የዱባና ቅል አበቃቀል ለየቅል -ጥሩነህ

ብሶታችን እውነት ነው: ተስፋ ማጣት ደረጃ ላይ ደርሰናል ስለሆነም ብዙ እንመኛለን: ምኞታችን ግን ከእሳት ወደ እረመጥ እንዳይሆን በተባሰ ህሊናችንም ማየት መቻል አለብን:

ዛሬ HR6600 ይለፍ የሚሉ ሰዎች አፍ አውጥተው ሲናገሩ መስማት ያሳምማል: የጠሉት የሚያልፈውን መንግስት ብቻ ሳይሆን ዘለዓለማዊቷን ኢትዮዽያንም ነው:: ከጤነኛ አእምሮ የሚሰነዘር አይደለም:

በፌደራልም ሆነ በአማራው መንግስታት ላይ ያለን ብሶት እንዳለ ሆኖ በሃገር ላይ ግን የጋራ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል: ጭፍን ጥላቻ ሃገር ማዳን አይችልም:

በሰዎች ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን በሃገራችን ግን ተስፋ አንቆርጥም: አንድ ያላት እንቅልፍ የላት ነውና በንቃት ልንጠብቃት ይገባል: ፅንፈኞች እንዲያፈርሷት አሳልፈን አንሰጥም: ቅሬታችን ብሶታችን እንዳለ ሆኖ የሃገራችንን ጥቅም ለማስከበር እስከሆነ ድረስ ከማንስምማቸው ሰዎችም ጋር አብረን እንሰለፋለን: ከኢትዮዽያ ጠላቶች ጋር አንሰለፍም:: ለግብፅ አናጎነብስም:ለአሜሪካ አናጎነብስም: ለወራሪው ትግሬ እፎይታ አንሰጥም:: ሰወች እየሞቱ ነው ሃገርም እንዳትሞት መጠንቀቅ ሃገራዊ ፍቅር ነው::

ያ ማለት ግን መንግስትን እንደጥፋቱና ድክመቱ አናውግዝም ማለት አይደለም: እንዲታረሙ ወይም በተሻሉ ሰወች እንዲተኩ መታገልን ይጠይቃል:: መወንጀል ብቻ መፍትሄም ስላልሆነ ተለዋጭ/የተሻለ ሃሳብንም ማቅረብ መልመድ ያስፈልጋል:: ከሁሉም በላይ የችግራችን ሁሉ መሰረት የሆነው ህገመንግስት እንዲቀየር አብክሮ መስራትና ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል::

በየጊዜው ወጥሮ የሚይዘን አጀንዳዎችን ጠላቶቻችን ይወረውሩብናል: አለመቀበል ግን የኛ ፅኑ ጥንካሬ መሆን አለበት:

የማይተማመን ጏደኞ በየወንዙ ይማማላል እንዲሉ በመንግስት ድክመትም ይሁን ክፋት በሃገራችን ላይ ያለን አንድነታዊ አቋም ወደመሃላ አይወስደንም ምን ጊዜም ኢትዮዽያ ከሁሉም በላይ ናት:

በመንግስት ተስፋ መቁረጥ በኢትዮዽያ ተስፋ መቁረጥ አይደለም: እንዲያውም አንዳንድ ባለጊዜዎች ይህን እንድናደርግ ይጥራሉ: ከአሜሪካ እብሪት ከወያኔ ጥላቻ ከኦነግ አሽከርነት ጋር ሊደምሩን ይፈልጋሉ: እኛ ኢትዮዽያ ስንል ሌላ ተረት ትረት ይጫወታሉ: ለዚህም HR6600 እንዲያልፍ ሁሉም አክራሪዎች የተግባርአንድነት እያሳዩ ነው: መልሳችን በኢትዮዽያ አትምጡብን ነው::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕገወጥነትና ብልግና የነገሰባት የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ “ብልጽግና” ኢትዮጵያ ወደ የት እያመራች ነው? - አክሎግ ቢራራ(ዶር)

የዋሆች ወይም ተንኮለኞች ይህን የሴኔት ውሳኔ መቃወም ከመንግስት ጋር መቆም ነው ሲሉ ሌሎችን ሊያማልሉ ይጥራሉ: ይልቁንም ይህን ውሳኔ አለመቃወም ከወራሪው ትግሬ ከኢምፔሪያሊስት ሃይሎችና ኮፈዳ ተሸካሚወቻቸው ጋር መቆም መሆኑን ብግልፅ ልንነግራቸው ሃገራዊ ግዴታ አለብን:

ወራሪዎች ዘረኞች ባለጊዜዎች ነገ አይኖሩም ውድ ኢትዮዽያ ግን ሁልጊዜም ትኖራለች::

ብዙ ብሶቶች አሉን

  • ዛሬም ሰዎች እየተገደሉ ነው: ሞትን ከመለማመዳችን የተነሳ ከነፍስ ይማር ባሻግር ደንዝዘናል:
  • ወንጀል ፈፃሚወች ተይዘው ለፍርድ አይቀርቡም ይህም በተራው ወንጀል መስራትን እያባባሰ ነው:
  • መንግስት በጠቅላይ ሚንስቴሩ በኩል ለጆሮ ግባት ያላቸውን ንግግር ከማድረግ ባሻገር የሃገራችንን ችግር ለመፍታት አቅሙ/ ፍላጎቱ የለም:
  • ህዝቡ የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ታማኒነት ከትልቅ ጥያቄ ውስጥ እስግብቷል: ለማስተባበል የሚሆን ስራም በተግባር ስለማይታይ ጥርጣሬው ይቀጥላል: ይህም ማለት ቢያንስ መንግስታቸው የመጀመሪያውን የመንግስት ተግባር የሰወችን ህይወት የመጠበቅ ችሎታ/አቅም/ ፈቃደኝነት የለውም ማለት ነው::

* ባጭሩ መንግስት አድላዊ ነው ሞትም ብዙ የሚያሳስበው አልሆነም

  • በዚህም በወያኔ ስልጣን በሁዋላ የነበረው የህብረት ገመድ ወደመበጠሱ እየቀረበ ነው:

ይህ ሁሉ እንዳለ ግን ሃገራችንን ለአንድ ፓርቲ ወይም መንግስት ስጥተን እጃችንን አንሰበስብም ሃገሪቱ የኛም ናትን::

ነገ በሚከስሙ ባለጊዜዎች ማኩረፍም ሆነ አያገባኝም ማለት አይቻልም:

ቤቱ ሲቃጠል ትኋኑን ተገላገልነው የሚለው አባባል የኛ አይደለም። እውነትም ጠቅላይ ሚኒስተሩ የኛ ናቸውን? ብለው ለሚጠይቁ መልስ ማግኘት እያስቸገረ አንዳለ ግልጽ ነው። ግን ኢትዮጵያ የኛ እንደሆነች አንዳፍታም ቢሆን አንጠራጠርም። ኢትዮጵያ የትቂት ግለሰቦች፤ ቡድኖች ወይም ፓርቲ የግል ንብረት አይደለችም እንደሚያልፉም እናውቃለን። ስለዚህ የምንወዳትን ሃገር በነሱ ምክንያት ለሞት አንዳርጋትም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሀገርን ከውድቀት ሕዝቡን ከልቂት የመታደግ ጥሪ - ሽማግሌው ነኝ ከሁስተን ቴክሳስ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share