ከድልድይ ላይ ራሷን በመወርወር ለመግደል ስትሞክር የነበረችው ወጣት ማን ትሆን?

ከዳዊት ሰለሞን

በርብርብ የተረፈችው ወጣት

ትናንት ከሰዓት አካባቢ አራት ኪሎ ለመንገደኞች መሸጋገሪያ ተብሎ በተሰራ ድልድይ ላይ የወጣች በሃያዎቹ መጨረሻ አካባቢ የምትገመት ሴት ራሷን ወደ መኪና መንገዱ ለመወርወር በምትዘጋጅበት ወቅት በአካባቢው የተገኙ ሰዎች ባደረጉት ርብርብ አደጋ ሳይደርስባት ለመትረፍ በቅታለች፡፡
ወጣቷን ለማትረፍ ሁለት የእሳት አደጋ መኪኖች ብዛት ያላቸው ፖሊሶች በስፍራው ተገኝተው የነበሩ ቢሆንም ወጣቷ ‹‹ሙስሊሞችን እወዳለሁ እነርሱን ጥሩልኝ››በማለቷ ሁለት ሙስሊም የሆኑ ሴቶች ቀርበው አነጋግረዋታል፡፡ በዚህ ቅጽበትም ሰዎች ቀርበዋት ይዘዋታል፡፡ ወጣቷን ለዚህ ውሳኔ ያበቃት ምን ይሆን?በቅርቡ ከሳኡዲ የተመለሰች ስደተኛ ትሆን? በስፍራው የነበሩ ሰዎች ይህን መሰል ጥያቄዎች እንድትመልስላቸው ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ፖሊሶች አጣድፈው ወስደዋታል፡፡የት አድርሰዋት ይሆን?

ተጨማሪ ያንብቡ:  አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም /የአማራው ፈተና

1 Comment

  1. “ፓሊሶች እያጣደፉ ወሰዶአት” አዎ የእኛ ነገር የታመመና የሚያሳምመንን ለይተን አናውቅም። ሰው የአእምሮ ችግር ካልኖረበት ራስን ለማጥፋት አይመኝም። ኑሮ ሲጭልም ሞትም ያስመኛል። ተረባርበው ህይወትዋን ያተረፉትን የሃገሬ ሰዎች አመሰግናለሁ። የወያኔ ፓሊሶች ግን ውሾች ናቸው። ምን ይጠበስ ተብሎ ነው የታመመን ሰው ማዋከብ። መቼ ይሆን ራሳችንና ህዝባችንን የምናስከብረው? አምናለሁ እስር ቤት ከተዋት እንደሚሆን። የወያኔ ሃኪም ቤት ከርቸሌ ነው።

Comments are closed.

Share