በኢትዮጵያ የጤና ተቋማት በአሸባሪው ሕወሃት ሲወድሙ የዓለም ጤና ድርጅት ዝምታን መምረጡ የሚያሳዝን ነው

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የጤና ተቋማት በአሸባሪው ሕወሃት ሲወድሙ ከማውገዝ ይልቅ ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ጤና ተቋማት በአሸባሪው ህወሃት ሲወድሙ ዝምታን መርጧል ብለዋል።
ድርጅቱ ለጤና ተቋማት በግንባር ቀደምትነት መሟገትና መከራከር የሚገባው ተቋም ቢሆንም የተከሰቱትን ውድመቶች በዝምታ ማለፉ አሳዘኝ መሆኑን ነው የገለጹት።
በተመሳሳይ የተ.መ.ድ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የላልይበላን ቅርስ ደኅንነት በተመለከተ ምንም አለማለቱ አስገራሚ መሆኑን ተናግረዋል።
በአፋርና በአማራ ክልሎች በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሃብ ሲዳረጉ የዓለም ምግብ ድርጅት ዝምታን መርጧል ነው ያሉት።
የተቋማቱ ሁኔታ የተነሱበትን መርህ በመተው ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያራምዱት አቋም እርስ በእርሱ የሚጋጭና አድሏዊነት የሚስተዋልበት መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የአንዳንድ አገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸው ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ መወትወታቸውም ትክክል አለመሆኑን ጠቁመዋል።
እነዚህ ኤምባሲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አምባሳደሮቹን በመጥራት አገሪቱ ውስጥ ያለውን አውነታ በተመለከተ ተከታታይ ማብራሪያ እየተሰጠ መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
አምባሳደሮቹ በተለይም በአፋርና አማራ ከልል ጉብኝት በማድረግ በክልሎቹ የደረሱትን ውድመቶች በአካል መጥተው እንደሚመለከቱ ተደጋገሚ ጥሪ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ቻይና ለአፍሪካ አገራት ከቀረጥና ከታሪፍ ነጻ ያቀረበችውን እድል ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምትነት ለመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየቷን ገልጸዋል።
በተለያዩ የዓለም አገራት ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚያደርጓቸው የ”በቃ” ወይም #NOMORE ዘመቻ ውጤት ማስገኘቱን ጠቁመው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
-አካባቢህን ጠብቅ፣
_ ወደ ግንባር ዝመት፣
_ መከላከያን ደግፍ።
ታህሳስ 5/2014 (ኢዜአ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለብዙሃኑ የሠራዊቱ አባል ወገናችን!!

1 Comment

  1. ካወሮበላ፣ ሌባና ወንጀለኛ ግሩፕ ምን ይጠበቃል፡፡ ዓለም ላይ በጣም የተቀለደበት ዘመን ሆኗል፡፡

    This WHO joking on people of the world, they are doing a mess in world communities.
    Who blame them???????????????

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share