በአማራ ክልል በሚደረገዉ ጦርነት ምክንያት ከ6 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለርሀብ ተጋልጠዋል

ዓለምአቀፍ ረጂ ድርጅቶች በጦርነት ቀጠና ላሉ ወገኖች እርዳታ ለማቅረብ ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን ያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ግን ለሕዝቡ ርዳታ አለመስጠታቸዉን አቶ ዘላለም አስታዉቀዋል።
አስቸኳይ ርዳታ የሚሻዉ 6 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ ባለማግኘቱ ሕብረተሰቡ ከተጋረጠበት አደጋ በራሱ ትግል ሊወጣ እንደሚገባ ኮሚሽነር ዘላለም መምከራቸዉን የባሕርዳሩ ወኪላችን የዓለምነው መኮንን ዘገቧል።
ይህን የዘገበው DW ከሁለት ቀናት በፊት ። ሌሎችም ሚዲያዎች ዘግበውታል።
የምጽፈው ይነበቧችኋል ? 6 ሚሊየን ለረሃብ ተጋልጧል ነው’ኮ የሚሉት ።
ታዲያ ይሄን እያዩ እየሰሙ ዝም ይባላል ወይ ?
መላ አይፈለግም ወይ ?
አይቶ እንዳላየስ ይታለፋል ወይ ?
ሰበር ዜና ተያዘ ተለቀቀ እየተባለ ህዝብ እያለቀ ዝም ይባላል ወይ ?
ዜናው ከ 4 ቀን በፊት የወጣ ነው። ሰበር ዜና ያልኳችሁ ሰበር ዜና ካልተባልን የወገኖቻችን ያሉበትን መረዳት ስላቃተን ነው ።
Via abdurahim ahmed
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጢስ አባይ ቃልኪዳን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share