ስለ የፋሺሽት ኢጣልያ የጦር ወንጀልና ለአድዋ ድል በቀል ለኢትዮጵያ ስለሚያስፈልገው ፍትሕ – ኪዳኔ ዓለማየሁ

ኪዳኔ ዓለማየሁ

ለአድዋ የኢትዮጵያ ድል፤ ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ድጋፍ፤ ስለ ፈጸመችው የበቀል እጅግ ከፍተኛ የጦር ወንጀልና ለውድ ሐገራችን ስለሚያስፈልገው ፍትሕ፤ እባካችሁ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ሰነድ ተመልከቱልኝና በጣም ተፈላጊ የሆነውን እርዳታችሁን ለኢትዮጵያ አበርክቱ፡፡ ለበለጠ ዝርዝር፤ (www.globalallianceforethiopia.net) እና መጽሐፌን፤ (My Journey with the United Nations and Quest for the Horn of Africa’s Unity and Justice for Ethiopia) መመልከት ይቻላል፡፡

Adwa Victory and Justice for Fascist Italian War Crimes (Power Point Presentation)3

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወደ ጦር ግንባር አልሄድም፣ ትምህርት እፈልጋለሁ ብሎ መቅረት በአሸባሪው ህወሓት ያስገድላል

4 Comments

  1. አሁን ነጩ ዓለም እንባ የሚያፈስላት ዪክሬን ፓለቲከኞቿ ረጋ ብለው ድሮ ገና ቢያስቡ ኑሮ አሁን ያሉበት አጣብቂኝ ባልገቡም ነበር። እኔ የዪክሬንን ሁኔታ የማየው እንደ ዓረቡ የጸደይ እብደት ነው። ያመጣው ለውጥ የለም። በግብጽ ሙባረክ ሄደ ሌላ ሙባረክ መጣ፤ በሊቢያ ጋዳፊ ሄደ የሽፍታ መንጋ ተንጋጋ፤ በቱኒሲያ ዛሬም አልሰከነ ኸረ ስንቱ ይወራል። በነጮች የቀን መቁጠሪያ በ 2013 ግርግር የፈጠሩት ዪክሬናዊያን አውሮፓን እንቀላቀላለን ራሺያን እናርቃለን ብለው ነበር ግልብጥብጡን ያወጡት። የያኔው ራሺያ አፍቃሪ መሪያቸው አሁን ተጠልሎ ያለው በሞስኮ ነው።
    የአሜሪካን ቃል በማመን የኔቶ አባል እንሆናለን በማለት ድምጻቸውን በአደባባይ ያሰሙት (2013-2018) ዪክሬናዊያን አሁን ምን ይሉ ይሆን? ዓለም በጉልበታም የምትገዛ መሆኗን ቀድሞም አሁንም እናውቃለን። የአሁኑ 24/7 የዜና ሽፋን ሁሉ መታየት ያለበት ይህ ሁሉ መከራ የሚደርሰው በነጮች ላይ በሌላ ነጭ ባይሆን ምዕራባዊያን ምን ያረጉ ነበር ብሎ በመመርመር ነው። በኢትዮጵያ ወያኔ ባደረሰውና በሚያደርሰው ግፍ፤ የኦነጉ ሸኔ በሚያተራምሰው የኦሮሞ ክልል ስንቶች ናቸው በግፍ የተጨፈጨፉት? ይህን የዘገበ፤ ያጋለጠ የምዕራባዊያን የዜና አውታር አለ? ጭራሽ፡፡ እንዲያውም የተሳሳተና የፈጠራ ዜና እየነዙ እርስ በእርሳችን እንድንጫረስ ሲሰሩ ተስተውለዋል።
    የፋሺሽት ጣሊያ ጦር ምን ያህል በኢትዮጵያዊያን ላይ የመከራ ዝናብ እንዳዘነበ ታሪክን ከጻፈው ጋር እያገናዘቡ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። በ1896 በነጮቹ የቀን መቁጠሪያ ጣሊያኖች አድዋ ላይ የደረሰባቸው ሽንፈት ዓለምን ያስደመመ ነበር። በተለይም በአፍሪቃ አህጉርና በዓለም ዙሪያ በባርነት ተጠፍረው ለተሻገሩ ጥቁሮች ሁሉ ብርሃን ፈንጣቂና የነጭን የበላይነት ያሳፈረ የጦር ገድል ነበር። The Battle of Adwa፡ African Victory in the Age of Empire by Jonas Raymond እና ሌሎችም በሃገር ሰዎች የተጻፉ መጽሃፍትን ዋቢ አርጎ ለተመለከተ የአድዋው ድል የጥቁር ህዝቦች ድል ጭምር መሆኑን አስረግጦ ይረዳል። ጣሊያን ይህን ሽንፈቱን ባለመቀበል እንደገና ራሱን አደራጅቶና ታጥቆ ፋሺሽታዊ ወረራውን በ1935 ዳግመኛ ሲከፍት መርቀውና ይቅናችሁ ብለው ዳግመኛ የላኩት