በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ ምስክር ማሰማት ጀመረ

image

ጥቅምት 10:2014 – የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት የተሰየመው ምስክር ለመስማት እና የቀሩ መስካሪዎችን ዝርዝር ለመቀበል ነው።

ሒደቱ እንደተጀመረ ዐቃቤ ሕግ ታዳሚዎች በስልክም ሆነ የድምፅ መቅረጫ ይዘው ፍ/ቤት ሪከርድ እንዳያደርጉ እና ፎቶ እንዳያነሱ በተጨማሪም የቀሩት 12 የወደፊት ምስክሮች ሥም ዝርዝር በማኅበራዊ ሚድያ እንዳይገለጽ አቤቱታ አቅርቧል።  ፍ/ቤቱ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ወስኖ የሚያሳውቅ ይሆናል በማለት ወደ ምስክር መስማት ሒደት እንዲገባ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ነገር ግን ችሎቱ ለታዳሚዎች መቅረጽም ሆነ ሪከርድ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ዐቃቤ ሕግ አለኝ ካላቸው 21 ምስክሮች ውስጥ 9 ምስከሮች ዝርዝር ለፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን፥ በትላንትናው ዕለት የሁሉንም ምስክሮች ጭብጥ በማስመዝገብ ነው የጠዋቱን የችሎት ውሎ ምስክር ማሰማት የጀመረው።

አንደኛ ምስክር  በአንደኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ እንደሚመሰክሩ ዐቃቤ ሕግ አስረድቶ፥ አንደኛ ምስክር አቶ ፋንታሁን አሰፋ ደበላ ምስክርነት ሰጥተዋል።

በመጀመሪያ ከተከሳሽ እስክንድር ነጋ ጋር የሚተዋወቁት በ2005-2006 በማረሚያ ቤት በውንብድናና ዘረፋ ዕድሜ ይፍታህ ተወስኖባቸው በማረሚያ ሳሉ ከተለያዩ ዞኖች ወጥተው ማቆያ ላይ የሆነ ሰው “እስክንድርን አታውቀውም?” ብሎ እንዳስተዋወቃቸው ገልጸዋል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ ደግሞ በ2012 በግምት የካቲት ወይም መጋቢት ወር ላይ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አከባቢ ኬላ የሚባለው አካባቢ ያለ አውቶብስ ፌርማታ አካባቢ እስክንድር ጫማ ሲያስጠርጉ አግኝተውት “እስኬው” ብሎ ሰላም እንደተባባሉ እና እስክንድርም “መቼ ተፈታህ?” ብሎ እንደጠየቃቸው፣ በመጨረሻም “እንገናኛለን” ተባብለው እንደተለያዩ ገልጿል።

በግምት ከአንድ ወር 15 ቀን በኋላ አሸብር የሚባል ግለሰብ (በመዝገቡ 6ኛ ተከሳሽ የነበሩት) “እስኬው ሊያገኝህ ይፈልጋል” ብለዋቸው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጋር እንደተገናኙ እና ተቀምጠው እንዳወሩ ለችሎቱ በማስረዳት፣ እስክንድር “ስለመሣሪያ ታውቃለህ?” ብሎ ጠይቆኝ “አዎ” እንዳሉ። እንዲሁም በቆይታቸው በአብዛኛው ስለቤተሰብ እንዳወሩ እና እስክንድር “ሥልጠና ትወስዳላችሁ” ብሎ እንደነገረው እና እስክንድር ስልክ ሲደወልለት “5000 አውጥቶ ለአንዳንድ ነገር ትሆናችኋለች” ብሎ ለአሸናፊ ሰጥቶት ትቷቸው እንደሔደ አስረድቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቆቦና አራዶም ከተሞች ነዋሪዎች የህወሓት ኃይሎች ጥቃት ኢላማ ሆንን ሲሉ ይከሳሉ

በሌላ ቀን አሸናፊ ከሚባለው ግለሰብ ጋር አብረው ምግብ እንደበሉ፣ የዚያኑ ቀን አሸናፊ እንዲመጡ እንዳዘዛቸውና መኪና ውስጥ እንደገቡ ምስክሩም “ልንሄድ ነው እንዴ?” ብለው ሲጠይቁ አሸናፊ “አዎ” እንዳላቸው አስረድተዋል። በዋና ጥያቄ ከዚህ በኋላ ረጅም ጉዞ እንደተጓዙ እና መንገድ ላይ ሌሎች አራት ሰዎች እንደተቀላቀሏቸው እና የሆነ ቦታ ሲደርሱ እንደወረዱ ምስክሩም “ይህ አገር ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ “አታውቀውም እንዴ? በማደግ ላይ ያለች ከተማ ሞጣ ነች” ብለው እንደነገራቸው ነገር ግን እነሱ በነገሯቸው እንጂ ሞጣ መሆኗን እንደማያውቁ በመስቀለኛ ጥያቄ ሲጠየቁ ተናግረዋል።

