አንበሳን ለአመንቲ ?? (እውነቱ  ቢሆን)

አንበሳ ፋርማሲ የአገሪቱ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እድሜ ጠገብ የታሪክ አሻራችን ብቻ አይደለም፡፡በአይነቱ ብቸኛ የሆነ፣ በሀኪሞች ታዝዘው በባለሙያወች ተዋህደውና ተቀምመው ፈውስ የሚሆኑ የአያሌ በሽታወችን የሚያድኑ መድሀኒቶች መቀመሚያ ፋርምሲም ነው፡፡ ይህ አገልግሎቱ አንበሳ ፋርማሲን በአይነቱ ብቸኛ አድርጎት እስካሁን ድረስ ለህዝቡ ምትክ የለሽ የጤና አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል፡፤

ከጤና አኳያ ስለፋርማሲው ምትክ የለሽነት እኔ ራሴ ምስክር ነኝ፡፡ ይዞኝ የነበረውን የቆዳ በሽታ ብዙ ጥሬ ጥሬ ሳይሳካልኝ ቀርቶ መጨረሻ ላይ በሀኪም ትእዛዝ ከዚህ ፋርማሲ ተቀምሞ የተሰጠኝ መድሀኒት ነው ያዳነኝ፡፡ ይታያችሁ ለአዲስ አበቤ ሰው በተለይ ዛሬ ላይ ያህንንን ማጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፡፡

ህዝብ ሲጠቀም የሚያመው መንግስት፣ የህዝቡ ጤና ሲጠበቅ ህመም የሚሰማው መንግስት፣ የህዝቡ ሰላም መሆን የሚያሰጋው መንግስት ጸረ ህዝብነቱ፣ ተረኝነቱ፣ አድሏዊነቱ፣ ማናአለብኝነቱና በጥጋብ እብጠቱ ጫፍ ደርሷል፡፡ ፋርማሲውን አፍርሶ ኦቦ ጀርመን አመንቲ የተባለ ተረኛ  ባለሀብት ህንጻ ሰርቶ በማከራየት ቢዝነስ እንዲሰራበት ቦታውን ከአንበሳ ፋርማሲ ቀምቶ ለኦቦ አመንቲ ሊሰጠው እንደሆነ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡

በከተማዋ ውስጥም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ ኦሮሙማ የሚሰራቸው ጸረ ህዝብና ጸረ አገር አብሮ የማያኗኑሩ ስራወች ተዘርዝረው አያልቁም፡፤ ጥጋቡና ማንአለብኝነቱ እየባሰበት ሄዷል፡፡ መቆሚያም ያለውም አይመስልም፡፡ይህ ጥጋብና እብ ጠት ሊፈነዳ  ደርሷል፡፡ ፍንዳታውም ለብዙ ይተርፋል፡፡ እንኳን እንደዚህ በዘረኝነት መጠኑን አልፎ በከረፋና በከፋ የተግማማ የፖለቲካ ስርአት ቀርቶ በበሰለ ህዝባዊ አመራርም ቢሆን የህዝብ ብሶትና ግፍ ሞልቶ ከፈሰሰ የሚያቆመው የለም፡፡

አንበሳ ፋርማሲን አትንኩ፡፤ የህዝብ ጤና መጠበቂያ ምትክ የለሽ ፋርማሲ ነው፡፡ታሪክ ያለን ህዝብ ስለሆንና ታሪክም ስለምናውቅ  ስለፋርማሲው የታሪክ አሻራነት ተረኞችን ለማስረዳት አንሞክርም፡፡ ታሪክ ደግሞ በተረኝነት አይሻርም፡፡ አይቀየርም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ህዝብ ተጋድሎ፥ በተለያዩ ከተሞች የመንግስት መዋቅር ፈርሷል፥ የኢንተርፖል መምሪያ ሃላፊ ከሀገር ወጡ

4 Comments

  1. ውድ ውሸቱ ቢሆን፣ ” … ይዞኝ የነበረውን የቆዳ በሽታ ብዙ ጥሬ ጥሬ ሳይሳካልኝ ቀርቶ መጨረሻ ላይ በሀኪም ትእዛዝ ከዚህ ፋርማሲ ተቀምሞ የተሰጠኝ መድሀኒት ነው ያዳነኝ” ስትል፦ ህንጻና መድሃኒት መለየት እስኪያቅተው ድረስ ልብህ በጥላቻ እንደ ጠቆረ ያመለክታል። ወይ የአንበሳ ህንጻ ሲፈርስ ድንጋዩን ገዝተህ ተንተርሰህ ትተኛ!