የቫቲካን ሰዎች ናቸው። ስለ ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ አያሌ መጽሃፍቶች የተጻፉ ስለሆነ ፈልጎ ማንበብ ነው። ከእነዚህ መጽሃፍቶች መካከል Prevail: The Inspiring Story of Ethiopia’s Victory Over Mussolini’s Invasion, 1935-1941 by Jeff Pearce ማንበቡ ለዛሬው ትውልድ እይታ ጠቃሚ ይሆናል። ጣሊያን በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመው በደል በሰው ብቻ ሳይሆን በእንስሳትም ላይ ነበር። ለዛሬው መሰረታችን መናጋት ዋናው ምክንያት የውጭ ሃሎችም ቢሆኑም ሥራ አስፈጻሚዎቹ እኛው ራሳችን ነን። የጥቁር ህዝቦችን ጥምረትና አንድነት ከመሻት ይልቅ በየጎጡ የዘር ጥሩንባ የሚነፉት ወስላታ ፓለቲከኞች የህዝባችን ሰቆቃ አብሰውታል። ተማረ፤ አልተማረ፤ ቄስ ሆነ ሰባኪ ያው ናቸው፡፤ በዘራቸው የሰከሩ እውሮች። ሰውን በሰውነቱ መመዘን የተሳናቸው የሰው አናብስቶች። የሚያመዛዝኑበት ጭንቅላት እያላቸው ቅራ ቅንቦ ነገር መሳዪች። እኮ በል አሁን በዪክሬን ላይ ራሽያ የምትፈጽመው አይነት ወረራ በሃበሻው ምድር ላይ የታጠቀና የጎለበተ የበላው የሚያስገሳው ሌላ ሃይል አይፈጽመውም ብሎ የሚገምት አለ? መንቃት፤ መዘጋጀት፤ አንድ መሆን አሁን ነው። የአድዋንና የሌሎችንም አንጸባራቂ ድል ስናስብ የእኛንም የዛሬ ዝግጅት በማሳመር መሆን አለበት።
    ልክ እንደ ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ ጊዜ የያኔው ሊግ ኦፍ ኔሽን ኢትዮጵያ በመርዝ ጋዝ ስትጠበስ ዝም ብሎ እንዳየው አሁንም በዪክሬን መከራ አንገባበትም ማለታቸው በራቸው ላይ እስኪደርስ ነው። ከዚያ በህዋላ የሚሆነውን የሚያውቅ የለም። ይህ ሁሉ የዪክሬን መከራ ግን አመንጭው ሁልጊዜም ከህዋላ ሆነው ሆያ ሆየ የሚጫወቱት አሜሪካኖች ናቸው። እውቁ ሳይንቲስት አልበርት አነስታይን እንዲህ ብሎ ነበር። I know not with what weapons World War III will be fought, but World War IV will be fought with sticks and stones. እኔም የሚገባኝ ይህ ነው። ጣሊያን ሁለት ጊዜ ባደረሰችው ወረራ ምክንያት የወደመው፤ የሞተው፤ የተዘረፈው ቢተመን አሃዙ የትየ ሌሌ ነው። ግን ለጥቁር ህዝብ ማን ገዶት? ማን ከሶ፤ ማን ተከሳሽ ሆኖ? እኛስ ዝንተ ዓለም አይደል እንዴ ስንገዳደል እየኖርን ያለነው? ቀና ብሎ ልብን ነፍቶ በአለም አደባባይ ላይ ተከሶም ሆነ ከሶ ለመሟገት እኮ የራስንም ባህሪ ማስተካከል ተገቢ ነው። ብቻ ዓለማችን በዚህም በዚያም ውልግድናዋን ቀጥላለች። ለመኖር ሰው ሆን ብለው በሚያስርቡበት የሃበሻ መሬት ምን አይነት ፍትህ ነው ከነጩ ዓለም የምንጠይቀው? እኛ ሰው ሆነን ህዝባችን ሰው እንዲሆን ስንሰራና ሰላም በምድሪቷ ሲሰፍን ያለፈንም የአሁንንም ለማስታረቅ ጉልበት ይሰጣል። አሁን ባለንበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ ሱሪን በአንድ እጅ ይዞ ሩጫ በመሆኑ ሩቅ የሚያደርስ ህልም ሰው የለውም። በቃኝ!

  2. አቶ ኪዳኔ እውነት ለመናገር ትግሬና ኦሮሙማ ከፈጸመብን በላይ ጥልያን አልፈጸመብንም። እነሱ ለፈጸሙብን ለማን አቤት እንበል?

  3. ሁለቱንም ወንጀለኞች ለፍትሕ ማቅረብ ነው፡፡ አንዱን ወንጀለኛ ለሌላው ምክክንያት በማድረግ ችላ ማለት ለሐገር ከፍተኛ ውርደት ነው! የፋሺሽት ኢጣልያኖች መሳለቂያ እንዳንሆን መጠንቀቅ ይሻላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share