ኢትዮጵያ እየከሳች አላሙዲ በሃብት እየወፈሩ ነው፤ የዓለማችን 61ኛው ቢሊየነር ሆኑ

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የዓለማችን የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ በየዓመቱ የዓለማችንን ቢሊየነሮች ደረጃ የሚያሳውቅበትን መረጃ ይፋ አደረገ። ባለፈው ዓመት የዓለማችን ሁለተኛው ሃብታም የነበሩት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ የዓለማችን አንደኛ ቢሊየነር ሲሆኑ የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከምበርግ 21ኛው የዓለማችን ቢሊየነር ሆኗል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በመሬት ነጠቃ የሚከሰሱት ሼህ መሀመድ አላሙዲ የዓለማችን የሃብታምነት ደረጃቸው ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ አምና ከነበሩበት የ65ኛ ደረጃ 4 ደረጃዎችን በማሻሻል የዓለማችን 61ኛው ሃብታም ሆነው በመጽሔቱ ተቀምጠዋል። እንደ ፎርብስ ገለጻ የ8 ልጆች አባት የሆኑት በአባታቸው የሳዑዲ፤ በእናታቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆኑት አላሙዲ $15.3 ቢሊዮን አላቸው።

ከሳዑዲ አረቢያ ሃብታሞች መካከል ሁለተኛው የሆኑት አላሙዲ የወያኔ/ኢሕአዴግ ደጋፊ ከመሆናቸውም በላይ፤ ከስር ዓቱ ጋር በፈጠሩት ስር የሰደደ ወዳጅነት በአድልዎ አብዛኛው የኢትዮጵያ ወሳኝ የንግድ ተቋማት በርሳቸው ስር እንዲያዙ ትልቅ ውለታ እንደተዋለላቸው በተደጋጋሚ እንደሚተቹ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሼኩ በነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ቢሆኑም በተለይም የኢትዮጵያን ወርቅ በእርሳቸው ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የሰውዬው ሃብት ከእለት ወደ ዕለት እንዲጨምር አስችሎታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

የፕላኔታችን 10ሩ ቢሊነሮች የሚከተሉት ናቸው።

1ኛ. ቢል ጌትስ 76 ቢሊዮን ዶላር
2ኛ. ቻርሎስ ሳሊም ሄሉ 72 ቢሊዮን ዶላር
3ኛ. አማሪኮ ኦርቴጋ 64 ቢሊዮን ዶላር
4ኛ. ዋረን ብፌት 58.2 ቢሊዮን ዶላር
5ኛ. ላሪ ኤልሰን 48 ቢሊዮን ዶላር
6ኛ. ቻርለስ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
7ኛ. ዳቪድ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር
8ኛ. ሼልደን አንደርሰን 38 ቢሊዮን ዶላር
9ኛ. ክርስቲ ዋልተን እና ቤተሰቦቿ 36.7 ቢሊዮን ዶላር
10ኛ. ጂም ዋልተን 34. 7 ቢሊዮን ዶላር

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወታደሮች ተላልፈው ተሰጡ፣300 ሰዎች ራሳቸውን ስተው ተገኙ፣ቄሮ የዘጋው መንገድና መንግሥት ያገደው አካውንት"72 ሰዓት ብቻ"ጠቅላይሚንስትሩ

የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በ28.5 ቢሊዮን ዶላር 21ኛ፣ አላሙዲ በ15.3 ቢሊዮን ዶላር 61ኛ፣ ቸልሲ ስፖርት ክለብ ባለቤት ኢብራሞቪች በ9.2 ቢሊዮን ዶላር 137ኛ ሆነዋል።

2 Comments

  1. የኢትዬጰያ ሀብት በጥሬው የዘፈረፋ እንዲሁም ሙሰኝነትና ሽርሙጥና ለህባችን ያስፋፉ ሴሰኞ ልማታዊ ባለሀብት ወያኔን ፉይናንስ የሚያረጉ ወራዳ ለትውልዱ የማይበጁ ናቸዉ

Comments are closed.

Share