    እውነት ግን፣ አንበሳ ፋርማሲ ሥፍራው ላይ አለ። ስንቱን ቀባጠርክ ልጄ! የነዛኸው ወሬ ከሁለት ዓመት በፊት ያረጀ ወሬ ነው፤ አንበሳ ፋርማሲ ዛሬም አለ፤ ወ/ሮ ፋሲካ ከበደን ስልክ ደውለህ ማረጋገጥ ትችላለህ።

  2. የታሪካዊ ቦታዎች መከበር ለሀገራችን ቅርስ ጠቃሚ ቢሆንም ብዙ ህዝባችንን የስራ እድልና ጠቃሚ ገቢ የሚያስገኙ ግንባታዎች ለመስራት የቆዩ ህንጻዎች ሁሉ ይጠበቁ ማለት አግባብ አይደለም ::በመሰረቱ የመጀመሪያው አንበሳ ፋርማሲ የነበረው ፒያሳ አሮጌ ፖስታ ቤት የነበረበት ቦታ ነበር:: https://www.facebook.com/heritageET/posts/in-history-top-image-is-of-the-first-pharmacy-in-addis-ababa-the-second-image-un/902528713508469/

  3. ይድረስ ለ Berale
    በፋርማሲነት መድሀኒት አስመጥቶ በመሸጥ ስራ ላይ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት መድሀኒቶችን ራሱ ቀምሞ ለህዝብ ጤና በማቅረብ የታወቀውንና የታሪክ ባለ አሻራውን አንበሳ ፋርማሲን አፍርሶ በተረኝነት ቦታውን ለኦቦ አመንቲ ህንጻ ሰርቶ ለመከራየት የንግድ ስራ ለመስጠት ጫፍ ላይ የደረሰው የተረኞቹ መንግስት ከድርጊቱ እንዲታቀብ የቀረበውን የእውነቱ ቢሆንን ሀሳብ የተቸህበት መንገድ እጅግ ያሳፍራል፡፡
    ህንጻና መድሀኒት መለየት ያቃተህ አንተ እንጅ ጸሀፊው ቢሆን አይደለም፡፡ ከዚህም ርካሽና ውሀ የማይቋጥር የተሳሳተ ትችትህ በተቸማሪ ጽሀፊውን ስጻደብ “ የአንበሳ ህንጻ ሲፈርስ ድንጋዩን ገዝተህ ተንተርሰህ ትተኛ! “” የሚል የወረደ ቃል መጠቀሙ አያስፈልግህም ነበር፡፡
    ግን ለእንሰሳ ስንቱን ይነግሯል?? እንደትስ እንደ ሰው እንዲያስብ መቀየር ይቻላል?? አንተ በተረኝነት የታወርክ ነህ፡፡ ወደ ቁም ነገሩና ወቅታዊ መረጃው ልመለስ፡፡
    በቅርቡ አንበሳ ፋርማሲ ቦታን ለተረኞው ኦቦ አመንቲ ለመስጠት ተወስኖ ፋርማሲው ለቅቆ እንዲወጣ በፌደራል ቤቶች አስተዳደር የታዘዘበትን መረጃ እንጥቀስ፡፤
    የፌደራል ቤቶች አስተዳደር ለፋርማሲው በ05/08/2014 ዓ.ም. በፃፈው ደብዳቤ፣ “የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 4 ጽ/ቤት የሚያስተዳድረው በአራዳ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 2 ቀበሌ 15 የቤት ቁጥር 158 የሆነው የንግድ ቤት ተከራይ መሆናችሁ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከቤቶች እና ይዞታዎች ማስከበር እና ማከራያ ዳይሬቶሬክት መጋቢት 30/07/2014 ዓ.ም በቁጥር 50/1/1/3377 በፃፈልን ደብዳቤ በተወሰነው ውሳኔ መሠረት ከሚያዚያ 1 /2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመካከላችን የነበረውን የቤት ኪራይ ውል ያቋረጥን መሆኑን እያሳወቅን፣ የተገለገላችሁበትን የቤት ኪራይ፣ የመብራት እና የውሃ ፍጆታ ሂሳብ አጠናቃችሁ በመክፈል ቤቱን እንድታስረክቡን እናሳስባለን” ብሏል፡፡
    አንተ ይህንን አታውቅም አንልም፡፡ ምክንያቱም የተረኞቹ ቤተኛ ነህና ፡፤ ቢያንስ ተከፋይ ነህና፡፡ አመለካከትህም ያ መሆንህን በእርግጥ ያመላክታልና፡፡
    እናስ አሁን ሀቁ ተገለጠልህ ወይንስ እዚያው በተረኝነቱ ቀዘፋ ላይ ነህ???

  4. Deegone Moretaw
    ፓስተር መስልከኝ፡፤ ጥሩ ነው ፓስተርነት፡፤
    አንተ የምትለው “”የስራ እድልና ጠቃሚ ገቢ ለማግኘት”” ተብሎ የታሪክ አሻራ ናቸው የተባሉ ቦታወች መፍረስ አልለባቸው ነው፡፡ ትክክል አይደለህም፡፡ የታሪክ አሻራ የተባሉበት በቂና አሳማኝ ምዘናወችንና ታሪኮችን መሰረት ያደርገገ ፍረጃና ምዘና ተከትሎ ስለሆነ አንተ ፓስተሩ ያልከው ያንን ምዘና ሊሽረው አይችልም፡፤ ታሪክ ታሪክ ነው፡፡ አሻራም አሻራ ነው፡፡ ታሪክንና የታሪክ አሻራነት ትርጉምና ጥቅም ለማያውቅ ቀላል ይመስላል፡፡ በተለይ በተረኝነት ለታወረ ጉዳዩ ምኑም አይደለም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share