በጀግናው የቴዎድሮስ ብርጌድ በግዳጅ ወቅት የተመዘገቡ ውጤቶች መካከል ለስለለ የመጣ የአሸባሪው ብድን ሰላይ 5 ቦንብ እና ስታር ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሎአል

በተከዜ ግንባር መስዋትነትን ሲከፍል ለነበረው ለጀግናው የቴዎድሮስ ብርጌድ የግዳጅ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫ የምክክር መድረክ “ጀግኖች በእናንተ መስዋትነት ኢትዮጵያ ምንግዜም ትኮራለች” በሚል መሪ ቃል የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት በዞን አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ክብር አቶ ዘውዱ ማለደ በመልዕክታቸው የመጀመሪያውን ምዕራፍ በድል አጠናቀናል እንኳን ደስ አለን ይህ ጀግና ብርጌድ መከላከያ የሰው ኃይል በፈለገበት ሰአት ከሌሎች ብርጌዶች ቀዳሞ የተገኛ ጀግና ብርጌድ ነው።

በተጨማሪም ይህ ብርጌድ የጎንደር ህዝብ የሰጣችሁን አደራ አኩሪ በሆነ መንገድ ፈፅማችሃል ወደ ከተማ ስትገቡ ጥይት አትተኩሱ ስንል ቃላችሁን ጠብቃቸህ በመግኘታችሁ በከተማ አሰተዳዳር ስም አመስግነዋል።

በመጨረሻም የመጀመሪያውን ምዕራፍ በድል አጠናቀናል ቀጣይ ለሚገጥምን ሁለንተናዊ ግንባር በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ልንዘጋጅ ይገባል። ጦርነቱ ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም ስለዚህ የመጨረሻው ግባችን የሚሆነው ወያኔን እስከ መጨረሻ መቅበር ስንችል ነው::

የምክክር መድረክ ላይ በመገኘት የጎንደር ከተማ አስተዳደር አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አዝመራው ተዘራ የግምገማ ሰነድ በፕሮግራሙ ለተገኙ ተሳታፈዎች አቅርበዋል።

የቴዎድሮስ ብርጌድ በርካታ በሆነ የሰው ኃይል የተዋቀረ ሲሆን በዘመቻው ወቅት በቆየበት ግንባር ከፍተኛ አስተዋፅኦም አበርክቷል።

የብርጌዱ ጠቅላላ አባላት በሶስት ዙሮች የስልጠና ሰነድ ተዘጋጅቶ ለምን እንደሚዋጋ የአማራ ህዝቦች እሴቶችን የተመለከተ ወሳኝ ስልጠናዎችን እንዲወስድ ተደርጎል::

የብርጌዱ አባላት ሁለንተናዊ በሆነ ስነ-ምግባር የተመሰገኑ በጦርነቱ ላይም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የሚወጣ ነበር። ለረዥም ጊዜ ከቤተሰብ ተለይቶ በመቆየት ሀገር የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ተችሏአል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቀጠናዉ ስጋናትና አሸባሪዉ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መለቀቅ ተጀምሮ የነበረው የኢትዮ ኤርትራ ግኑኝነት እንደሚያሻክረዉ የኤርትራው ፕሬዘዳንህ ኢሳያስ አፈወርቂ ገለፁ !!

በነበርን ጠቅላላ ቆይታ ምስጋና ለጎንደር ህዝብና ለጠቅላላ አመራሩ የሎጀስቲክ ሁኔታ የአቅርቦት ሆነ የስርጭት ችግር አልገጠመንም ።

በጀግናው የቴዎድሮስ ብርጌድ በግዳጅ ወቅት የተመዘገቡ ውጤቶች መካከል ለስለለ የመጣ የአሸባሪው ብድን ሰላይ 5 ቦንብ እና ስታር ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሎአል። ምሽግ ለሰበሩ ክ/ጦሮች ከፊት በመሆን ሽፋን የሰጠ ጠንካራ ብርጌድ ነበር ::

በአጠቃላይ ጦርነቱ ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም ስለዚህ የመጨረሻው ግባችን የሚሆነው አሽባሪው መቅበር ስንችል ነው ለዚህ ደሞ ያጋጠሙንን ድክመቶች በማረም ለቀጣይ ድል ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል ብለዋል::

በመጨረሻም የቴዎድሮስ ብርጌድ አባላት በግንባር ያጋጠማቸውን እና ለቀጣይ ሊስተካከል ይገባል ያሉአቸውን ጉዳዩች አንስተው ፕሮግራሙን ከመሩት የከተማዋ ከፍተኛ አመራር ጋር ተወያይተውበታል ::

ለጎንደር ከተማ ቴዎድሮስ ብርጌድ እና የጎንደር ከተማ ታዎድሮስ ብርጌድ ጤና ባለሙያዎች ቡድን የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶል በተጨማሪም በየሻምበሉ ላሉ አካላትም የምስጋና የውቅና የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል ክብር ከንቲባችንም ለጀግናው ብርጌድ ለከፈላችሁት እና እየከፈላችሁ ላላችሁት መስዋዕትነት በከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቀርበዋል።

#እናልማ_እንገንባ_እንዘጋጅ!

መረጃው የጎንደር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የዲጂታልና የማህበራዊ ሚዲያ ክፍል ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share