ከአውሮፕላኑ ጠለፋ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ም/ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ለቀቁ

በአንድ ጎሳ እና ቋንቋ አመራር ስር ወድቋል በሚልና በዘረኝነት ሰራተኞቹን ፍዳቸውን እያሳየ ነው በሚል የሚተቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የበረራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ። እንደ ሽግግር ምክርቤቱ ዘገባ የስልጣን መልቀቂያው ጉዳይ ግልጽ ምን እንደሆነ አይታወቅም።

ሌሎች ምንጮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ስዊዘርላንድ በረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ካረፈ በኋላ በአየር መንገዱ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።

ምንጮቹ የአየር መንገዱ አብራሪዎች በቂ እውቀት እና ችሎታ እያላቸው ከውጪ አብራሪዎችን በማስመጣት ለኢትዮጵያውያኑ እድገት እና የበረራ ፍቃድ መከልከል እንዲሁም አላስፈላጊ የሆነ መንግስታዊ የደህንነት ወከባ እና የአይነ ቁራኛ ጥበቃ በአብራሪዎች ላይ ከመደረጉም በላይ የስራ መብቶቻቸው እና የሰብአዊ መብቶቻቸው በዘረኝነት ላይ የተመረኮዘው የአየር መንገዱ ማንጅመንት እንደማያከብርላቸው እነዚሁ ምንጮቹ አክለው የሚገልጹ ሲሆን፤ በወያኔ ፈጠራ ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራን “የአእምሮ በሽተኛ ነው” በሚል የተወራው ወሬም በአየር መንገዱ የሚበሩ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት እየሆነው እንደሆነም ምንጮች ይናገራሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ልክ ከግቢ እስከ ሀገር (የአብይ ቪደኦ)

6 Comments

  1. if this Information is correct they are trying to take steps as to why the Boss didnot follow up the matter when the copliot was in a health Problem and didnot send him to leave anf further medical Treatment. In other words this step will be taken as a pretext for falsifying the Situation of the political Motive of the co-pilot.

    Or if thisn part of the Story is not considered it may be to Show to the world that the Copilot has grievances, but was not adressed properly by the responsible Person and the Boss has to sacrifice himself for making such adminstrative Problems to the pilots carrer. At the end of the day they will tell us appropriate measures are taken to fix the Problem that has been surfaced during the previous months as a hot issue in the country.

    The third reason may be if the captain is innocent for himself and for the Company he may not be willing to tell a lie to the world that the Copilot has a health Problem or other reasons that made him to hijak the plane. Let is wait and see since time will tell the truth behind this Action in the Airline. He knows clearly that the Copilot has a political Motive which couldnot be denied by all means since the world has heard the copliot asking for asylum from himself. We wish him all the best for his future eventhough he has played a critical role to cultivate the rule of woyane Junta in the Company by firing ethiopian pilots that are not committed to promote the interest of woyane. We hope other important Actions will be taken by others too.

  2. እጅግ አመሰግነወታለሁ የተከበሩ የአደራ ቅኔ የኢትዮጵያ አዬርመንገድ ምክትል ሥ/ አስኪያጅ ካፒቴን ደስታ ዘሩ! ይህ ደግሞ ሌላው የተስፋ ፍንጭ ነው። የቅንጦት ፖለቲካ አራማጆችም የሚገራ ጠቋሚ መንገድ ነው።

    በተጨማሪም ምስጋናዬ የትኩስ መረጃ አውደ ምህረት ትጉኃንም።

    እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

  3. እጅግ አመሰግነወታለሁ የተከበሩ የአደራ ቅኔ የኢትዮጵያ አዬርመንገድ ምክትል ሥ/ አስኪያጅ ካፒቴን ደስታ ዘሩ! ይህ ደግሞ ሌላው የተስፋ ፍንጭ ነው። እንዲሁም የቅንጦት ፖለቲካ አራማጆችም የሀቅ አቅጣጫ ጠቋሚና ገሪ መንገድ ነው።

    እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

  4. ወያኔዎች ከሃበሻ ዶክተር የነጭ ዝሪያ ያለው ድሬሰር የሚመርጡ ናቸው። የሃገራችን ምሁራና የተዋጊም ሆነ የህዝብ ማመላለሻ አውሮጵላን ተመራማሪዎችንና አብራሪዎችን ሲመች በወያኔ ካድሬዎች ያለምንም ብቃት፤ ሳይመች በውጭ ዜጎች እየተኩ ሃገራችን ማተራመሱን ይዘውታል። በሃገራችን በአንድ ጎሳ ፍቅር የሰከረ ድርጅት እንደ ወያኔ በምድሪቱ በቅሎ አያውቅም። ብቁ የሃገራችን አብራሪዎች እያሉን ለምን በውጭ አብራሪዎች እንደሚጠቀሙ መገመት ይከብዳል። ጄኒብ የገባው ረዳት አብራሪ ቅሬታው ይህ ይሆን? ማን ነበር ቀዳሚ ካፕቴኑ? ሃበሻ የወያኔ ካድሬ ወይስ ነጭ? አሁን ካፒቲን ደስታ ዘሩ ከሥራቸው ለቀቁ ተብለናል። ለምን አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ከሥራቸው አይለቁም? የወያኔ ሂሳብ አከፋፋይ ስለሆኑ ማንም አይነካቸውም። በዘርና በጎሳ የተጠላለፈችው ውድ ሃገራችን የወያኔ መቀለጃ የምትሆነው እስከ መቼ ድረስ ነው?

  5. ካፒቴን ደስታ ዘሩ ጡረታቸው ደርሶ ነው የለቀቁት። እርሳቸውን የሚተካ ማን ይሆን? ሥራ አስኪያጅ ተወልደ፣ ምክትሉ ደስታ ዘሩ፤ ሌሎቹስ እነማን ይሆኑ?

  6. እኔ ግርም የሚለኝ ወያኔ ከሆነ ብቃት የሌለው፣ ወያኔ ሆኖ ከተሾመ በዘር ነው የተሾመው ብሎ ማላዘን እሚቀናቸው ሰዎች አሉ ይህ ግን ራሱ መነሻው ዘረኝነት መሆኑን እንኩዋን ቅንጣት ትዝ አይላቸውም ወያኔና የወያኔ ደጋፊ ወደ ስልጣን አይምጣ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለም ይሄውና አገሪቱን መምራት ከጀመረ 23 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ብቻ ቀሩት ያውም በጥሩ የልማት ጎዳና እየተጉዋዘ ብቃት ሲባል ደግሞ የቀለም ትምህርት ብቻ አድርገን መውሰዱ ትክክል አይደለም እንደ ሃይለመድህን ያሉ ከሃዲዎች አካዳሚያዊ አቅም አላቸው ተብሎ ነው እዚህ ቁልፍ ቦታ የተመደቡት ነገር ግን ሀገራችን አለኝ የምትለውንና በዓለም ዝና እና ክብር ያለውን ተቅዋም ጥላሸት ለመቀባት ነው የሞከረው ባይሳካለትም ስለዚህ በሰው ያለውን ትንሽ ጉድፍ ከማየታችን በፊት የራሳችንን —— ጠቃሚ ነው ወገን እግዚአብሄር አገራችንን ይባርክ

Comments are closed.

Share