የቀረቡት አቶ ዮሐንስ መኮንን የፓርቲው ምክትል መሪ ሲሆኑ፤ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ደግሞ የፓርቲውን የሊቀመንበርነት ቦታ ተረክበዋል።

የፓርቲው አመራሮች የተመረጡት ዛሬ እሁድ ሰኔ 26፤ 2014 በተካሄደው የኢዜማ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ነው። ከትላንት ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚሁ የኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ 900 ገደማ ጉባኤተኞች መሳተፋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትዕግስት ወርቅነህ ገልጸዋል።

የፓርቲው ጉባኤተኞች በሁለተኛ ቀን ውሏቸው፤ ኢዜማን ለመምራት በዕጩነት ለቀረቡት ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዷለም አራጌ እንዲሁም የፓርቲውን ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች ለመያዝ ለተወዳደሩ ግለሰቦች ድምጽ ሰጥተዋል። በውጤቱም መሰረት ፕሮፌሰር ብርሃኑ 549 ድምጽ በማግኘት የኢዜማ መሪነት ስልጣናቸውን አስጠብቀዋል።

ከኢዜማ ምስረታ አንስቶ የፓርቲውን የምክትል መሪነት ቦታ ይዘው የቆዩት አቶ አንዷለም አራጌ 326 ድምጽ አግኘተዋል። ኢዜማን ለመምራት በዕጩነት የቀረቡት ሶስት ተወዳዳሪዎች የነበሩ ሲሆን ሶስተኛው ተወዳዳሪ አቶ ጸጋው ታደለ ራሳቸውን ከውድድሩ አግልለዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመሪነት በመቅረብ ብቸኛው የነበሩት አቶ ጸጋው ራሳቸውን ከውድድር ያገለሉት ምክትላቸው የነበሩት አቶ አየለ ዳመነ “የፓርቲውን ውስጥ መስፈርት ባለማሟላታቸው” ምክንያት ከውድድር ውጭ በመሆናቸው ነው። አቶ ጸጋው ከእሳቸው ጋር ምክትል መሪ በመሆን የሚወዳደር ግለሰብ እንዲመርጡ በፓርቲው የአንድ ሳምንት ጊዜ ቢሰጣቸውም ማቅረብ አልቻሉም።

ለፓርቲው መሪነት ተወዳድረው በተሸነፉት አቶ አንዷለም አራጌ ምትክ፤ አቶ ዮሐንስ መኮንን የኢዜማ ምክትል መሪ እንዲሆኑ ዛሬ በጉባኤተኛው ተመርጠዋል። አቶ ዮሐንስ ለተረከቡት ቦታ በሌላኛው ጎራ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት አቶ ሐብታሙ ኪታባ ነበሩ።

ፓርቲው ከመሪ እና ምክትል መሪ ባለፈ፤ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር፣ ጸሐፊ እና የፋይናንስ ኃላፊ ምርጫዎችንም አድርጓል። ኢዜማን በሊቀመንበርነት ለመምራት አምስት ጣምራ ዕጩዎች ለውድድር ቀርበው ነበር።

ከዕጩዎቹ መካከል የአሁኑ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ምክትላቸው ዶ/ር ጫኔ ከበደ ይገኙበታል። ዶ/ር ጫኔ 435 ድምጽ በማግኘት የፓርቲውን ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፤ አቶ የሺዋስ 238 ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል። የኢዜማ የጸሐፊነት ቦታቸውን ለማስጠበቅ የተወዳደሩት አቶ አበበ አካሉ 740 የጉባኤተኞች ድምጽ በማግኘታቸው በያዙት ኃላፊነት እንደሚቀጥሉ ተረጋግጧል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

2 Comments

  1. የነብርሀኑን ጥርስ የነቀሉበትን ጥልፍልፍ የሸር አሰራር አልፈህ ኢዜማን እንደማታድነው ከዚህ በፊት ጠቁመን ነበር አንዱ ስህተት ኢሳት የብርሀኑ ሚዲያ ላይ መቅረብህ ነበር እንደውም ገላግሎሀል ያለፈው ስቃይ ይበቃሀል አሁን እረፍት አድርግ ይህ የክፉዎች ስብስብ ካንተ ሰብአዊነት ጋር አብሮ አይሄድም

  2. ህብታሙ ኪታባን ፋና ቴሌቪዥን ላይ ከአንድ [የአጠያየቅ ስታይሉ] ብዙም ከማይመቸኝ ጋዜጠኛ ጋር ያደረግውን ቃለምልልስ አዳምጬ ነበር። ካወቀበት በወደፊት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ገንቢ ሚና መጫወት የሚችል፣ ተስፋ የሚጣልበት፣ የዘመነና የሰለጠነ ወጣት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለአቶ አንዷለም ድምጽ የሰጠውን ጉባኤተኛ ቁጥር ግምት ዉስጥ በማስገባት የፓርቲውን የውስጥ ልዩነት የማጥበብ ሥራ ይጠብቃቸዋል። ለዚህም የህብታሙም የአንዷለምም ትብብር ያስፈልጋቸዋል። የአቶ የሺዋስ አለመመረጥ ግን ትንሽ ግር ያሰኛል [ጨዋ አንደበቱ እና እርጋታው እጅግ ያስቀናኛል!]።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

w4545433
Previous Story

የህዝብን ጥያቄ መንግስት የጥያቄው ባለቤት ከሆነው ህዝብ በላይ አውቃለሁ ማለት አይችልም

birhanu
Next Story

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢዜማ መሪ ሆነው ስለተመረጡ እንኳን ደስ ያለዎት! (አንዱዓለም አራጌ )

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop