ሰራዊትታችንን ከጀርባው አጥቅቶ ያሞራ ሲሳይ ሲያደርግ ከበሮ ይዘው የጨፈሩ-ለከንቱ አላማ የትግራይ ወጣት ረገፈ

ለአመታት በቀበሮ ጉድጓድ ሲጠብቀው የነበረን የሀገር መከታ የሆነውን ሰራዊትታችንን ከጀርባው አጥቅቶ ያሞራ ሲሳይ ሲያደርግ ከበሮ ይዘው የጨፈሩ፣ በምርኮኛ ስም በባዶ እግሩ እያስኬዱ በየከተማው የተሳለቁ፣ አልሸባብ በሞቃዲሾ እንዳደረገው በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ ሰንደቅ አላማችንና የሰራዊታችን ዩኒፎርም በመኪና እየጎተቱ የጨፈሩ፣
በአዲስአባ ሆቴሎች ‘መቀሌን ያዝን’ በሚል አጉል ደስታ ባንዲራ እያቃጠሉ ሲጨፋሩ ያላፈሩ፣ ከማይካድራ ጀምሮ በየደረሱበት ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) እየፈጸሙ አክሱም ላይ ለተፈጸመው ብቻ አልቅሱልኝ የሚሉ፣ አንድ ሺህ በላይ የእርዳታ መኪናዎችን አግተው ይዘው ለጦርነት እንቅስቃሲያቸው እያዋሉ እያየን ‘እርዳታ እንዳይገባ ተደረገ’ ብሎ በሰባዊ እርዳታ ስም ፖለቲካ ትርፍ የሚሰሩ. …. ገና ለገና የውጭ ኃይል በሰባዊ ድጋፍ ስም ጣልቃ ይገባል ብሎ ‘ህዝቤ ነው’ የሚሉትን ማህበረሰብ በረሀብ እንዲቀጣ እያደረጉ የፖለቲካ ጨዋታ የሚጫወቱ፣ ….. አምና በሰኔ ወር የተናጥል ተኩስ አቁሙን ባለመቀበል ጦርነቱን እስካሁን እንዲቀጥል ሲደረግ…. ድርጊቶቹን አደለም ሊኮንኑ እነዚህ ድርጊቶችን በጋራ እንደቅድስና ሲቆጥሩ ስመለከት ያኔ በዚህ ሀይል የቀረችኝ እንጥፍጣፊ ተስፋዬ ተነነ።
ጎበዝ በዚህ ሀይል ዙሪያ የተሰበሰበ ሁሉ ይሉንታ ቢስ፣ እፈረት አልባ፣ እራሳቸውን ብቻ የሚያዳምጥ ናቸውና የትግራይ ህዝብ ህወሃትን በመራው የጥፋት ሀይል ላደረሰው በደልና ሰባዊም ሆነ ቁሳዊ ውድመት በልጆቹ ደም ላይ ቆሞ በኩራት ያጨበጭባል እንጂ መሪዎቹን ተጠያቂ ያደርጋል ብለህ እንዳትጠብቅ። ትግራዋይም በስሜት ከገቡበት አዘቅት ውስጥ እስኪነቁ ድረስ የህወሓት መግለጫዎችም ይቀጥላል።
እኔም ጉዳዩ ሀገር የማዳን ጉዳይ ነውና አንተ ሀገር ለማፍረስ ስትመጣ እኔም ሀገሬን ለማትረፍ ከማንም ጋር አብሬ እሰልለፋለሁ።
ይሄው ነው!
አንተነህ መለስ
ተጨማሪ ያንብቡ:  Ethiopia plans power exports to neighbours

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share