በመቀጠልም ሞጣ ተብሎ በተነገረው ከተማ ከአሸናፊ እና ሌሎች አራት ሰዎች ጋር ለ4 ቀን በአንድ ቤት ውስጥ እንደቆዩ፤ በቆይታቸው ወቅት አሸናፊ የተባሉት ግለሰብ ሱሪ ውስጥ 5 የተለያየ መታወቂያ ሻወር በሚወስዱበት ወቅት ወድቆ እንዳዩ፣ ነገር ግን ለሰውየው “ምንም አላየሁም” እንዳሉት አስረድተዋል። በመጨረሻም 2012 ሚያዚያ ወር ወደ አዲስአበባ እንደተመለሱ ገልጿል።  በተጨማሪም ከተመለሱ በኋላ አሸናፊን ለማግኘት ሞክረው “አንድ ግዜ እንዳትከተለኝ ብሎ ሽጉጡን በማሳየት አስፈራርቶ ጥሎኝ ሔደ፤ አንዴ ደሞ ማታ ላይ ስከተለው እንዳትከተለኝ ብሎ ሽጉጥ ተኩሶ ስቶኛል”  ብለው ገልጸዋል።

ትዕዛዝ ሰጪው እስክንድር እንዴት እንደሆነ እንዳወቁ እና ዐቃቤ ሕግ ወስደዋል ያለውን ሥልጠና ማግኘት አለማግኘታቸውን በሚመለከት ሲያስረዱ በስልክ የሚደርሳቸውን ትዕዛዝ አሸናፊ ስልክ በሚያወራበት ወቅት በሙሉ ማነው ስለው እስክንድር ነው ስለሚለኝ ነው ቢሉም፣ ሥልጠናውን ግን እንዳልወሰዱ አስረድተል።

ምስክሩ የደረሰባቸውን የማስፈራራት እና ተተኩሶ መሳታቸውን ለማን አሳውቀው እንደነበር ተጠይቀው፣ ለፖሊስ እንዳሳወቁ ነገር ግን ድጋሚ እንዳልሔዱ፣ በተጨማሪም ከዐቃቤ ሕግ ጋር ተገናኝተው እንደማያቁ እና ጥበቃ ይደረግልኝ ጥያቄ ጠይቀው እንደማያቁ አያይዘው በመስቀለኛ ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። እስክንድር ነጋ በበኩላቸው ምስክሩን እንደማያቁት፣ ከዚህ በፊት በእስር በነበሩበት ወቅት ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግባቸው እና ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እንደማይገናኙ አሳውቀዋል። ምስክሩ ወደዚህ ጉዳይ የገቡት ለምን እንደሆነ ተጠይቀውም መሣሪያ እና ብር ለማግኘት እንደሆነ መልስ ሰጥተዋል፤  ነገር ግን ብር ፍለጋ ከሆነ ለአሸናፊ የተሰጠውን ብር እንዴት አልተካፈሉም ለሚለው ጥያቄ መልስ ሳይሰጡበት አልፈዋል። ችሎቱ ከሰዓት በኋላ የቀጠለ ሲሆን ከሰዓት በቀጠለው ችሎት ተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ለዐቃቤ ሕግ አንደኛ ምስክር አቅርበዋል። ምንም እንኳን የተከሳሾች መስቀለኛ ጥያቄ ያለቀ ቢሆንም ችሎቱ በሒደት ላይ እያለ በመምሸቱ  በይደር እንዲቀጥል አድሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልቃይት አስተዳደር ለህወሃት ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጠ | "አብይን አህመድን ገርስሰን ጥለነዋል" ፋኖ ማርሸት | የመቀሌ - አዲስ አበባ መንገድ ፋኖ እጅ ገባ | ጀነራል አበባው ጀነራል ተገኝ አስቻለውን ገደለው | “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፤ ወልቃይትን እንይዛለን” ግምገማ | በአብይ ትዕዛዝ ሚ/ሩ በርካታ ሚሊዮን ብር ዘረፈ |

Center for Advancement of Rights and Democracy (CARD)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share