ንጉሱ አብይ በአድዋ የፈጸመው ገድል – ምስጋናው አንዷለም

እነሆ ስም አጠራሯ በሻሻ በተባለች አንዲት አገር አንድ አይነ ገብ፣ መልከ መልካም እና ቁመተ ረዥም ልጅ ነበረ፡፡ ይህ ልጅም አባቱ ይሁኑ እናቱ አልታወቁም እንጅ በተወለደ ጊዜ ስሙን አብዮት አሉት፡፡ አስራ አራት አመት በሆነውም ጊዜ አቦይ ስብሀት ለተባሉ የትግሬ አገር ባላባት በአደራ ልጅነት ተሰጠ፡፡ የአቦይ ስብሀትን ምክር በመቀበልም አብዮት የተባለውን ስሙን ወደ አብይ ቀየረ፡፡ አቦይ ስብሀት አብዮት የሚለው ስም የደርጊ ጸላኢ ስም ነው ብለው ነበርና አብዮት በሚለው ስሙ ሊጠራ አልሆነለትም፡፡ ስሙን አብይ ብሎ በቀየረ ጊዜም እኒህ የትግሬ ባላባት ደስ አላቸው፤ ወደዱት፤ ማንጁስ አሉት፡፡ ሌሎቹም የትግሬ ሹማምንት ማንጁስ እያሉት ይላላክላቸው ነበር፡፡ የባላባቱ አቦይ ስብሀትም ስልክ ጠላፊ ሆነ፡፡
ብዙዎችንም የትግሬው ባላባት ጠላት የሆኑ አረመኔዎች አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሶማሌዎች፣ ጉራጌዎች እና የአዲስ አበባ ሰዎች ወደ እስርቤት ያስወረወር ነበር፡፡ አሳዳጊውን አቦይ ስብሀትን ለማስደሰት ከነበረው ፍላጎት የተነሳም ለአይኑ ደስ ያላሉትን ሁሉ ያስር እና ያስደበድብ ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀንም የእናትና አባት ሀይማኖቱን ቀይሮ ክርስቲያን ሆነ፡፡ አሳዳጊው አቦይ ስብሀትም ደስ አላቸው፡፡ ምንም እንኳ አቦይ ስብሀት ኮሚኒስት የተባለውን ሀይማኖት ቢከተሉም ለክርስቲያኖች አልፎ አልፎ በጎ እይታ ነበራቸውና ይህ አብይ በፊታቸው ሞገስ አገኘ፡፡ ይህ አብይም ክርስቲያን ከሆነ በኋላ የጠለፈው ስልክ ቀድሞ ያደርግ ከነበረው የበለጠ ሆነ፡፡ የትግሬ አገር ስዎችም፤ ንጉሱን መለስ ዜናዊን ጨምሮ፤ ወደዱት፡፡ አረመኔዎችን አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሱማሌዎች፣ ጉራጌዎችና የአዲስ አበባ ሰዎችንም እንዲያጠፋላቸው ተስፋ አደረጉበት፡፡ ብዙዎችንም አጠፋላቸው፡፡ የትግሬ አገር ሰዎችም ከጠላቶቻቸው አርፈው ብዙ አመት ገዙ፣ ነዱ፣ ዘፈኑ፣ በሉ፣ ጠጡ፣ ደስም አላቸው፡፡ ይህ አብይ የተባለውም ስልክ ጠላፊ ወታደር እንዲሁ ያደርግ ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀንም ጥልያን የተባለ ከባህር ማዶ የሆነ፤ እጅግም ከራቀ ምድር የሆነ፣ መንግስት ሀገረ ኢትዮጵያን አስገብሬ እገዛለሁ፤ ስሜንም እተክልባታለሁ ብሎ እልፍ ጦር አስከትሎ መጣ፡፡ ይህም አብይ የተባለው ስልክ ጠላፊ ወታደር በትግሬው ባላባት ይሁንታ የበሻሻ፣ ወንጭና ጨለንቆ ገዥ ሆኖ ተሾመ፡፡ በአምባላይ ፈረሱም ላይ ተቀምጦ አድዋ ወደተባለው አሚጸኛው ጥልያን በመሸገበት ተራራ ላይ ደረሰ፡፡ በፈረሱ ሽህ፣ በጎራዲውም ሽህ የጥልያን ሰራዊት ፈጀ፡፡ ጥልያንም በየካቲት ጊዮርጊስ እለት በዚህ ብርቱ ስልክ ጠላፊ ወታደር አብይ ሀይል ተደቆሰ፡፡
በየቦታው ተበታትኖ ውሀ ውሀ ይልም ነበር፡፡ ይህም አብይ ውሀ ውሀ ለሚሉት ጥልያኖች አንዳንድ ችግኝ ለጥላ ይሆና ቸው ዘንድ እጎናቸው ትከሉላቸው አለ፡፡ በዚህም አድራጎቱ የአድዋ ተራራ በዛፍ ተሸፈነ፡፡ ይህም ስልክ ጠላፊ አብይ የካቲት ጊዮርጊስ በሆነ እለት ሁሉ ይከበር ይዘከር ነበር፡፡
——————————-

ተጨማሪ ያንብቡ:  የ100 ቢልየን ብር ሃብት የ100+ ሚልየን ህዝብ ጉዳይ ነው፤ - ነብዩ ስሁል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share